#አውጅ_ቢን_ኡኑክ
አውጅ የነብዩላህ አደም የልጅ ልጅ ነበር። በጣም ረጅም እና ግዙፍ ቁመቱም 3300 ክንድ ይረዝም ነበር። አውጅ ቢን ኡኑክ እስከ 4,500 አመት እድሜ ያለው ሰው ነው። በነብዩላህ ኑህ عليه سلم ዘመን አላህ መርከብ እንዲሰሩ አዘዛቸው። መርከቡ ለመስራት ግን እንጨት ያስፈልጋቸው ስለነበር እንጨቱ የሚገኘው ኩፋ ውስጥ ነበር እናም ኑህ ካሉበት በጣም ስለሚርቅ ተጨነቁ በዚህ ጊዜ አላህ ራእይ አወረደላቸው አውጅ ቢን ኡኑክን ጠይቅ አላቸው። እሳቸውም አውጅን ጠየቁ እሱም ቅድመ ሁኔታ ጠየቀ ሆዴ መሙላት ስላለበት ምግብ አቅርብልኝ አላቸው። ኑህም ምግብ ሰጡት ሊያጠግበው ግን አልቻለም በመጨረሻ ቢስሚላህ ብሎ እንዲበላ ነገሩት በዚህ ጊዜ ቢስሚላህ ብሎ ሲመገብ ጠገበ። እንጨቱን አመጥቷላቸው መርከቡን ሰሩ። የጥፋቱ ውሀ በመጣና አለምን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ ለአውጅ ግን የውሃው ከፍታ ከጉልበቱ መብለጥ አልቻለም ነበር።
አንዳንዶች በተራሮች ላይ እንደሚኖር ይናገራሉ ረሃብ ሲሰማው አሳ ከባህሩ ስር አውጥቶ በፀሐይ ሙቀት ይጠበስ ነበር። ሰዎችን እንደቆሎ ያፍስ ነበር።
በነብዩላህ ሙሳ ዘመን ዐውጅ ሙሳንና ህዝቦቹን ሊያጠፋ አሰበ። ከዚያም አውጅ የነብዩላህ ሙሳን ወታደሮች መኖሪያ ቤት ለማየት መጣና ከቦታው ብዙም ሳይርቅ የነብዩ ሙሳ ወታደሮችን መኖሪያ አገኘ። ከዚያም በዙሪያው ያሉትን ተራሮች ነቅሎ በነብዩላህ ሙሳ ወታደሮች ላይ ሊወረውር ተራሮቹን ከጭንቅላቱ አኖራቸው። አውጅ ከጭንቅላቱ በላይ የተያዙትን ተራሮች በነቢዩ ሙሳ ወታደሮች ሊወረውር ጊዜ ከማግኘቱ በፊት አላህ ሁድ(የጀነት) አእዋፍ አማካኝት የአልማዝ ድንጋይ ልኮ አውጅ በያዘው ተራራ ላይ አስቀመጣቸው። አልማዝ በአላህ ሃይል በአውጅ የተያዘውን ተራራ አንገቱ እስኪደርስ ድረስ ዘልቆ ገባው መቋቋም አቃተው። 'አውጅ አልማዙን ለማስወገድ ፈቃደኛ አልነበረም፣ በመጨረሻ ሙሳ መጡ።
የነብዩላህ ሙሳ ቁመት አርባ ክንድ ሲሆን የበትራቸውም ርዝመት አርባ ክንድ ነበር እና ከቁመታቸው በላይ አርባ ክንድ ዘለው (80 ክንድ) አውጅን በበትራቸው ቁርጭምጭሚቱ ላይ መቱት። በዚያን ጊዜ አውጅ ሙሳ ሆይ ወደ ቀኝ ልውደቅ ወደ ግራ አላቸው ሙሳ ተንኳሉን ስለሚያቁ ወደ ቀኝ አሉት የዚህን ጊዜ ወደ ግራ ወደቀ ግራ ቢሉት ኖሮ ወደ ቀኝ ይወድቅና ሰዎች ላይ ጉዳት ያደርስ ነበር ወደ ቀኝ ሲወድቅ ቀይ ባህርን ለሁለት ከፈለው ለዘመናትም መተላለፊያ ድልድይ ሆነ ሰውነቱንም ጅብ በልቷ እንደጨረሰው ይነገራል። አውጅ በአላህ ሱ.ወ ፈቃድ ወደቀ በመጨረሻ ምንም እንኳን ረጅም እና ከፍተኛ ጥንካሬ ቢኖረውም ከሞት ማምለጥ አልቻለም።
ኢብኑ ከሲር እንዲህ ይላሉ "ስለ አውጅ ዘገባዎች ለመዘገብ ያሳፍራሉ ምክንያቱም 'የአደም ዝርያዎች ተክለ ሰውነት ከዘመን ፍሰት እያነሰ እንደሚመጣ ከሚናገረው ሶሂህ ሀዲስ ጋር ይጋጫል። ምክንያቱም አባታችን አደም ርዝመታቸው 60 ክንድ ነበር" ብለዋል።
*የአደም ልጅ ከሁሉ ፍጥረት የላቀው በግዝፈቱ አይደለም እንደዛ ቢሆንማ ዝሆን ከሰው ይልቅ በከበረች። ሁሌም ይህን በልብህ አኑር: ጥበበኛውን አላህ ማወቅ የልዕቅና ሁሉ ሚስጥር ነው።
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM