«ንቀውናል» ነው ያሉት?😉
°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ጫና ሲበዛባቸው ትላንት ባደረጉት የይምሰል ስብሰባ ላይ .. «የሙስሊሙን ብቸኛ መሪ በመናቅ በማን አለብኝነት ሄደው መስጂዶችን አፈረሱ» .. ብለው ሲናገሩ ሰምቼ እንደ ሁሌው ሁሉ የሰውየው የዋህነት አስገረመኝ።
ሲጀመር የሙስሊሙን ተቋም በዘ^ር፣ በጎጥ፣ በወሃ^ቢያዊ ቡድ^ንተኝነት በመቀራመት፣ ሰፊውን ሙስሊም በማግለል፣ ቡድ^ንን መሠረት አድርጎ መስጂዶችን በመቀማት ተቋሙን ያጠነ^ባውና ያዋ^ረደው ማን ሆነና?!
ሰሞኑ መስጂዶች እየፈረሱ ጭምር እነ መሀመድ አባተና አቶ ሱልጣን አማን ግን መስጂዶችን በፖሊስ ኃይል በመቀማትና በማስበጥበጥ፣ ሙስሊሞችን በማሳሰር፣ በማስደብደብ፣ ኢማሞቹን አባረው በምትካቸው ቡድናቸውን በመሾም ተጠምደውና እረፍት አጥተው እንደሰነበቱ እያወቃችሁ?! በዚህ ጥበ^ታችሁ ፈፅሞ ሰፊውን የሙስሊሙን ኡማ አትመጥኑም፤ ጭራሹኑ አዋረዳችሁት።
ደሞ መንግስት እራሱ ዑለሞቻችንን አዋ^ርዶ ከመጅሊሱ እንዲያባርር ከተመሳጠራችሁ በኃላ፤ መንግስት በአፈሙዝ ኃይል የመጅሉሱን በሩን ገንጥሎ አዝሎ አስገብቷችሁ ምን ዓይነት ክብር ነው ከሱ ምትጠብቁት?! እራስን አዋ^ርዶ መከበር ከየት ይመጣል?!
መሳጂዶችን ሚያፈርሰውና ቁርአንን ሚያዋ^ርደው መንግስት እናንተን መጅሊስ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈለው «ለኢስላም አዝኖ ነው» እንደማትሉን መቸም ተስፋ አደርጋለሁ። የመንግስትን ፖለቲካ እንድታስፈፅሙና የሱ አሽ^ከርና ተላ^ላኪ እንድትሆኑ በሚል አዝሎ እንዳስገባችሁ ከማንም በላይ እናንተው ታውቁታላችሁ። ታዲያ አሽ^ከሩን የሚያከብር ማን አለና ነው መንግስት ንቆ^ናል ምትሉት?! መጅሊሱንም ሆነ ሙስሊሙን ከእናንተ በላይ ማን ያዋ^ረደ አለና?!
መንግስት ምን ያህል እንደና^ቃችሁና እንዳቀ^ለላችሁ ምታውቁት ለመከላከያ የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ በሚል ስም በተዘዋዋሪ ሰልፈኞቹ መንግስትን እንዲደግፉ ለማድረግ ለዛሬ እሁድ ግንቦት 20/2015 በሸገር ሲቲ ሰልፍ ሲጠራ ነው። መንግስት እናንተ በሰልፉ ላይ ኖራችሁም ቀራችሁም ምንም አታመጡም እያላችሁ ነው። ሰልፉን ሚደግፍና ሚያደምቅ በቂ የፕሮቴስታንት ኃይል እንዳለው ሊያሳያችሁ ነው።
እናንተ ነባሩን ሙስሊም ለማግ^ለልና ከገዛ ተቋሙ ለማፈ^ናቀል በጠ^ባብነት ሩጫ ተጠምዳችሁ ሳላችሁ መንግስት ግን ሚፈልገውን ሁሉ አድርጎ ጨረሰ። እናንተ ዑለሞቻችንን በየጊዜው በማሳሰር፣ በማዋ^ረድና በማንገላታት ስትጠመዱ፤ መንግስት ግን ሙስሊሙንም መስጂዱንም ከሸገር ሲቲ ጠርጎ በማስወጣት በምትኩ የኔ ሚላቸውን ጴንጤዎች አደላደለ። የእናንተ ጦሳችሁ ለእኛም ተረፈ።
እኩሎቻችሁ በዘ^ርና በጥቅም ተጠልፋችሁ ጭራሽ የመንግስት አጋር ሆናችሁ አረፋችሁት። ንቀ^ትንም አተረፋችሁ። ሲጀመር መንግስት እራሱ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ መጅሊሱ አምጥቷችሁ እንዴት አይና^ቃችሁ?! ዑለሞቻችንን ያዋረ^ዳችሁ ጊዜ እናንተም በመንግስት ሚዛን ላይ ይበልጥ ረከ^ሳችሁ።
መንግስት በሸገር ሲቲ በሙስሊሞች ሂሳብ የኔ ሚለውን የፕሮቴስታንት ኃይል ካደላደለና ዲሞግራፊውን ከቀየረ በኋላ፤ እናንተ ማለት በብዛትም ሆነ በክብደት ምንም እንደሆናችሁ ሊያሳያችሁ የወሰነ ይመስላል። ወደ መጅሊስ አዝሏችሁ እንድትገቡ ያደረገበት ፖለቲካዊ ሚሽናችሁም ሊያልቅና expire ሊያደርግ እየተቃረበ መሆኑን ሊያረጋግጥላችሁ መንግስት ለዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ቀጠሮ ይዟል።
የሸሂዶቹ ደም ይፋረዳችሁ!
Hamsa Hamsa
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM