#ተሶውፍ (ሱፍይነት) ክፍል3
በተሰውፍ ጎዳና ጦሪቃ_(ሱሉክ) አለ። በዚህ መንገድ በጉዞ ላይ ያለ አንድ ሰው "ሳሊክ" (ተጓዥ) ይባላል።
እንደ ሱፍዮች ማንኛውም ሰው በሀይማኖታዊ እውቀት ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ይችላል። ነገር ግን በሱፍይ መንገድ ለመራመድ ግን የሸይኽ ( #ሙርሺድ ) ምሪት ያስፈልጋል።
ሳሊኩ ከ ሙርሺዱ ልክ እርሱም ከተዘረጋው ከሸይኽና ሳሊክ ሰንሰለት የጉዞውን ጅማሮ ይቀበላል።
በዚህ ቅብብሎሽ ውስጥ ከነብዩ (ሰ.አ.ወ) የተመዘዘ በረካ አብሮ ይተላለፋል። እንደ ሱፊዮች እምነት ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ይህን በረካ የሰጡት እጅግ ውስን ለሆኑ ሶሃቦች በተለይም ለ አባበክር (ረ.አ) እና ለአልይ (ረ.አ) ሲሆን እነርሱም በተራቸው ለተከታዮቻቸው አስተላልፈዋል።
በዚህ መንገድ ቅብብሎሹ እስካሁን ጊዜ ደርሷል ለወደፊትም ይቀጥላል። ይህ የቅብብሎሽ መንገድ በአረብኛ ሲልሲላ ሲባል። ከመምህር ወደ ተማሪ የሚተላለፍ ህያው ትውፊት ነው።
ተማሪው ፈላጊ (ጣሊብ)፥ከዚያ ሳሊክ፥በመጨረሻ አሏህ ከተደሰተበት እና ከሻለት አሏህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ አሪፍ፥የበቃ ይሆናል።
ነገር ግን መንፈሳዊ እውቂያ ያለሸይኽ ወይም መንፈሳዊ መሪ አስጀማሪነት፥ምክር እና ምሪት ሊሳካ አይችልም።
የሱፊ መንገድ ለመከተል የሚሹ ወደ አንድ ሸይክ ይቀርቡና መንፈሳዊ ትስስር ሲልሲላ ይቀበላሉ፡፡ ይህ ትስስር እስከ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ድረስ ሳይበጠስ ወደኋላ ይተረተራል፡፡ ፈላጊው መርጦ ሊከተለው የሚችል በርካታ ሲልሲላዎች ሲኖሩ ሁሉም ግን ነቢዩ ራሳቸው ካስጀመሯቸው አንድ ወይም ሌላ ሶሃባ ላይ ያርፋል፡፡ በተሰውፍ የመጀመሪያ ዘመን ውስጥ የነበሩ ብዙ የሱፊ አለቆች ቢኖሩም ተቋማዊ ቅርፅ አልነበረውም፡፡ በአስራ አንደኛው እና አስራ ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር የመጀመሪያው የቃድሪይ ስርዓት ወይም ጠሪቃ በሸይክ አብዱልቃድር ጀላኒይ (1071-1166) የተመሠረተው።