(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከዚህ ቀደም በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን እንዲመሩ ዕጩ ሆነው ቀረቡ።
በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩትን አቶ ብርሃኑ አዴሎን፣ አሁን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ እጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጿል።
በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመን፣ አቶ ብርሃኑ እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ በወቅቱ ከተወለዱበት የደቡብ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በአቶ ብርሃኑ ላይ የተፈራረሙትን የቅሬታ አቤቱታ (ፔቲሽን) ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማስገባታቸውን በወቅቱ ተዘግቦ ነበር፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበባቸው ሪፖርት ከካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸውና ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉም አይዘነጋም፡፡
ከዚያም በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ከ10 ዓመት በፊት ሲመሩ የነበር ሲሆን ከዚያም ስልጣናቸው "በቀረበባቸው ቅሬታ" ተነስተው ነበር፡
አሁን አቶ ብርሃኑ አዴሉ፣ ስልጣናቸውን የለቀቁትን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነርን ተክተው እንዲመሩ እጩ ሆነው መቅረባቸው ታውቋል።
ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ብርሃኑ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ከሕንድ አገር የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።