"ርእሰ አንቀጽ"
"…ከትናንት ወዲያ በዕለተ ማክሰኞ ጠዋት በቴሌግራም፣ ምሽት በቲክቶክ፣ ትናንት ደግሞ በርእሰ አንቀጼ ላይ የጎጃም ፋኖን በተመለከተ የተጠራቀመ የሕዝብ ብሶትንና እሮሮን መነሻ ምክንያት በማድረግ ሓሳብና ትችት፣ ሸንቆጥም፣ ዠለጥም የሚያደርግ ሓሳብ ሳራምድ፣ መልእክት ሳስተላልፍ መዋል ማደሬ ይታወቃል። ያን የእኔን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን መተቸት ተከትሎ ቀላል የማይባል ቁጥር ባላቸው የዐማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ወዳጆች ዘንድ ድንጋጤ፣ መረበሽ፣ ስጋት መፈጠሩን አይቻለሁ። የስጋታቸው መነሻም የፋኖ አደረጃጀቱ በተሻለ ቁመና ላይ ስለሚገኝ እንደው ዘመዴ ዐሳብ ስታነሳ ችት ስታቀርብ ጠላት እንዳይጠቀምበት፣ በውስጥ ቢያልቅ ወዘተ የሚልና የፋኖ አደረጃጀት አሁናዊ ተቋማዊ ገጽታ ምን እንደሚመስል ካለማወቅ የመጣ ስጋት ያንጸባረቁ ነበሩ። ስጋታቸው ስለሚገባኝ፣ ክፋትም ስለሌለው እነሱን "አይዞኝ" ብሎ ማለፉ በቂ ነበር።
"…ሌሎች ደግሞ ለእኔ ቀን የሚጠብቁልኝ ተረፈ ብአዴኖች፣ ዐማራ መሳይ አሞሮች፣ በጎጃም የተሰገሰጉ ያልተገለጡ የፋኖ ወዳጅ መሳይ ብአዴኖች፣ ዐማራ ሆነው በሃይማኖቴ የሚጠሉኝ፣ ኦርቶዶክስ መሆኔ የሚያንገበግባቸው አንዳንዶች የወሃቢይ እስላምና የብልፅግና ወንጌል አማኝ ዐማሮች አንዳንዶቹ ደፍረው፣ ፈራ ተባ እያሉ ሲጽፉ፣ ሌሎች ደግሞ ፈራ ተባ እያሉ በእነዚህ ሰዎች የተጦመረውን ጦማር ሼር ሲያደርጉ ነበር የዋሉት። እጠቅሳለሁ። በብዕር አጣጣሉ፣ ባለማቋረጥ በሚሰጠው መረጃ፣ በአጫጭር ግን ግልጽ መልእክት በመጻፍ በሚታወቀው፣ በተለይም የእስልምናው አማኝ ዐማራወረ ፋኖን እንዲወድ፣ እንዲቀርብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲወጣ የከረመው እጅግ የማከብረው ዐማራው ብዕረኛ አቶ መሀመድ ሐሰን አንደኛው ነው። መሐመድ ሐሰን ትናንት ባቀረብኩት ሓሳብ ቢተቸኝ መልካም ነበር። ማሜ ግን እኔን ወስዶ ከእነ ሀብታሙ አያሌውና፣ ከእነ አበበ በለው ጋር አብሮ አጃምሎ ግልጽ ያልሆነ ትችት በማንፀባረቁ እኔን ራሴን ባስደነገጠኝ መልኩ ከወዳጅ ዘመዶቹ የትችት ናዳ ሲወርድበት፣ እርሱም ከድንጋጤ የተነሣ አንዳንድ ኮመንቶችን ሲደልት ለመዋል ተገዷል። በእውነት መሀመድ ሀሰን እንዲህ ያለ ወጣ ያለ ስድብ መሰደብ የሚገባው ዓይነት ሰው አይደለም። ከምር የማከብረው ዐማራ ነው። አንዳንዶች እንዳሉት የወሃቢይ እስልምናው ተጽዕኖ አድርጎበት እኔን ክርስቲያን ስለሆንኩም ነው ወስዶ ከእነ አበበ በላው ጋር የጀመለህ እንዳሉትም አይመስለኝም። ወሃቢይ ስለመሆኑም ማረጋገጫም የለኝም። እንዲያውም ፋኖነትን ከእስልምና ነጥለው በሌላ ጠርዝ ላይ ለቆሙ ለዐማራ እስላሞች ፋኖነት ዐማራነት እንጂ እስላም ክርስቲያን እንዳልሆነ ሲያሳይ፣ ሲያስረዳ የኖረ ወንድም ነው። ማሜ አዝናለሁ። ያነሣሁትን ዐሳብ ብቻ ብትተች ጥሩ ነበር። እናንተም ተቺዎች በአንደዜ እንዲህ ከመዘርጠጥ፣ አንሥቶ ከማፍረጥ ተቆጠቡ። ለማሜ የተሰጠውን ኮመንት ዓይቼ "ነግ በእኔ" ነው ያልኩት። በቃ አፉ በሉት።
"…ሌሎች ደግሞ አሉ። እነሱ ቢናገሩት ጠላት እንደሚበዛባቸው ዐውቀው፣ ፈርተው ሌላ ሰው የጻፈውን ፈልገው በገጻቸው ላይ ሼር አድርገው ጸሐፊውም እነርሱም ሲወቁ፣ ሲወቀጡ ውለው ያደሩ። የABC ጋዜጠኛዋ ውቃቢዋም፣ ቀልቧም ከድሮ፣ ከጥንት ጀምሮ የማይወደኝ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ የወይንሸት ሞላ እህት የምትመስለኝ መልካም ሰላም ሞላ የመሀመድ ሀሰንን ጦማር በገጿ ሼር አድርጋ፣ ዐሳቡን የምትገዛው መሆኑን በማወጇ የደረሰባትን ተቃውሞም አዓይቼ ለእሷም አዝኛለሁ። ይሄ የእሷ ዐሳብ እንጂ የABC የተቋሙ እንዳልሆነ ግን መገመት እችላለሁ። መልካም ከድሮ ፌስቡክ ላይ ሳለሁ ጀምሮ ቀልቧ፣ ውቃቢዋና ቆሌዋ አይወደኝም። አንድ ጊዜ ብቻ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ቀውጢ ተፈጥሮ ዝም ስል "ለዚህ ጊዜ ነበር እንደ ዘመድኩን ዓይነት ሰው የሚያስፈልገው" ብላ መጻፏን አስታውሳለሁ። ሆኖም ግን እሷም ቢሆን በራሷ ዐሳብ አልሞገተችኝም፣ በመሀመድ ሀሰን ላይ ተንጠላጥላ ነው ውርውር ያለችው።
"…ሌላው ከአርበኛ ዘመነ ካሤ ጋር አብሮ ፎቶ በመነሣቱ፣ አርበኛ ዘመነ ካሤን በተለየ እቀርበዋለሁ ብሎ ራሱን የሚያሻሽጠው የጎጃሙ ይኼነው የሸበሉ ነው። ይኼነው የሸበሉም ከድሮ ጀምሮ ቀልቡም፣ ውቃቢውም እንደማይወደኝ ዐውቃለሁ። እሱም እንደ መልካም የመሀመድ ሀሰንን ዐሳብ ነው የገዛው። እሱን ነው አምጥቶ በገጹ ያጋራው። ሆኖም ግን ይኼነውም ያልጠበቀው ግብረ መልስ ነው የገጠመው። አርበኛ ማንችሎትን ተችቶ ጽፎ እነ ተስፋዬ ለምነው ያስነሡትን ረስቶ አሁን የእኔን ሓሳብ ከአበበ በለውና ከሀብታሙ አያሌው ጋር ደምሮ መውቀጥ አግባብ አይደለም ነበር ያሉት ጎጃሞች። እሱ ይኼነው የሸበሉ ከአርበኛ ዘመነ ካሤ ጋር አብሮ የተነሣውን ፎቶ ስለለጠፈ እኔ ከዘመነ ካሤ ጋር የተነሣሁት ፎቶ ስለሌለኝ ዘመነ ካሤን አልቀርበውም ማለት እኮ አይደለም። እሱ ይኼነው ጎጃሜ ነኝ ስላለ እኔ የሐረርጌ ቆቱው ዘመዴ ለጎጃሞች ሩቅ ነኝ ማለትም አይደለም። ከይሄነው በላይ በምድር ያሉት ጎንደርም፣ ጎጃምም፣ ሸዋና ወሎም ያሉት የፋኖ አመራሮች ከሚገመተው በላይ ወዳጆቼ ናቸው። ለምሳሌ ፋኖ ማርሸት ፀሐዩን በግልጽ የተቸሁት እኔ ነኝ። ትችቴን ተከትሎ በእኔ ትችት ባይሆንም ማርሸት ወዲያው ነበር ከሁለት ሓላፊነቶች የተነሣው። ፋኖ ማርሸት ግን እስከአሁኗ ደቂቃና ሰከንድ ድረስ ያልተቋረጠ ወዳጄ ነው። መማር ደጉ ማለት ይኸነዜ ነው። ማርሸትን ለከፍተኛ ማዕረግ የምጠብቀውም ከዚህ ተነሥቼ ነው። ሓሳቤን ስሸጥ ሓሳቤን የሚገዛ ካገኘሁ የሌላው ነጋዴ መንፈራገጥ ከቅናት የዘለለ ሌላ ነገር የለውም። ይሄነው የሸበሉም ብዙም ባይወቀጥ ደስስ ይለኛል።
"…ሌላው መንቆረር ኢንሳይደር በሚባለው የፌስቡክ ፔጅ ሲያንጸባርቀው የዋለው ሓሳብ ነው። ከጎጃም ፋኖዎች መንደር ሲንጨረጨር ያየሁት ይሄንን ፔጅ ብቻ ነው። የፔጁ አስተዳዳሪ በፎቶው ላይ የምታዩት አቶ ጥጋቡ መኮንን ይባላል። ጥጌክስ በግል የማርሸት ጓደኛ ነው። በግል እኔ ከማርሸት ጋር ያወራነውን ዐሳብም በገጹ ላይ አስፍሮ አይቼዋለሁ። መረጃ ለዘመዴ የሚሰጡት ላይ እርምጃ እንወስዳለን ብሎም ሲፎገላ ነበር ያየሁት። ስምን መልአክ ያወጣዋል እንዲሉ አበው አቶ ጥጋቡም ከአሁኑ ምኑንም ሳይያዝ ጥጋብ ደረቱን ነፍቶት ከአሁኑ ደርግና ወያኔን አስንቆ እንደ ሳዳም፣ እንደ ጋዳፊ፣ እንደ ኤዲአሚን ዳዳ ወጠጤ አምባገነን ለመምሰል ሲፎገላ አይቼው ስስቅበት ነው ያመሸሁት። ይሄ የፋኖነት መገለጫ አይደለም። ነገር ግን ጥጌክስ ትተነፍሳለህ፣ ጥጋብህም ይበርዳል እንጂ እንደፎገላህ አትቀርም። ጥጌክስ ጥጋቡ ከጎጃም አልፎ ወሎና ሸዋ ውስጥ ባሉ ታጋዮች ጭምር ላይ ነው ሲፎገላ፣ ሲዝት የዋለው። እኔ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ደንቆሮ ሳገኝ ማገዶ ፈጅቼም ቢሆን ሊቅ ነው የማደርገው። ይሄን ፋኖ አሰዳቢ ጥጋበኛ ጎጃም አሰዳቢ ነውረኛ ሰገጤ ጊዜ ወስጄ አበርደዋለሁ። ሰከን አደርገዋለሁ። ጥጋቡ ጠግበህ ጠብቀኝማ።
"…ሌሎች ግን ገና እኔ በጎጃም ዐማራ ፋኖ ላይ የትችት፣ የተግሳጽ፣ የጭቃ ዥራፌን እመዛለሁ በማለት ቀጠሮ ሲያዝ ጮቤ ረግጠው፣ ፌሽታ በፌሽታ ሆነው፣ እየጨፈሩ አዋራ ሲያስነሱ የዋሉም ነበሩ። ስኳድ ጌትነት ይስማውና ሙላት አድኖ የፈራ ይመለስ በቃ የሴራ ቦለጢቃ ሠራን ብለው ብብታቸውም፣ ብሽሽታቸውንም እስኪያልባቸው ነበር የተወራጩት። ቁናስ በቁናስ ሲያደርጉን ነበር የዋሉት። እነሱ በሴራ ሚሳኤል፣ በሴራ ፈንጅ፣ በሴራ ቦንብ፣ በሴራ መድፍ፣ በስድብ፣ በሀሜት፣ በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣…👇①✍✍✍