👆④ ✍✍✍ …አልሞክርም። ወዳጄ ነው፣ ጓደኛዬ ነው ብሎ ነገር እኔጋር አይሠራም። እውነትን በውለታ አልለውጣትም። አልሸቅጣትም። በማኅበራዊ ሚዲያው እንዲከተለኝ እንጂ የምከተለው ሰው የለም። እንዲሰማኝ እንጂ የምሰማው ሰው የለም። እኔ በሱቄ የራሴን ምርት ነው የምሸጠው። ከከሰርኩ እኔ ልክሰር ማንም አያገባውም። በቶሎ እከብር ብዬ የሰው ጤና በሚጎዳ የሐሰት ንግድ ላይ አልሳተፋትም። እንዲህች ብዬ ሀብታም ሆኜ ለመታየት ለመገኘትም ስል በቅቤ ላይ ሙዝ፣ በበርበሬ ላይ ቀይ የሸክላ አፈር፣ በማር ላይ ስኳር፣ በጤፍ ላይ አሸዋ፣ በከሰል ጆንያ ላይ የኮረት ድንጋይ፣ በእንጀራ ላይ ጂፕሰም፣ የአህያና የውሻ፣ የጅብም ሥጋ የበግ፣ የፍየልና የበሬ ነው ብዬ አልሸጥም። ትርፍ እንደሌለው ባውቅም እውነትን ብቻ። እውነትን አልኩህ። ወይ ንቅንቅ።
"…ዘመዴ የእስክንድር ነጋን መንጋ ስለተጋፈጠ፣ ከግንቦቴ፣ ከባልደራስና ከግንባሩ ሰዎች ከደጋፊዎቻቸውም ጋር ስለተቧቀሰ። ሸዋ ገብቶ ከነመከታው፣ ወሎ ገብቶ ከነ ሙሀባው፣ ጎንደር ገብቶ ከስኳዱ፣ ወልቃይት ገብቶ ከኮሎኔሉ ጋር ስለተዋገረ፣ ከምህረተ አብ ደጋፊዎች፣ ከጃንደረባው ሄኖክ ደቀ መዛሙርቶች፣ ከቲክቶሎጂው ሊቅ ከግብጽ ቅጠረኛው ከአክሊል ወፈፌዎች ጋር ስለተነቋቆረ አይሳካለትም። አይሆንለትም። በተለይ አሁን ደግሞ ገንዘብ፣ አፍ፣ አክቲቪስትና ጋዜጠኛም ሚዲያም ካላቸው ከጎጃሞቹ ሸንጎዎች ጋር እየተፈሳፈሰ ስለሆነ ወፍ የለም ያሉ ነበሩ። አውነት አላቸው። አንድ እኔ ብቻዬን በአንዲት የእጅ ስልኬ ብቻ በሚጻፍ ጦማር የአረመኔው የኦሮሙማ አገዛዝ፣ የወዩና የብአዴን የኦነግም መንጋ ሳይጨመር ሁሉንም ድባቅ ስመታቸው ከመደነቅ፣ በፈጣሪ ሥራ ከመደመም ይልቅ በሰው ሰውኛ እያሰቡ ይሰጋሉ። ስለእኔም ይጨነቃሉ። አዪዪ ሲያልቅ አያምር አሁንስ ዘመዴ እገሌን ነካው፣ እነ እገሌን ተሳፈጠ አለቀለት ብለው ተስፋም ይቆርጣሉ። እኔ ግን የያዝኩት እውነት ዐውቀዋለሁ። አልሰጋም አልፈራምም። አውነት ማለት ቀራንዮ ላይ ተሰቅሎ፣ ወደ መቃብር ወርዶ፣ ድንጋዩን አንከባልሉልኝ፣ መግነዙን ፍቱልኝ ሳይል የታተመ መቃብር ፈንቅሎ ከፍቶ የተገለጠ፣ ሞት ቀብሮ የማያጠፋው እንደሆነ አይረዱም። እውነት ይሰቀላል፣ ይገደላል፣ መቃብር ይወርዳል። ነገር ግን በክብር ይነሣል። እውነት እግዚአብሔር ነው። እውነትን አግቡ፣ ውደዱ፣ አፍቅሩም፣ እንዳትፋቱም።
"…በዚህ መሃል ነው የዘመዴን ሚዲያ አየር ላይ ለማምጣት ወደ አደባባይ የወጣሁት። 32 ሺ መንጋ ይዤ አይደለም ለሰልፍ የወጣሁት። 22 ሺ ፈሪ፣ ድንጉጥ፣ አስመሳይ፣ በትዳሩ፣ በኑሮው አርቴፊሻል የሆነ ሜካፓም ሠልፈኞችን አይደለም ይዤ ለመገለጥ የፈለግኩት። ሰው ሰው ነው። እኔ አንድም ቀን ይለዩኛል ብዬ አስቤ የማላውቃቸው ሰዎች ጥርቅም አድርገውኝ ታዝቤአቸው ዐውቃለሁ። ይሄ የሚገጥም ነው። 10,700 የውሻ ጠባይ ያላቸው፣ የተፉትን የሚልሱ፣ ግብረ ገብ፣ ኤቲክስ የምትሉት ነገር የሌላቸውን ስግብግቦች ይዤ አይደለም ለሰልፍ የወጣሁት። እኔ የእውነት ወዳጆች፣ አፍቃሪዎች፣ ተመሳሳይ ላባና ክንፍ ያለንን ሰዎች ነው በባትሪ የፈለግኩት። ጥሪም ያቀረብኩት በአደባባይ ነው። በኃጢአት፣ በበደል ገንዘብ ያካበቱ ማጅራት መቺዎችን አይደለም የፈለግሁት። በላባቸው፣ በወዛቸው በሃቅ ጎዳና ላይ ላሉቱ ነው ጥሪ ያቀረብኩት። ሚዲያ ላቋቁም ነኝ ተከተሉኝ አልኩ። የምፈልገውንም የሰው ብዛት ተናገርኩ። በቃ የሰሙኝ ጥሪዬንም ሰምተው ወደ እኔ ጎረፉ። 300 ሠራዊተ ጌዴዎን ዘ ኢትዮጵያ አባላትን ምልመላ ጀመርኩ። አሁን 300 ልሞላ 18 ሰው ብቻ ነው የቀረኝ። እሱም ዛሬ ወደ ጎጃም ወደ ጮቄ ተራራዬ ከመመለሴ በፊት የሚሞላ ይመስለኛል።
"…የሚዲያ ፈቃዱን ያወጡት በሥላሴ ስም ሦስት፣ ሚዲያውን በቦርድ አባልነት ይመሩ ዘንድ የተመረጡት አምስት አእማድ የሆኑ ወንድም እህቶች ናቸው። የሳታላይት ቴሌቭዥኑን ከውልደቱ እስከ እድገቱ በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸውና በጎልበታቸው የሚያገለግሉት 300 ቋሚ፣ 3000 ሺ አጋር፣ አጋዥ ኢትዮጵያውያን በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። 300 ዎቹ ተመራጭ የጌዴዎን ሠራዊቶች ከፍ ሲል አንድ ሺ፣ ከዚያም በላይ፣ ዝቅ ሲል ደግሞ መቶና ሁለት መቶ 300 ም ዶላር ይዘው አዋጥተው የሳታላይት ቴሌቭዥኑን የዓመትና የሁለት ዓመት የአየር ላይ ቆይታውን በመክፈል አረጋግጠው ሥራ የሚያስጀምሩ ናቸው። አሁን የባንክ አካውንት፣ የዜልና የካሽአፕ ቁጥርም እየተዘጋጀ ነው። ሁሉም እንዳለቀ ይለጠፍላችኋል። ከ300 ዎቹ ውጪም ሚልዮኖች ይሳተፉበታል። እንደ እኔ ከእውነት ጋር ሙጭጭ ያሉ ሁሉ አብረውኝ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ሽር እልም ነው። ከአውቶቡሱ ላይ ከፌርማታው መውረድ ብሎ ነገር የለም። ከ300 ው የሚያፈነግጥ ሲገኝ ከተጠባባቂው እየተካን ወደፊት ነው አለቀ። አስገድጄ ያመጣሁት፣ ኪሱ ገብቼ የገፈፍኩት የለም። ወዶና ፈቅዶ ነው የመጣው አለቀ።
"…ሌላም ነገር ላንሣ። አንድ ድርጅት ለማቋቋም የምታዩትን መከራ አስታውሱ። ሰው ፍለጋ። ስብሰባ፣ አበል፣ ብድር ፍለጋ፣ የኢንቬስተር፣ የለጋሽ ባለሀብቶችን ቤት ለማንኳኳት መኳተኑ፣ የስልክ ወጪውን፣ የቢሮ ኪራዩንም ሁሉ አስታውሱ። እገሌን እንያዘው፣ እገሌን እናምጣው፣ አምባሳደር እናድርገው፣ ከዚያ ደግሞ ቲክቶከሮችን፣ የማስታወቂያ ሠራተኞችን ፍለጋ፣ በሰበር ዜና በቴሌቭዥን፣ በታዋቂ ጦማርያን "እገሌ ሚዲያ ሊመጣ ነው፣ እየመጣ ነው" ወከባው፣ ግርግሩን ሁሉ አስታውሱ፣ ከዚያ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም፣ በኢንስታግራም፣ በቲክቶክ፣ በቴሌቭዥንና ራዲዮ ሁሉ ሞዴላ ሞዴሎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች ምስክርነት ሰጥተውት፣ ዛር ወጥቶ ተንቀጥቅጦ ነው ሚዲያም ተቋም የሚመሰረተው። የዐማራ ማኅበራት፣ የትግሬና ማኅበራት ተለምነው፣ ደጅ ተጠንቶ ነው የሚመሠረተው። ጎፈንድሚው፣ ጨረታውን ሁሉ አስታውሱ። እኔ ጋ ግን ወፍ። ወፍ የለም አልኩህ።👇④ ✍✍✍