ረቡዕ፦ አልዓዛር ይባላል።
"…የማርታና የማርያም ወንድማቸው አልአዛር መሞቱን ተከትሎ ከተቀበረ ከ4 ቀን በኋላ ጌታ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መግነዝ ፍቱለት መቃብሩንም ክፈቱለት ሳያስብል እንዳስነሣው እያስበን የምናከብርበት ዕለት ነው። “…ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” ዮሐ 11፥25 የሚለውን ወርቃማ የትንሣኤ ትምህርት ያስተማረንም በዚሁ በአልአዛር መቃብር ላይ ቆሞ ነበር።
"…በእርግጥ አልአዛር የሞተው በዚህ ዕለት አልነበረም። አልአዛር የሞተው ከበዓለ ሆሣዕና በፊት በነበረው ረቡዕ ሲሆን አራተኛ ቀኑ የሚሆነው ቅዳሜ የሆሣዕና ዋዜማ ላይ ነበር። ጌታም ያስነሣው በዚሁ በዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 17 ቀን ነበር። በዚሁ ቀን መታሰቢያ እንዳያደርጉለት የግርግር ወራት ሆነ። በ22 ሆሳዕና ሆነ። በ23ም ርግመተ በለስ አንጽሖ ቤተ መቅደስ ሆነ፣ ደግማሞ የአልዓዛር ትንሣኤ ከሞት ወደ ሞት እንጂ ለሕይወት ያልሆነ፣ ከጊዜም በኋላ ተመልሶ የሚሞት ትንሣኤንም ጠባቂ ስለነበር በዚህ ምክንያት የትንሣኤው በኩር የክርስቶስ ትንሣኤ ካለፈ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር ሥርዓት ሠርተውልናል።
"…ለምሳሌ ጌታ የወይን ጠጁን ወደ ውኃ የቀየረው የካቲት 23 ነበር። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ግን ሥርዓት ሲሠሩልን የካቲት 23 በዐብይ ጾም የሚውል ሆነው ቢያገኙት በዚህ ዕለት ሀሴት፣ ደስታ ማድረግን ከልክለው የየካቲት 23ን የቃና ዘገሊላ በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተው ከበዓለ ጥምቀት በኋላ የውኃ በዓል ከውኃ ጋር ይከበር ይውል ዘንድ እንደወሰኑት ሁሉ የአልአዛርንም ትንሣኤ ከትንሣኤ ጋራ እንዲውል ነገር ግን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር አደረጉልን።
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።