👆③✍✍✍ …እነዚህን በግልጽ መታገል ይገባል። በፍልሰታ ደብረ ሊባኖስ፣ ደብረ ዳሞ ዋልድባ መሄድ ትቶ ወደ አውሮጳ አሜሪካ የሚሸሸውን መዋጋት ያስፈልጋል። በአሜሪካ ኑሮ ጳጳሱ መጡ ተብሎ ሴቶቹ ተራ ገብተው መቀለብ የለባቸውም። ይሄን የተራበ ጳጳስ በሌላ በምንም ወደመስመር ልታስገባው አትችልም።
"…በተመደቡበት ሀገረ ስብከት በራሳቸው ላይ በዘመዶቻቸው በኩል ተቃውሞ አስነሥተው አውሮጳና አሜሪካ ካልተመደብኩ የሚሉ እኮ ነፍ ናቸው። አዲስ አበባ ተቀምጠው ሀገረ ስብከታቸውን በሪሞት ኮንትሮል የሚያስተዳድሩ እኮ የትየለሌ ናቸው። ሀገረ ስብከታቸው ሄደው ጎብኝተውም የማያውቁም የትየለሌ ናቸው። መኖሪያቸውን አራት ኪሎ መንበረ ጵጵስና አድርገው የሀብታም ፍትፍት የሚያማርጡ እኮ ብዙ ናቸው። የተከፈተ አዲስ ሱቅ የሚመርቁ ጉደኞችን እኮ ነው እያየን ያለነው። ድህነትን ሸሽቶ የእነ ጸጋዬ ሮቶ ማዕድ ለመባረክ የጰጰሰን እንዴት አድርገህ ነው የድሆች አባት ሁን የምትለው? ድህነትን ለማሸነፍ ዋጋ ከፍሎ ሀብታም የሆነና ከሀብታሞቹ ጎራ ራሱን የመደበን አባት በምን ተአምር ነው የድሆች አባት የምታደርገው። ጭቅቅቱን፣ ቅጫሙን፣ አራግፎ በፈረንሳይ ሽቶ፣ በጣልያን ጫማ፣ በግሪክ ልብስ የተሽቆጠቆጠን ሊቀጳጳስ እንዴት አድርገህ ነው ተፈናቃዮችን፣ ስደተኞችን፣ ምስኪኖችን ጎብኝ፣ አባት ሆናቸው ብለህ የምትነዘንዘው? አይሰማህም። ከደሀ መቀነት ተፈትቶ በሚሰጥ ሙዳየ ምጽዋት ተንቀባርሮ እየኖረ ደሀን የሚጠየፍን አባት፣ ዘወትር በባለፀጋ ቤት ፀበል እየረጨ ደሀ ቤት ድርስ የማይልን፣ የምእመናንን እጅ የሚያይ ጳጳስ፣ ፈጣጣ ለማኝ የሚያስንቅ ስብእና የያዘን አስተዳደጉ ጫና የፈጠረበትን ምስኪን ምንአድርገህ ወደ መስመር ትመልሰዋለህ? ግርማ ወንድሙ፣ ሄኖክ ቅባቅዱሴ፣ ጆኒ ራጋም እኮ ጳጳሳት፣ ካህናቱን ጢባጢቤ የሚጫወቱባቸው አሳምረው ስለሚያውቋቸው ነው። ለገንዘብ ያላቸውን ፍቅር ስለሚያውቁ ነው የሚያዝረከርኳቸው። ጠቁር ራስን ግፋው ባለቆብን አስገባው የሚል የቆብ ዘረኛ ከባድ ነው። ፌደራል የተመደበለትን ጳጳስ ስለ መላእክት ጠባቂነት እንዲሰብክ መጠበቅ የዋሕነት ነው።
"…ወደ አባ ገብርኤል እንመለስ። ኦሮሞው አቡነ ገብርኤል ዐማሮቹን የጎንደር ተወላጅ ሊቃነጳጳሳት አቡነ ዮሴፍንና አቡነ በርናባስ ወይም በቀድሞ ስማቸው አባ ወልደ ትንሣኤን አስቀምጠው ነው ምንፍቅናቸውን የዘሩት። አሁን ግን የማየው ነገር ደስ አይልም። ለአቡነ ገብርኤል ምላሽ እየሰጡ ያሉት ሊቃውንት በሙሉ ትኩረታቸው ኦሮሞው ሰውዬ ላይ ብቻ ነው። የመናፍቅ ቆንጆ የለም። መናፍቅ መናፍቅ ነው። አባ ወልደ ትንሳኤን እየዘለልክ አባ ገብርኤል ላይ መደንፋት ልክ አይደለም። ኦሮሞዎቹም እየጠየቁ ነው። አባ ገብርኤል ከተሳሳቱ ልክ እንደ አባ ገብርኤል ያስተማሩት አባ ወልደ ትንሣኤም መጠየቅ አለባቸው እያሉ ነው። በኦርቶዶክስ ዘር የለም። ጎንደሬም፣ የሰላሌ ኦሮሞም ከመነፈቀ መነፈቀ ነው። ጎንደሬዎቹን ለይቶ ኦሮሞዎቹ ላይ መጮህ ልክ አይደለም። እኔ ሁለቱንም ነው የምቃወመው። የምለየው የለም። አይደለም ሁለቱን ሦስተኛውን የትግሬ መናፍቅ አባ ሰረቀንም ለይቼ አላየውም። ሚዛናችን ይስተካከል።
"…ወደ መጨረሻው ጦማሬ ስመጣ የዲያቆን ኃይሌ ጉዳይ ነው። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌም በመጨረሻ ጊዜ፣ በመጨረሻው ሰዓት ላይ አቡነ ገብርኤል ላይ አደገኛ የተባለ ከባድ ሰይፉን አንሥቶ ታይቷል። የሄኖክ ኃይሌን የትናንቱን ጦማር ባደንቅም እኔ ግን በሄኖክ ኃይሌም ላይ ያለኝ ጥያቄ አልተነሣም። ሄኖክ ለእኔ ዘመናዊ አፈ ጮሌ የሃይማኖት ነጋዴ ነው። ሄኖክ ኃይሌ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ መዋቅሩ ውስጥ ሳይኖር ከሮም ካቶሊክ ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ የፈጸመ ሰው ነው። ሄኖክ ኃይሌ በግልጽ በአደባባይ ወጣቶችን አደረጃቶ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ያስገደ፣ ያዋረደ ሰው ነው። ዘረኛ እወደድ ባይ፣ አፍቃሬ ትግሬ ፀረ ዐማራ የሆነ ሰው ነው። ለትግራይ ጦርነት ብዕሩን ያነሣ፣ የተቃወመ፣ ለዐማራው ፍጅት ራሱን የደበቀ ሐዋርያ ለመምሰል በማስታወቂያ ብዛት፣ በዩቲዩበሮች ቤት በመንጦልጦል የራሱን የስብእና ካፒታል ለመገንባት የሚላላጥ ሰው ነው። በሄኖክ ኃይሌ ላይ ያለኝ ጥያቄ እስከአሁን አልተነሣም። በየትኛውም ጊዜ ለተነሡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ የመከላለል ምላሽ ያልሰጠ ሰውዬ አሁን ምሳር የበዛበትን አቡነ ገብርኤል የተባለ ጳጳስ መውደቁን ሲያረጋግጥ አድቫንቴጅ ለመምታት ሲላላጥ ነው ያየሁት። የትግራይ መነኮሳት ቤተ ክርስቲያንን ገንጥለው ሲለፋደዱ እያየ እሱ የአዲስ አበባ ትግሬዎችን ሰብስቦ አብሮ ቢዝነስ እየሠራ ጮጋ ብሎ አንድ በግልጽ የሳተን የኦሮሞ ጳጳስ እንዲህ ጠንከር አድርጎ ስለተቃወመ አይደንቀኝም። አይገርመኝም። ተቃውሞውን ግን አልንቅም። አከብርለታለሁም።
"…ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ የጻፈውን የተቃውሞ መልእክት ሳይ እኔ ራሴ የጻፍኩት እስኪመስለኝ ነው የተደነቅኩት። እባጭ፣ ማድያታም፣ ከነንፍጡ፣ ምናምን ብሎ ሲጨርስ አሸበርቲው ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ ብሎ የቋጨው ሁላ ነበር የመሰለኝ። ዘመድኩን ተሳዳቢ ነው። ዘመድኩን ኃይለ ቃል ይናገራል ሲሉኝ የከረሙ ሁላ ናቸው ሼር ሲያደርጉለት የዋሉት። ድፍረቱ የሌለ ገራሚ ነው። የጦማሩን ኤዲት ሂስትሪ ስቆጥር አብዝቶ መጨነቁንም ነው ያየሁበት። እስቲ ሄኖኬ የተጠቀማቸውን ቃላት እንመልከት። ይሄንን ድፍረት በእነ አኬም ላይ ያነሣ ይሆን? በእነ ወልደ ትንሣኤና በእነ አባ ሠረቀ ብርሃንም ላይ ያነሣ ይሆን? ለማንኛውም እንቁጠር።
፩፦ ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር።
፪፦ ጌታ በወንጌል"ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል።
፫፦ በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደሀ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል።
፬፦ ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን።
፭፦ ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር።
፮ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን። አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ፣ (አቡነ ጴጥሮስ) በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ (አቡነ ጴጥሮስ) ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው (አቡነ በርናባስ)
፯፦ ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች (እነ አኬ፣ ራሱ ሄኖኬ) ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ።
፰፦ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል።
፱፦ በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው። ቤተ ክርስቲያን መናፍቃንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም።…👇③✍✍✍