ሳዑዲ የፊታችን እሁድ በሚከፈቱ ከ90 ሺ በላይ መስጊዶቿ ጸረ ኮሮና መድኃኒት ርጭት አደረገች‼️
ሳዑዲ አረቢያ ከ90 ሺ በሚልቁ መስጊዶቿ የጸረ ኮሮና መድኃኒት ርጭት ማድረጓን የሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ ሪያድ ርጭቱን ያደረችው መስጊዶቹን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡ ከነገ በስቲያ እሁድ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑም የሃገሪቱ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሆኖም በመካ የሚገኙ መስጊዶች ሚኒስትሩ አብዱላቲፍ አል-ሼክ ተጨማሪ ፍቃድ እስከሚሰጡ ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ፡፡
ስለ ወረርሽኙ መከላከያ የጥንቃቄ መንገዶች ግንዛቤን ለመፍጠር ሰፊ ዘመቻዎችን የጀመረችው ሳዑዲ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት በሚል ጥላቸው የነበሩ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እገዳዎችንና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ማቅለል ጀምራለች፡፡ የሃገር ውስጥ በረራዎች የፊታችን እሁድ ይጀመራሉም ተብሏል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በሳዑዲ በአጠቃላይ 80 ሺ 185 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 54 ሺ 553 አገግመዋል፤ 441 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡ ዘገባው የአልአይን ነው።
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa