Aß Mustefa


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ለማንም ስል ያልጀመርኩትን መንገድ ለማንም ስል አላቆምም ።
©ABDURAHIMAN
Amuwa Production😎

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


#ደስ_የሚል_ዜና
90 በመቶ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ከመያዝ ታድጓል የተባለው ክትባት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሁለት ኩባንያዎች ይፋ የተደረገው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት 90 በመቶ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ከመያዝ ታድጓል ተብሏል፡፡

ክትባቱን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮንቴክ ሲሆን ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ አበርክቶ ነው ብለዋል፡፡

ኩባንያዎች ክትባቱን በስድስት የተለያዩ ሃገራት በ43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሃገራቱ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቱርክ መሆናቸው ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

በሙከራውም በሰዎች ላይ እስካሁን አሳሳቢ የጤና ችግር ያለመታየቱን ነው ባለሙያዎቹ ያነሱት፡፡

ኩባንያዎቹ ክትባቱን በህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን የአሁኑ ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካው ኩባንያ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ እንደሚያቀርብ የገለፀ ሲሆን በ2021 ደግሞ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን እንደሚያመርት ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

@Ab_Mustefa


ይህ ከታች የምታዩት የመስጂደል ሐረም በመካ የሚገኘው መስጂድና የአካባቢው ምስል ሲሆን ወጥ ከሆነ እንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ነው ለቦታው ያለህ ፍቅር ሲጨምር ሲንር እንዲህ ለፈጠራ ያነሳሳኻል።
እንደምታዩት የእውነት ይመስላል ኢስላሚክ አርክቴክቸርና ዲዛይን ለዛሬው የስነ ህንፃ ዲዛይን ዕድገት ትልቁን ድርሻ አበርክቷል።

@Ab_Mustefa


My Birthday😎
የሁለት ምስሎች ገፅታ።
ካለማወቅ እስከማወቅ ከማጥፋት እስከ ማልማት የእድሜ እንደ አየር የመጓዝ ፍጥነት እስካሁኗ እድሜዬ ድረስ በሁሉም ሂደት ውስጥ አላህ እንድኖር ፈቅዶልኝ አሁን ላይ ደርሻለው።
/አልሃምዱሊላሂ አላ ኩለ ኒዓም/

ብዙ ማለት ባልፈልግም ከአምናው ዘንድሮ የተሻለ ቦታ ላይ እንዳለው አምናለው።

የአመቱ መጨረሻ ላይ ብዙ ነገሮች ተከስተው አስተምረውኛል። ስላለፈው አልፀፀትም ምክንያቱም ሳላውቅ ነውና
እድሜ ትምህርት ቤት ነው እኔም በዚያ ሂደት እያለፍኩ ስለሆነ አልሃምዱሊላህ።

ሁላቹንም ወዳችዋለው አከብራቹሃለው እንደ ሰው ለሚያስብ ሁሉ አላህ የሚፈልገውን ይሰጠው ዘንድ ምኞቴ ነው።

©ABDURAHIMAN MUSTEFA
©September 26
© Nazareth Ethiopia

@Ab_Mustefa


ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር ነው!

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ስነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማህበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል፡፡

በስነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል፡፡

Via Al Ain News/Elias Meseret
@Ab_Mustefa


በስልክ ቁጥራችሁ ሊፈጸም ከሚችል ወንጀሎች ተጠንቀቁ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አሳሰበ!

በተጠናቀቀው የበጀት አመትም በ130 ሺህ የኩባንያው ደንበኞች የመስመር ስልክ ላይ የማጭበርበር ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ኢትዮቴሌኮም አስታውቋል፡፡

በተጠቀሰው የማጭበርበር ወንጀል የተነሳ ደንበኞች ለአንግልትና ለወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት እየተዳረጉ መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ኩባንያውም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጸዋል።

የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል መከላከል እንዲቻል ደንበኞች በተለያየ አጋጣሚ የሞባይል ስልካቸው በሚጠፋበት ወቅት በአቅሪያባቸው በሚገኙ የሽያጭ ማዕከላት በማሳወቅና የስልክ መስመራቸውን በማዘጋት ምትክ ሲም ካርድ መውስድ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ደንበኞች የስልክ መስመራቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ባለመስጠትና ለወንጀለኞች ተባባሪ ባለመሆን በስልክ መስመራቸው አማካኝነት ከሚፈጸም ወንጀል እንዲጠነቀቁ ማሳሰባቸውን አስታውቀዋል፡፡

@Ab_Mustefa


ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለ100 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ!

ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን 20 ሚለየን ብር በጀት የያዘለትንና በ7 ኢንድስትሪ ፓርኮች ውስጥ አንድ መቶ ሺ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ እንዲሁም ሙሉ የመረጃ ሲስተም ለመዘርጋት የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በትላንትናው ዕለት ተፈራርሟል፡፡

በፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች 100 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ያሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ያሉትን የስራ እድሎች፣ ጥቅሞቹን፣ ለስራው ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ምን እንደሆነና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያገኙበት ሲስተም በመዘርጋት የመረጃ ችግሩን ለመቅረፍ ያስችላል ተብሏል፡፡

ፋውንዴሽኑ ድጋፍ የሚደርግባቸው ኢንድስትሪ ፓርኮችም በአዳማ፣ ድሬደዋ ፣ባህርዳር፣ ደብረ ብርሀን፣ሀዋሳ፣ መቀሌ እና ኮምቦልቻ የሚገኙት ሲሆኑ በቀጣይ 3 ኢንድስትሪ ፓርኮች ላይም ድጋፍ እንደሚደርግ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@Ab_Mustefa


አንዲት አንገቷ ላይ መስቀል ያረገች ሴት ታላቁን የአላህን የተከበረውን ቁርዓን ስትረግጥ እና ስትገነጣጥል ሁሉም ይሳደብና ያልፋታል።አንዱ ግን በብሄሩ ምክንያት ሲገደል አክራሪ ሙስሊም ገደለው ተብሎ ታርጋ ይለጠፋል።
አርሲ ላይ ከ100 65% ሻሸመኔ ላይ ደሞ ከ100 58% ንብረት የወደመው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው ማሀበረቅዱሳኑ ግን ክርስቲያኖችን ለይቶ ለማጥቃት ሙስሊሞች ነው ጥቃቱን ያደረሱት ብሎ ፕሮፖጋንዳ ይሰራልሃል።
በሞጣው የሽብር ጥቃት ላይ ያ ሁሉ ንብረት ሲወድም ጥቃቱ እንዲፈፀምም በሚዲያ ሲያነሳሱ የነበሩት ሰዎች ምን ተባሉ?!🤨
እሱስ ይሁን መስጊዱን አቃጥለው የቤተክርስቲያን መዝሙር ሲዘምሩ የነበሩትስ አክራሪ ክርስቲያኖች ማን አላቸው?!።
ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ውጪ ያለው ሲጎዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ተጎዳ ይሉሃል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሲገደልና ንብረት ሲወድምበት ግን🤔🤔
አንድም ሚዲያ አክራሪ ክርስቲያን አይልም! እዚጋ ክላሽ አላረገም😊

አንተን በደበረህ ቁጥር እስልምናዬን ላንተ ፖለቲካ ማራመጃ ልታረገው አትችልም።
ዛሬም ነገም ከከነጎዲያም እስልምናዬን በማንም የፖለቲካ ዲስኩር ልታጠለሸው አትችልም።
እኔ ስወለድ እማቀው ኢትዮጲያዊ ሙስሊም መሆኔን ነው። ኢትዮጲያዊ ሙስሊም ሆኜ ነው መኖርም መሞትም ምፈልገው። ያንተን የተግማማውን ፖለቲካ እዛው

©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


በነቢዩ (ዐሰወ) ዘመን አንዲት በጌጣጌጥ የተሸለመች ሴት በመንገድ ስትሄድ አይሁዳዊ ያገኛትና ለወርቋ ሲል ጭንቅላቷን በድንጋይ መትቶ ገደላት። ነቢዩም (ዐሰወ) የሴቲቱ ነፍስ ልትወጣ ስትቃረብ ደረሱባትና ማን እንደመታት ይጠይቋት ጀመር። «እገሌ ነው?» አሏት። «አይደለም» በማለት በምልክት ነገረቻቸው። ሌላም ሰው ጠሩ። «አይደለም» አለች። በመጨረሻ የአይሁዳዊውን ስም ጠሩላት። «አወ!» አለቻቸው። ከዚያም ነፍሷ ወጣች።

ነቢዩም (ዐሰወ) አይሁዳዊውን አስመጥተው ጥያቄዎችን ጠየቁት። እሱም ወንጀሉን መፈፀሙን ተናዘዘ። ከዚያም ሴቲቱን በገደላት መልኩ እንዲገደል አዘዙ። በድንጋይ ተወግሮም ተገደለ።
(አንነሳዒ 4742)

የሴቶች መብት ነቢዩ (ዐሰወ) ከሄዱበት መንገድ ውጭ ሊከበር አይችልም።

@Ab_Mustefa


🔵 ሰላተል ኩሱፍ ( የፀሀይ ግርዶሽ ሰላት )

🔵 ፀሀይ በጨረቃ ግርዶሽነት ምክንያት ብርሀኗ ከመሬት ሲጋረድ የሚሰገደው ሱና የሆነው ሰላት (ሰላት ኩሱፍ) (صلاة الكسوف) ይባላል ። ጨረቃ ደሞ በመሬት አማካኝነት ስትጋረድ የሚሰገደው ሰላት (ሰላተል ኹሱፍ) (صلاة الخسوف ) ይባላል።

🔵 የፀሀይ ኩሱፍ ሰላት በሸሪዐ የተደነገገው በሁለተኛው አመተ ሂጅራ ሲሆን ፤ የጨረቃ ኹሱፍ ሰላት ደሞ በአምስተኛው አመተ ሂጅራ ነው። (ሁለቱም ሰላቶች ሱና ናቸው ለወንድም ለሴትም ። በጀመዐ መስገዱ የተወደደ ቢሆንም ለብቻም መስገድ ይቻላል። )

🔵 አሰጋገዱ
ሁለት አይነት አሰጋገድ አለው

1️⃣ አንደኛው - ሁለት ረክዐ እንደማንኛው ረክዐተይን ሰላት ። ኡሰሊ ሱነተ ሰላተል ኩሱፍ ብሎ መስገድ ይቻላል።

2️⃣ ሁለተኛው - በሁለት ቂያምና በሁለት ሩኩዕ ይሰገዳል ።
- ነይቶ በተክቢር ወደ ሰላት ይገባል። መክፈቻ ዱዐውን ይላል
- ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ረጅም ሱራ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል፤ ረበና ለከል ሀምድ ብሎ ዱዐውን ይላል
- ከዛ ድጋሚ ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ከመጀመርያው ሱራ አነስ ያለ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል
- ረበና ለከል ሀምድ ብሎ የኢዕቲዳል ዱዐ ይላል
- ሱጁድ ይወርዳል ፤ ይነሳል፤ ሁለተኛ ሱጁድ ያደርጋል
- ከዛ ተነስቶ ሁለተኛውንም ረክዐ በእንደዚህ አይነት ይጨርሳል።

🔵 በሁለተኛው አሰጋገድ ላይ አምልጦት የመጣ ረክዐዋን ለማግኘት የመጀመርያዋን ሩኩዕ ማግኘት አለበት ። ከአንዱ ረክዐ የመጀመርያው ሩኩዕ ያመለጠው ረክዐው አምልጦታል።

🔵 ከሰላት ቡሀላ እንደ ጁምዐ አይነት ሁለት ኹጥባ ማድረግ ይወደዳል።

🔵 የሰላቱ ግዜ የሚወጣው .. የፀሀዩ ግርዶሽ ሙሉ በሙሉ ሲወገድ ወይም ደሞ ምሽት ደርሶ ፀሀይዋ ስትጠልቅ ነው
የጨረቃውም ግርዶሹ ሙሉ ለሙሉ ከተወገደ ወይም ደሞ ነግቶ ፀሀይ ከወጣች ጊዜው ይወጣል።

🔵 ሰይዳችን ሰ.ዐ.ወ. ከስር የተጠቀሰው ሀዲሳቸው ላይ : '' ፀሀይና ጨረቃ ሁለቱ ከአላህ ተዐምራቶች ውስጥ ናቸው። ለማንም መሞት ወይም መኖር አይደለም የሚጋረዱት። ይሀንን ካያቹ ወደ ሰላት ሽሹ '' ብለዋል።

عن عائشة زوج النبي صلى الله عليه وسلم قالت : خسفت الشمس في حياة رسول الله صلى الله عليه وسلم فخرج رسول الله صلى الله عليه وسلم إلى المسجد فقام وكبر وصف الناس وراءه فاقترأ رسول الله صلى الله عليه وسلم قراءة طويلة ثم كبر فركع ركوعا طويلا ثم رفع رأسه فقال سمع الله لمن حمده ربنا ولك الحمد ثم قام فاقترأ قراءة طويلة هي أدنى من القراءة الأولى ثم كبر فركع ركوعا طويلا هو أدنى من الركوع الأول ثم قال سمع الله لمن حمده ربنا ولك الحمد ثم سجد ثم فعل في الركعة الأخرى مثل ذلك حتى استكمل أربع ركعات وأربع سجدات وانجلت الشمس قبل أن ينصرف ثم قام فخطب الناس فأثنى على الله بما هو أهله ثم قال إن الشمس والقمر آيتان من آيات الله لا يخسفان لموت أحد ولا لحياته فإذا رأيتموها فافزعوا للصلاة }

رواه مسلم

@elmeewa
@Ab_Mustefa


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የኡጋንዳው ዘመድኩን በቀለ
መጽሀፍ ቅዱስ ነብይ አይልም ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ለገላጋይ ሲያቸግር ከቆዬ ቡሃላ በስተመጨረሻም ገልጠን ስናየው በሀፍረት እንዲህ ኩምትር ብሎ በአደባባይ ተዋርዷል፡
ወዳጄ ! ሊከራከርህ የመጣን ኡስታዝ ካየህ አለሁ አለሁ መጣሁ መጣሁ እያልክ በጓዳ በኩል ቶሎ ወተህ ንካው አምልጥ አለ ዘመዴ!

አቦ ፏ ያለ ጁመዓ❤❤❤
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ይህ መልእክት በስፋት ቴሌግራም ላይ እየተሰራጨ ነው!‼️⬆️

መልእክቱን የከፈቱ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ሙሉ ለሙሉ ዶክመንቶችን ከቴሌግራም ላይ ያጠፋል። ለሰው አይላኩት፣ እርስዎም አይክፈቱት።

©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


• ህፃናት ልጆቻችሁን በተለይ ሴቶችን ልታስተምሯቸው የሚገቡ ነጥቦች፡ (ለሌሎች ወላጆችም # Share አድርጉ)

ህፃናት ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም እየተደፈሩ ያለበት አስቀያሚ የአኺሩ ዘመን የመጨረሻው ግዜ ላይ ነን። እንደ ቀልድ ችላ የምትሏቸው ልታስጠነቅቋቸው የሚገቡ ነጥቦችን ልብ በሉ፡

1: ሴት ህፃናት ልጆቻችሁን የማንም ታፋ ላይ እንዳይቀመጡ ተቆጧቸው (አጎትም ይሁን የማንኛውም ዘመድ ታፋ ላይ እንዳይቀመጡ አስጠንቅቋቸው

2: ልጆቻችሁ 2 ዓመት ከሞላቸው ቡኃላ ልብሳችሁን በነሱ ፊት አትቀይሩ

3: በሰፈር በጎረቤት ወይም በዘመድ ማንም ሰው ልጆቻችሁን
# ባሌ ወይም # ሚስቴ ወይም የእገሌ ባል የእገሌ ሚስት እያለ እንዳይቀልድ አድርጉ

4: ልጆቻችሁ ለጨዋታ ሲወጡ ከማን ጋር እንደሚጫወቱ በሚገባ እወቁ እድሚያቸው ትንሽ ከፍ ያሉ ጎረምሶችና ኮረዶች ወደ ወሲብ የሚገፋፉ ጨዋታዎችን ከትምህርት ቤት ለምደው ስለሚመጡ ምን እንደሚያጫውቷቸው ማወቅ አለባችሁ

5: ለጉርምስና የደረሱ ልጆቻችሁን ስለ ወሲብ ምንነት በትክክለኛው መንገድ አስተምሯቸው። እናንተ በትክክለኛው መንገድ ካላስተማራችኋቸው ማህበረሰቡ በተሳሳተ መንገድ ያስተምራቸዋል

6: የሚመለከቷቸውን የካርቶን ፊልሞች ይዘት አስቀድማችሁ ተመልከቱ። በተለይ አሁን ላይ የሚሰሩ የአኒሜሽን ፊልሞች ለአዋቂዎች የሚሰሩ (የወሲብ ቃላትን ልቅ የሆኑ ንግግሮችን በግልፅ የሚያስተላልፉ) ናቸው

7: ዕድሚያቸው ከ3 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆችን የመፀዳጃ አካላታቸውን ራሳቸው እንዲያጥቡ ካካም ሲሉ ራሳቸው እንዲጠርጉ አስተምሯቸው። ከእነሱ ውጭ ማንም የቅርብ ሰው ይሄንን እንዳያደርግ አስጠንቅቋቸው ይሄ እናንተንም ይጨምራል በደንብ አስተምራችኋቸው በራሳቸው እንዲጠናቀቁ አስተምሯቸው

8: በቤት ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞችና ድራማዎችን ይዘት በጥንቃቄ አስተውሉ። ስለፍቅር እና ስለተቃራኒ ፆታዎች በግልፅ የሚወራባቸውን ፕሮግራሞች በፍፁም አትክፈቱ። በተለይ በአሁን ሰዓት የሚወጡ ዘፈኖች፣ ድራማዎችና ፊልሞች በጠቅላላ ያለ ጥናት የሚወጡ ልጆችን የሚያበላሹ ናቸው በተለይ የአማርኛ ፊልሞች መንገድ ከሳቱ ቆይተዋል።

9: ልጆቻችሁ በቤተሰባችሁ በብዛት ስለሚመጡ የቅርብ ሰዎች የሚነግሯችሁን ሳትንቁ አዳምጧቸው።

10: የማንንም ሞባይል ለጌም እንዳይጠይቁ አድርጓቸው። ነውር እንደሆነ አስተምሯቸው።

11: ያለ ዕድሚያቸው በፍፁም ስልክ አትስጧቸው። ከተጫወቱም በእናንተ በወላጆቻቸው ስልክ ብቻ እንዲጠቀሙ አድርጉ።

12: የሚጫወቷቸውን የቪዲዮ ጌሞችም በደንብ አስተውሉ እንደ አኒሜሽን ፊልሞች በካርቶን የተሰሩ ልቅ ለህፃናት የማይሆኑ ጌሞችን በኮምፒውተርም በስልክም በታብሌትም እንዳይጠቀሙ አጥፉባቸው። እንደነ ቫይሲቲ ያሉ ጌሞችን የኢትዮጵያ ህፃናት በስፋት ይጫወታሉ ይሄ መሆን የለበትም።

13: በስልኮቻችሁ ከትዳር አጋራችሁ ጋር የተነሳችኋቸውን የግል ፎቶዎች ልጆቻችሁ በፍፁም ማየት የለባቸውም።

14: ሴቶች ልጆች ራሳቸውን የሚያጋልጡ ልብሶች ቤት ውስጥም ቢሆን እንዳያስለምዱ ማስተማር ከተቻለ ከልጅነታቸው ሂጃብንም እንግዳ ሲመጣ እንዲለብሱ ማስተማር


ከነዚህ ውጭ ሌሎች ችላ የምትሏቸውን ነገሮች ትኩረት ሰጥታችሁ ልጆቻችሁን በሚገባ እና በስርዓት ማሳደግ ኃላፊነታችሁ በመሆኑ ለሰከንድም መዘናጋት የለባችሁም።


በተረፈው ዱዓ አድርጉላቸው።

©አይስክሬሙ እንዳጠናቀረው
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ሰይዲ አል ዐሊም አል ሉገዊይ አል ሙፈሲር ሸይኽ አህመድ አብዱላሂ አላህ ደረጃቸውን ከፍ አድርጎ ሁሌም ከሚያወሱዋቸውና ከሚያወድሷቸው አካቢሮች አንቢያ አውሊያና ሳሊሂኖች ጋር አንድ ላይ ፊታቸውን ጀነት ውስጥ ያሳየን 😔😔ኡለማዎች እየሄዱ ነው በላውም እየተከታተለብን ነው።😢😢
ነይተን ፋቲሀ እንቅራላቸው


©HAKUMI
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ኩሉ ቢዳዓቲን ዶላላ ምን ማለት ነው
አንዳንድ ካለ ዒልም ለተመቻቸው አጀንዳ ብቻ ፈትዋ እንደሚሰጡት ሰዎች ነው?!
የቢድዐው ስለት ከሲራጥ ሲቀጥን

ክፍል ሁለት
====================

ለማጠቃለል ያክል...ኢማሙ ሻፍኢይ፣ ኢማሙ ነወዊህ፣ ኢማሙ ቀራፊ፣ ኢማሙ ዙርቃኒ፣ ኢብን አቢዲን፣ ኢማሙ ኢብን ጀውዚ እና ኢማሙኢብኑ ሐዘም ለቢድዐ የሰጡት ትርጉም ወካይ በሆነ መንገድ ኢማም አልኢዝ ኢብኑ አብዱሰላም 'ቀዋኢዱል አህካም' ላይ እንዲህ ያስቀምጡታል
"ቢድዐ በነብዩ ዘመን ያልነበሩና ያልተለመዱ ተግባራትን ሁሉ ይወክላል። ግዴታ/ዋጂብ የሆነ ቢድዐ (ነህው መማርን የመሰለ)፣ የሚወደድ ቢድዐ (ተራዊህን የመሰለ)፣ የሚፈቀድ ቢድዐ (በአለባበስ እጅግ መጠንቀቅን የመሰለ)፣ የሚጠላ ቢድዐ (መስጂድን በጣም ማሽቆጥቆጥን የመሰለ) እና የሚከለከል ቢድዐ (ቀደሪያ፣ ጀበሪያ፣ ኻዋሪጅና መሰል አንጃዎች) ተብሎ ለአምስት ይከፈላል።
እናም ወንድሜ ....የቢድዐን ስለት ያለልክ ሞርደህ ከሲራጥ ስታቀጥነው....ቴክኖሎጂ ሀሉ ፈጠራ ነውና በጨለማ እራቱን የሚበላ፣ በፈረስ የሚጓጓዝ ፣ በሙበሊግ ምንጣፍ እና ማይክ አልባ መስጂድ ውስጥ የሚሰግድ፣ ጅንስና እስኒከር የማይለብስ...የከተማ መናኝ ትሆናለህ። ግድየለም ልሁን ካልክ መብትህ ነው።ይመችህ!......እኔን ግን "ቢድዐ!ቢድዐ!" እያልክ አታዝገኝ...የቢድዐ አረዳዴ ካንተ ቢለይም የእውቀት መልክዐ ምድሬን (Epistomological Landscape) ከሲዲ በተገኘ ስፒል ሳይሆን...[አለም ነጅዐሊል አርደ ሚሃዳ ፤ ወልጂባለ አውታዳ] እንዳለው በተራሮቹ በእነ ኢማሙ ሻፍኢይ እና ኢማሙ ነወዊህ...ነው እንዳያረገርግ ችካሉ የተመታው...መቼም ያንተ ጀበል ከነዚህ ተራሮች አንፃር ብጉር ነውና ተፋታኝ....ቢድዓቱል ሰይዐ (መጥፎ ቢድዐ) ስሰራ እንጂ ቢድዓቱል ሀሰና (መልካም ቢድዐ) ስሰራ "ኩሉ ቢድዐ! ኩሉ ቢድዐ" እያልክ አትጨቅጭቀኝ....[ለማንኛውም ሲሉ ሰምተህ...'ቢድዐ' ለማለት 'ቢዳዋ' ብለህ ቢድዐ የሆነ ቃል የተናገርከው ልጅ ግን ደህና ነህ!🤔

ወንድም አትሁን ተላላ
በልገባው ሳይሞቅ በፈላ
ስንቱ በጃሂል ተበላ
ሲያብላላ ወሬ ሲያንጋ

©FUAD YASIN
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ኩሉ ቢዳዓቲን ዶላላ ምን ማለት ነው
አንዳንድ ካለ ዒልም ለተመቻቸው አጀንዳ ብቻ ፈትዋ እንደሚሰጡት ሰዎች ነው?!
የቢድዐው ስለት ከሲራጥ ሲቀጥን

ክፍል አንድ
====================
"እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት፤ አጅግም ብልሃት ያደርሳል ከሞት"
ሀገርኛ ብሒል
"እጅግም ጡሃር ንጃስ ያመጣል"
አንድ የወሎ ሸህ

አንዳንድ ሁለት ገፅ ቀርተው ስለ ቢድዐ ሚናገሩ ሰዎች ''ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ ..." ....ብሎ የጀሃነም ካታሎጉን መዘርዘር ይቀጥላሉ.....ወንድሜ በዚህ ሀዲስ ላይ የትኛውም ሙስሊም የሶሒነት ጥያቄ አያነሳም...ይኸ የረሱል(ሰዐወ) ንግግር ነው....ይህንን ሀዲስ ግን የሀዲሶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ስታደርገው ነው ችግር የሚፈጠረው...ምን መሰለህ ችግሩ..."ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው" [ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ]ብለህ የጀሃነም ደላላነትህ ላይ ታንቄ እሞታለሁ ስትል...የቢድዐው ስለት የሚያስተርፈው የለም.... ...ከረሱል(ሰዐወ) ህልፈት በኋላ መስጊድ ውስጥ ሰዎች በኡበይ ኢብኑል ከዐብ ኢማምነት ሲሰግዱ ሰይዱና ዑመር(ረ.ዐ) አገኟቸውና "ኒዕመቲል ቢድዐቱ ሀዚሂ"... አሉ...ሰምተሃል! ዑመር ኢብኑል(ረዐ) ኸጣብ፤ ዑመሩል ፋሩቅ... ናቸው ይህንን ያሉት...በግልፅ 'ቢድዐ' ብለው
በነገራችን ላይ 'ቢድዐ' የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም "ፈጠራ" (innovation) ማለት ነው። ከአላህ ሰሞች አንዱ "በዲዕ" ነው፤ መሠል የሌላቸው ነገሮች ፈጣሪ ማለት ነው....ይህንን ጥሬ ትርጉም ይዘን "ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ፤ ኩሉ ደሏሏቲ ፊ ናር" ብለን ስንገግም...የቢድዐው ስለት ማንንም አያስተርፍም....በነብዩ የሕይወት ዘመን ቁርዓን በመፅሐፍ መልክ አልተዘጋጀም....በሰይዱና ዑመር(ረ.ዐ) ጎትጓችነት...ሰይድና አቡበከርሲዲቅ (ረ.ዐ) ቢድዐ ሰሩ...ቁርዓኑን በመፅሐፍ መልክ ጠረዙ፤...ሰይዱና ዑስማን ኢብኑ ዐፋን(ረ.ዐ)...ነብዩ ያላደረጉትን የጁምአ የመጀመሪያ አዛን በማስደረግ ቢድዐ ሰሩ...ሰይዱና አሊይ(ረዐ) በየህያ ኢብኑ የዕመር አማካኝነት የቁርአን ነጠብጣብና ተሽኪል(ፈትሃ፣ ኪስራ...)በመጨመር ቢድዐ (ፈጠራ) አሰፋፉ....ወንድሜ በዚህ አያያዝ የቢድዐው ቁልቁለት ማቆሚያው ሩሩሩሩቅ ነው....የመስጅድ ሚናሬት ፣ የመስጅድ ምንጣፍ ፣ማይክራፎን፣ የኢማሙ ሚህራብ ፣በግመል ና በቅሎ ሳይሆን በመኪና መሄድ፣ በእጅ ሳይሆን በማንኪያ መብላት፣ በስንዴ ቂጣ ፈንታ እንጀራ መብላት ፣ ቀሚስ(ጀለቢያ) እንጂ ጂንስ ማድረግ ፣ ሸበጥ ትቶ እስኒከር ማድረግ፣ በሲዋክ ምትክ ኮልጌት መጠቀም፣በሲዲ ሃዲስ ማሳተም....እያልክ ክሩን ስትተረትረው...አዳዲስ ፈጠራ ሁሉ ጥመት፣ ሁሉም ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ገቢ ይደረጋልና ጀነት ፆም ማደሯ ነው....
እና ምን ተሻለ?
*****
ወንድሜ(ለምን ግን እህቴ አላልኩም?)....የአረብኛን ትርጉም ማወቅ ማለት ቁርአንና ሀዲስ ማወቅ ማለት አይደለም ለዚህ ነው ከተፍሲር በፊት ነህው (የቋንቋ ህግጋትና ሰዋሰው) ተማር የሚባለው። የቁርአንና የሀዲስ መልዕክት ና የገለፃ አይነት ፣ስልትና ክብደት(ዐምና ኻስ፣ ናሲኽና መንሱኽ ፣ ሙጥለቅና ሙቀየድ) በወጉ ገብቶህ እንጂ እንደወረደ ነፃ ትርጉም ተጠቅመህ የምትተነትን ከሆነ አተናተንህ እርስ በእርሱ እየተጋጨ ዘላለም ስትወዛገብ ትኖራለህ...
ለምሳሌ 'ኩሉ' የሚለውን ቃል ስትተረጉም ቀጥታ ትርጉም ማለትም ኩሉ=ሁሉም(All) ብለን ስንቀጥል...ሱረቱል ዩኑስ ላይ [10፥47] ... ሲል ...ነገ የውመል ቂያማ መልዕክተኛ አልተላከልንም ብለው የሚከራከሩትን የት ታደርጋቸዋለህ?...ሱረቱ ፋጢር[35፥22] ......ሲል ኩሉ=ሁሉም(All) ከሆነ የመርዛማዎቹንም ሥጋ ይጨምራል ማለት ነው?....ሱረቱል አህቃፍ[46፥25] ለአድ ህዝቦች የተላከችውን ነፋስ.........ሲል ኩሉ=ሁሉም ከሆነ ቤቶቻቸውስ?ተራሮቹስ (ይግረምህ ሲል አለፍ ብሎ አዛው ላይ ...ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ኾኑ ይላል).....ሌላም አብነት ልጨምርልህ....አቡ ሙሳ አል አሽዓሪይ ባወሩትና ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል (ሰዐወ) [ ﻛﻞ ﻋﻴﻦ ﺯﺍﻧﻴﺔ ] ... ሲሉ ኩሉ=ሁሉም (All) ካልክ ...የነብያት ዓይንስ?
መቼም ከሪያዱ ሷሊሂን አዘጋጅ፥ ኢማም አን ነወዊህ እበልጣለሁ አትለኝም።ኢማም አን-ነወዊይ ሰሒሕ ሙስሊምን የተነተኑበት መፅሐፋቸው ውስጥ (በጥራዝ 6፤ ገፅ 154) እንዲህ አሉ፦ ነብያችን(ሰዐወ) ﻭﻛﻞ ﺑﺪﻋﺔ ﺿﻼﻟﺔ ያሉት ﻋﺎﻡ ﻣﺨﺼﻮﺹ ‹ጠቅላይ ውስን›› ነው። ማለትም ጥሬ ቃሉ ጠቅላይ ሲሆን ትርጉሙ ግን ውስን ነው (በሆነ ነገር የተወሰነ ነው)...Universal thing mentioned in the sense of specific...ወይንም ኩሉ=አብዛኛው (most) ማለት ነው።
አንድ ሀዲስ ላይ ካልተቸነከርኩ ብለህ ነው እንጂ ይሄም አለ.......

ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
©FUAD YASIN
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ቢዳዓ ምንድነው🤔?!
.
.
ነገ በሰፊው በዚህ ጉዳይ ጠብቁኝ

©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


የጁምዓ ሶላት በቱርክ ከ10 ሳምንታት ቡኋላ።
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ሳዑዲ የፊታችን እሁድ በሚከፈቱ ከ90 ሺ በላይ መስጊዶቿ ጸረ ኮሮና መድኃኒት ርጭት አደረገች‼️

ሳዑዲ አረቢያ ከ90 ሺ በሚልቁ መስጊዶቿ የጸረ ኮሮና መድኃኒት ርጭት ማድረጓን የሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ ሪያድ ርጭቱን ያደረችው መስጊዶቹን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡ ከነገ በስቲያ እሁድ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑም የሃገሪቱ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሆኖም በመካ የሚገኙ መስጊዶች ሚኒስትሩ አብዱላቲፍ አል-ሼክ ተጨማሪ ፍቃድ እስከሚሰጡ ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ፡፡

ስለ ወረርሽኙ መከላከያ የጥንቃቄ መንገዶች ግንዛቤን ለመፍጠር ሰፊ ዘመቻዎችን የጀመረችው ሳዑዲ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት በሚል ጥላቸው የነበሩ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እገዳዎችንና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ማቅለል ጀምራለች፡፡ የሃገር ውስጥ በረራዎች የፊታችን እሁድ ይጀመራሉም ተብሏል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በሳዑዲ በአጠቃላይ 80 ሺ 185 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 54 ሺ 553 አገግመዋል፤ 441 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡ ዘገባው የአልአይን ነው።

©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa


ለእነዚህስ ማን ይጩህላቸው!?
በአይሁድ አክራሪ ወራሪ ኢስራኤላዊያን በግፍ ለሚገደሉ ፊሊስጤማዊያን ህዝቦች ማን ይጩህ!?
ማን #Put this as ur profile እያለ ቴሌግራም ፎቶ ይቀይር!?
ሰው ከሆንክ ለሁሉም ልትቆረቆር ይገባል። አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ሲገደል አለም ሲንጫጫ ለፍልስጤማውያንስ!? እነሱ ሰው አይደሉም !?
ቀን በቀን ስንት ህፃናትን፣እናቶችንና አባቶችን እየተገደሉ በዓለም Live እየታየ ዝም ተብሎ አሜሪካ ሲሆን ሁሉም ተንጫጫ አሽቃበጠ እኮ ለምን!?
አሜሪካ ምን ስለሆነች ይጮሃል?!
ፍልስጤም ምን ስለሆነች ዝም ይባላል !?
እኔን የገረመኝ የዚህ ህዝብ ማሽቃበጥ ነው Put this as ur profile እያለ ሼር ይደራረጋል። ፕሮፋይል ማረጉን ያርጉ እኔ ግን Put this as ur profile ብለው ያረጉትን ከማሀይም ለይቼ አላያቸውም።

ትልቅ ዓሊም እና ሙፍቲህ የሆኑት ዶ/ር ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ገነቴ በአንድ ወቅት
ሰውነት ይቀድማል ያሉት ለዚህም ነው።

ጁመዓ ሙባረክ
# free_palestine Israel is the terrorist murder
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa

19 last posts shown.

839

subscribers
Channel statistics