Forward from: ከ ቀደምቶች ንግግር🔊
~ ከሁሉም በላይ ለራሴ ችግር የሆንኩት እኔው ራሴ ነኝ፡፡ ትልቁ ትግሌ ከራሴ ጋር ነው፤ ትልቁ ወሬዬም ከኔው ጋር ነው፡፡ አሳምሬ መገንባት የምፈልገው ትልቁ ህንፃ እኔነቴን ነው፤ ራሴን ካስተካከልኩ ሌላዉን ማስተካከል ቀላል ነው፡፡ መጀመርያ እኔ:ሌላው ጉዳይ ቀጥሎ ነው፡፡
ዛሬን ጠፋሁ ወይም አጠፋሁ ብዬ ተደፍቼና ተከፍቼ አልኖርም፡፡ ኃጢአት ብሠራ ከወደቅኩበት ለመነሳት እፍጨረጨራለሁ፤ ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አላህ ካቆየኝ እስከ ዕለተ ሞቴ በርካታ ዕድሎች እንዳለኝ አውቃለሁ፡፡ ማለዳ በመጣ ቁጥር ተስፋዬም ፈገግታዬም ይመለሳል፡፡ በጥፋቴም ከምንም በላይ የአላህን እዝነት እያሰብኩ ከተጓዥ ወንድሞቼ ጋር ወደ አኺራ ወንዝ እፈሳለሁ፡፡
ደስተኛ ነኝ፡፡ ጠዋት ከቤት ይዤ የምወጣዉም ሆነ ስተኛ ተሸክሜ የምተኛው ሀሳብ የለኝም፡፡ ስወጣ አራግፌ ጭንቅላቴን ወጣለሁ፣ ስገባ ሀሳቤን እደጅ አስቀምጬ ገባለሁ፣ ስተኛም ከትራሴ አርቄው እጋደማለሁ፣ ሐዘን በቤቴም በዉስጤም ሥፍራ ያገኝ ዘንድ አልፈቅድለትም፡፡ ሙሉ ቀን ከዋለብኝ ድክመቱ የኔ ነው፡፡ እሱ እንደ ድንገተኛ እንግዳ ሁሉ መጥቶ የሚሄድ ነገር ነው፡፡ በሰው ቤት ከሦስት ቀን በላይ የማደር ሐቅ የለዉም፡፡
ሶሻል ሚዲያ ላይ የምጣደው ለማንበብ ነው፡፡ ለራሴም ለተከታዮችም ደስ የሚል መልዕክት ለመምረጥ ነው፡፡ በመረጥኳቸው ነገሮችም የደከማቸዉን አበረታለሁ፣ ያዘኑትን አጽናናለሁ፣ ከከፋቸው ጋር እስቃለሁ እጫወታለሁ፡፡
ዓላማዬ የኢማን ህመምተኞችን መርዳት ነው፤ ዋናው እና ትልቁ በሽተኛም እኔው ነኝ፡፡
ከሰው ጋር ጨዋታ ይዤ ለተወሰነ ጊዜ እዘናጋ ይሆናል፡፡ ተዘናግቼ እንደማልቀር ግን ዉስጤ ይነግረኛል፡፡ አንድ ቀን ሳጠፋ ብዉል ኪሳራዬን በሌላኛው ቀን ለማካካስ እታገላለሁ፡፡
ሕይወት ትሂድ ትቀጥል፤ ተነጫንጨን አናስቆማትም፡፡ ተደስተንም አናቆያትም፡፡ ዱንያ ዛሬ ይሁን ነገ ጠፊ ናት፡፡የቀደሙን ሁሉ ምርጦች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ በመሞታቸው ትልቅ ትምህርት ሠጥተዉናል፡፡ እነርሱ በርግጥ ታድለዋል።
ጌታዬ ሆይ ካንተ ጋር ወሬ እንዳለኝ አውቃለሁ፤ የኔን ነገር አደራ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan