የተሟላ የመሰረተ ልማት የሌለበት ቤት ማስረከባቸው ለቤት ኪራይ ዳርጎናል -የ40/60 ቤት ባለቤቶች
👉"የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ተግባር አሳዝኖናል"
ማክሰኞ መስከረም 21 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ቦሌ አያት 2 የሚገኙት ከ7 ሺ በላይ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ከተላለፉ 6 ዓመታትን ያስቆጠሩ ቢሆንም እስካሁን የመሰረተ ልማት አልተሟላልንም ሲሉ የ40/60 ቤት ባለንብረቶች ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
አንድም መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ ሁሉም ኮሚቴ አቋቁሞ እስከ አዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ድረስ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ምላሽ ባለማግኘታቸው በኪራይ ቤት ለመኖር መገደዳቸውን አስታውቀዋል፡፡
ባለንብረቶቹም ቤቶቹ በሽያጭ የተላለፉት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መሰረታዊ የሚባሉ ግንባታዎችን ሳያከናውን በመሆኑ ወደ ቤታችን መግባት አልቻልንም ብለዋል፡፡
አክለውም የውሃና መብራት ቆጣሪ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ እና የኢንተርኔት መስመር እንዲሁም ከ1 ሺ 800 በላይ ቤቶች በርና አልሙኒየም መስኮቶች አለመገጠማቸው እና አለመሰራታቸውን አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በአካባቢው የኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ የሳፋሪ ኮም ኔትወርክ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ መሆኑን እና የመጸዳጃ እና የማብሰያ ቦታዎችም በተመሳሳይ የግንባታ ጉድለት እንዳለ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም “ከንቲባዋ የተገለፁት መሠረታዊ ጉዳዮች ሳይሟሉ እርስዎ የሚመሩት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እስከ ጥቅምት 30/2017 እንድትገቡ የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አሳዝኖናል” ብለዋል።
“ከተጠቀሱት ጉድለቶች ቢያንስ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሠጣቸው መሠረታዊ ግንባታዎች እንዲሠሩልንና ቤታችንን አሳድሰን መግባት እንድንችል ነው” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን "የቤት ባለቤቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በያዙት የሽያጭ ውል መሰረት እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ ቤቶቹን ለሌላ እድለኛ አስተላልፋለሁ ሲል ማስጠንቀቁን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡