“የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያው የኩላሊት ህመምተኞችን ሁኔታ ከባድ አድርጎታል” የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት
👉 “አንድ ድሃ ታማሚ በቀን ከ5 ሺህ ብር በላይ ከፍሎ እንዴት ነው ሊታከም የሚችለው”?
ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ እና መገልገያ ተቋማት ላይ የተለያየ የዋጋ ልዩነት እና ጭማሬ እየተስተዋለ ነው፡፡
ይህን ተከትሎ በጤና ዘርፉ ላይ በተለይም የኩላሊት ታማሚዎች ለአንድ እጥበት 3ሺ500 ብርእንደሚያስፈልጋቸው እና ቀድሞ ከነበረው የአንድ ሺብር የዋጋ ጭማሬ ማሳየቱን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
እጅግ እየጨመረ እና ከቀን ቀን እየከበደ የመጣው የህክምና ወጪ አንድ ታካሚ በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ ያለበትን የኩላሊት እጥበት ወደ ሁለት እና አንድ ዝቅ ለማድረግ እንዲገደድ ስለማድረጉም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
አንድ ታካሚ በአግባቡ መንቀሳቀስ እንዲችል እና ንቅለ ተከላውን እስኪያካሂድ በህይወት ለማቆየት በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት ማድረግ ያለበት ሲሆን በአሁን ሰአት በሳምንት ሶስት ጊዜ ለማድረግ በአጠቃላይ በአንድ ወር 42ሺህ ብር እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል፡፡
ይህም የገንዘብ መጠን መካከለኛ እና አነስተኛ የህክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ላይ የሚጠየቅ እንደሆነ እና ከፍተኛ በሚባሉ ሆስፒታሎች አራት ሺ አምስት መቶ እና ከዛ በላይ ለአንድ የእጥበት አገልግሎት እንደሚጠየቅ አቶ ሰለሞን አመላክተዋል፡፡
እንዲሁም የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ ድርጅቶች እና መስሪያ ቤቶች የእርዳታ ጥሪዎችን እንደሚያቀርብ ነገር ግን መልካም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉ ከዋጋው ጭማሬጋር ሌላኛው ስጋት እንደሆነባቸው ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
በብዛት በበሽታው ተጠቂ ሆነው የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉት ወጣቶች በመሆናቸው እንደሀገርም የስራ ሀይል ያለውን ዜጋ ማጣት ሊያሳዝን እና ሊያሳስብ ይገባል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ሁሉም ሰው ለታማሚዎቹ በተቻለ መጠን እርዳታ ለማድረግ ፍቃደኛ እንዲሆን እና ሁሉም ሰው በየእድሜ ክልሉ የኩላሊት ምርመራ በየጊዜው በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
በቤተልሔም ይታገሱ