የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ካርድ መታገዱ ተሰማ
ዓርብ ህዳር 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን አስታውቋል::
መንግስት ካገዳቸው የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ውስጥ “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አመላክቷል፡፡
ባለስልጣኑ ለእገዳው እንደምክንያት ያቀረበው የመብት ተቋማቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባቸው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራታቸውና ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ካረጋገጠ በኋላ እግድ እንዳሳለፈ ዋዜማ ዘግቧል፡፡