የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ
ጥር 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በአክሱም አካባቢ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
ምክርቤቱ ለክልሉ መገናኛ ብዙሀን በላከው ደብዳቤ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤቶች ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የተፈፀመው ህገወጥ በሆነ የሂጃብ ክልከላ ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ለወራት ከትምህርት ገበታ እንዲገለሉ ማድረጉን አመላክቷል።
ምክርቤቱ አክሎም እስካሁን ድረስ ለተለያዩ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያልናቸው አካላት በአካልና በፅሑፍ ጥያቄ ስናቀርብ ብንቆይም እስካሁን ድረስ ጉዳዩ መፍትሄ ሳያገኝ መጥቷል ብሏል።
እየተካሄደ ያለው ሰልፍም የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤትና ከክልሉ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዋና ፅህፈት ቤት መነሻውን አድርጎ በሮማናት አደባባይ ፍፃሜውን እንደሚያደርግ ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት የተገኘው መልእክት አመላክቷል።
በተመሳሳይ በአጠቃላይ አራት የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን እና እስካሁንም ድረስ የተደረሰ የጋራ መግባባት እንደሌለ እና ተማሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እስማኤል አብድራህማን ገልጸው ነበር፡፡
እንዲሁም በአስተዳደር ደረጃ ማንም ሂጃብ አይልበሱ ብሎ የሚከራከር አመራርም ሆነ ግለሰብ ባይኖርም ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ የሰጠም አለመኖሩም መገለጹን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡