ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንን ገጽ ይከተሉ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በየካቲት 2014 በእኔ በአሕመዲን ጀበል መስራችነት የተቋቋመው ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ንቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተምሳሌታዊ ዜጐችና ተቋማትን በኢትዮጵያ እንዲፈጠሩ አበክሮ እየሠራ ያለ ሀገር በቀል የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ ጥናትና ምርምርን መሠረት በማድረግ የአቀም ግንባታ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ለግለሰቦችና ለተቋማት እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁ መሰረት ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና ከሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር በተመረጡ የአገራችን የተለያዩ ከተሞች ለአራት ቀናት የሚቆይ የወጣቶች ስልጠና እያሰለጠ ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከል በወራቤ፣ በሻሸመኔና በሀዋሳ ከተማ በዋናነት በአመራር (leadership) እና በሥራ ፈጠራ (entrepreneurship) ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች በስኬት ተጠናቋል።በሌሎች ከተሞችም ይቀጥላል።
ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጋር በደረሰው የመግባቢያlpih v ስምምነት በክፍለ ከተማ ደረጃ የእስልምና ጉዳዮች እና የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣት ሊጎ አባላትን በተቋማዊ አሠራር ላይ አቅማቸውን የማጎልበት ሥልጠና ሰጥቷል።በቅርቡም ከየኢትዮጵያ፣ከአዲስ አበባ፣ከኦሮሚያና ከሸገር ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዉስጥ የተለያዩ ዳይሬክቶሬትና መምሪያዎች የተውጣጡ ባለሚያዎችን በአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል የአምስት ቀናት ተግባር ተኮር ስልጠና ሰጥቷል።
ከስር ባለው ሊንክ በመግባት የኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንን የፌስቡክ ገጽን ፎሎም እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።👇
https://www.facebook.com/share/p/15tMebcEMg/