አል አኒስ ቁርአንና ሱና አካዳሚ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


👉የቻናሉ ትኩረትና አላም ቁርአን ማስተማር
👉ቅን ባለራእይ ዲኑን የሚወድ በእውቀት የበለፀገ ትውልድ መፍጠር ነው ሼር በማድረግ ለምታግዙንና ትምህርቶቻችንን ለምትከታተሉ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን አስተያየት በዚህ እንቀበላለን@Alanis166_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


👂🔊የረመዳን ጥሪወች
↪️ቀን አምስት
↪️ ለሀብታሞች ለነዛ የገንዘብ ባልተቤቶች
በረመዳን ምጽዋት

ከረመዳን ወር መለያዎች
አንዱ ሰደቃ ነው

በጤና እያሉና በሙሉ ጥንካሬ ላይ ሆነው የሚሰጡት ሰደቃ ሞት አፋፍ ላይ ሆነው ከሚናዘዙት አሊያም በሽታ ስር ወድቀው ከሚሰጡት የበለጠ ደረጃ አለው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ‹በላጩ ሰደቃ አንተ ጤና ላይ እያለህ ነፍስህ ስስታም ሆና ሳለ ሀብትን እያሰብክና ድህነትን እየፈራህ ምትሰጠው ነው፡፡ ነፍስህ ለመውጣት ተቃርባ ‹ለእገሌ ይህን ያህል ለእገሌ ይህን ያህል እስከምትልበት ጊዜ ድረስ አታቆይ፡፡ ያኔ በርግጥም የእገሌ ሆኗልና፡፡›


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


✴️🔊ሱረቱ በቀራ 211-256 🎵👂

የቁርአን ግብዣ

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ

ቁርአን ለባለቤቶቹ አማላጅ ይሆናል

ከአቢ ኡማማ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በተወራ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ቁርአንን አንብቡ እሱ እኮ (ቁርአን) በትንሳኤ እለት ለባለቤቱ አማላጅ ሆኖ ይቀርባል፡፡›› ሙስሊም

ቁርአን በምስክርነትም እንዲሁ ይቀርባል፡-

ከነዋስ ኢብኑ ሰምዓን አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተገኘው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አለ፡-

‹‹በትንሳኤ ዕለት ቁርአንና በምድራዊ ዓለም በሱ ይሰሩበት የነበሩ ባለቤቶቹ ይቀርቡና በየተራ የበቀራ ምእራፍና የአል ዒምራን ምእራፍ እየመጡ ለባለቤቶቻቸው (ለሚቀሯቸውና ለሚሰሩባቸው) ምስክርነታቸውን ይሰጡላቸዋል፡፡›› ሙስሊም  

በተጨማሪም አቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ቀጣዩን ሀዲስ ይነግሩናል፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በእለተ ትንሳኤ ቁርአን ይመጣና፡- ጌታዬ ሆይ (ቁርአን የሚቀራውን ሰው) አስውበው ይላል። ሰውየውም የክብር ዘውድ ይደረግለታል፡፡ ጌታይ ሆይ ጨምርለት ይላል፡፡ የክብር ጌጥ ይለብሳል፡፡ ከዚያም ጌታዬ ሆይ ከሱ የሆነን ውደድ ይላል፡፡ ጌታውም ከሱ የሆነን ይወዳል፡፡ከዚያም እንዲህ ይባላል፡- አንብብ፣ ከፍ በል፣ በያንዳንዱ አንቀፅ ደረጃህ ከፍ ይደረግልሃል፡፡›› ቲርሚዚ  


👂🔊የረመዳን ጥሪወች
↪️ቀን አምስት
↪️ረመዳን ከዱአጋር

ከረመዳን ወር መለያዎች
አንዱ ዱአ ነው

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ


✴️🔊ሱረቱ በቀራ 142- 210 🎵👂

የቁርአን ግብዣ

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ

ቁርአን ለልብ እርጋታ

ቁርአን ለልብ ሰላም
✔️📚🎧


👂🔊የረመዳን ጥሪወች
↪️ቀን አራት
↪️ረመዳን ከቁርአን ጋር

ከረመዳን ወር መለያዎች
ቁርአንን በሱ ውስጥ ማውረዱ ነው

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ🎧


ዛሬ ገራሚ ስጦታ ልስጣቹ👇

#የንጽጽርን ሁኔታ #አንድ_ደረጃ ከፍ
እንዲሉ
#የምፈልጉ እነዚህን ቻናሎች
ይቀላቀል👇
ይቀላቀላሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል 👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿
👉🏿👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👉🏼👇🏻👇🏻👇🏻👈🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿 👉🏾 ቻናሎቹ ለማግ ይንኩት👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👉🏼👆🏻👆🏻👆🏻👈🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👉🏽👆🏼👆🏼👆🏼👆🏼👆🏼👈🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👉🏾👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👆🏽👈🏾👈🏿
👉🏿👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾👈🏿
👉🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿👆🏿☝️


የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል

በየ ቀኑ የብርሀን ጎዳና የሚዙ ሰለምቴዎች የሰለሙበት የድምፅቸው ለስማት እና በዚ
ተቀላቀሉ👇👇join👇
https://t.me/+WcX0xjLLtHhhMzVk
https://t.me/+WcX0xjLLtHhhMzVk


👂🎧 ግብዣ ቁርአን በአቡ ነጅሚያ

ቁርአንን ማንበብ ከዝህች ዓለምና በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ ይበልጣል


🔊👂የረመዳን ጥሪ
ቀን ሶስት
↪️ረመዳን ከጾም ጋር
↪️የጾም ደረጃ
እጥር ምጥን ባለ ገለጻ

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
➯የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች
፡፡፡።፡፡፡፡።።።።።።።።።።

1✍))))
#ረመዳን ነክ ጉዳዩች

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ للهِ تعالى عند كلِّ فطرٍ عُتَقاءَ من النارِ، وذلك في كلِّ ليلةٍ﴾

“አላህ በሁሉም የረመዳን (የኢፍጣር ቀን) ከእሳት ነፃ የሚላቸው አሉ። ይህም የሚሆነው በሁሉም ሌሊት ነው።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1340


2✍))))
#ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَلِلصّائِمِ فَرْحَتانِ يَفْرَحُهُما: إِذا أَفْطَرَ فَرِحَ بفِطْرِهِ، وإذا لَقِيَ رَبَّهُ فَرِحَ بصَوْمِهِ.﴾


“ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት። ደስታዎችም፦ ፆመኛ ማታ ሲያፈጥርና በአኼራ ጌታውን ሲገናኝ ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1151




3✍))))
#ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

  ﴿الصَّلَواتُ الخَمْسُ، والْجُمْعَةُ إلى الجُمْعَةِ، وَرَمَضانُ إلى رَمَضانَ، مُكَفِّراتٌ ما بيْنَهُنَّ إِذا اجْتَنَبَ الكَبائِرَ.﴾

“አምስቱ ሰላቶች፣ ከጁምዓ እስከ ጁምዓ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው ያሉትን ኃጢአቶች ያብሳሉ ታላላቅ ወንጀሎችን ሲቀር፡፡”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 233

https://t.me/alanisquranacademy


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
👍✔️


🔊👂የረመዳን ጥሪ
ቀን ሁለት
↪️ረመዳን ከኢስቲግፋር ጋር
↪️ኢስቲግፋር ማብዛት ፋይዳው

በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ✔️🎧


✴️🔊ሱረቱ በቀራ 1-48 🎵👂

የምሽት ግብዣ

📢በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ
የደስታ የሀሴት የተረጋጋ ምሽት ያድርግላችሁ

ቁርአንን የሚያነቡ ሰዎች የአላህ ቤተሰቦች ናቸው፡፡

ከአነስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡

‹‹ለአላህ ከሰዎች የሆኑ ቤተሰቦች አሉት፡፡›› ሰሃቦችም ‹አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ እነሱ እነማን ናቸው;› ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እነሱ የቁርአን ቤተሰቦች ናቸው፡፡ የአላህ የተለዩ ቤተሰቦች፡፡›› ነሳኢና ኢብኑ ሂባን✔️📚


የረመዳን  ጥሪወች

ቀን አንድ  

የረመዳን ልዩ ስጦታ

ረመዳን ልዩ የስልጠና ማእከል

በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ

https://t.me/alanisquranacademy


የምስራች ከአል አኒስ ትምህርት ቤት
እንደሚታወቀው የወሮች ሁሉ ቁንጮ የሆነውና ታላላቅ ችሮታዎችን ጠቅልሎ የያዘው የረመዳን ወር ከነሙሉ ስጦታው ገብቷል
ታላላቅ ትሩፋቶችን አዝሎ በአላህ ፀጋዎች ደምቆ ልቦቻችንን በብርሀኑ ሊሞላን ፊት ለፊታችን ተደቅኗል
በአላህ ፍቃድ በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ የሚመራው አል አኒስ ትምህርት ቤት በቋሚነት
የዚህን የተከበረ ወር የለውጥ ክፍሎች ስልጠና ይዞላችሁ ቀርቧል  ይህ ስልጠና ነጻና ሁሉን አካታች በመሆኑ  ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር  በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል 

የረመዳን ጥሪ  ስልጠና  ተከታታይ ፕሮግራምቻችን
1 ረመዳን መግቢያ
2 ረመዳን ከኢስቲግፋር ጋር 
3 ረመዳን ከጾም ጋር
4 ረመዳን ከቁርአን ጋር
5 ረመዳን ከዱአ ጋር
6 ረመዳን ከሶደቃ ጋር
7 ረመዳን ከተቅዋ ጋር
8 ረመዳን ከልጆች ጋር
9 ረመዳን ከለይል ስግደት ጋር
10 ረመዳ ከጊዜ ጋር
11 ረመዳን ይቅር ከመባባል ጋር
12 ረመዳን ከትግስት ጋር
13 ረመዳን ከዚክር ጋር
14 ረመዳን ከተውበት ጋር
15 ረመዳን ከስነ ምግባር ጋር
16 ረመዳን ከአንድነት ጋር
17 ረመዳን ከምላስ ጣጣ ጋር
18 ረመዳን ከኢኽላስ ጋር
19 ረመዳን አላህ ከማመስገን ጋር
20 ረመዳን ከሙታበአ ረሱል ጋር
21 ረመዳን ከአሽረል አዋኺር ጋር
22 ረመዳን ከለይለተል ቀድር ጋር
23 በረመዳን የለይለተል ቀድር መገኛ
24 በረመዳን የለይለተል ቀድር ምልክቶች
25 በረመዳን የሰወች ስህተት ወሷያ
26 በረመዳን ኢስቲቃማ ጽናት
27 የረመዳን ስንብት
28 የረመዳን ስንብት
29  ኢድ በተመለከተ
30  ኢድን በተመለከተ
በረመዳን እነዚህን ሁሉ የለውጥ የስልጠና ክፍሎችን
ለመሰነቅ እንዘጋጅ

የአላህን ጥሪ ሰምተው ፈጣን  ምላሽ ከሚሰጡ
የሱን አንቀጾች ሲነበቡላቸው ልባቸው ከሚረጥብና

ሲጾሙ ደግሞ ምላሳቸው ጆሮአቸውና አይኖቻቸው ከሚጾሙ ሰወች ሰወች ያድርገን

የአላህ እዝነትህን አደራ
ሁኔታችንን ሁሉ አስተካክልልን
ለሰከንም ከራሳችን ጋር አትተወን  አሚን ያረበል አለሚን

ሼር ሼር

https://t.me/alanisquranacademy


ሰበር ዜና

ሳኡዲ አረቢያ ታላቁ የረመዳን ጾም ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አስታወቀች።

በሳኡዲ አረቢያ የቴሌስኮፕ ባለሙያዎች አዲስ የረመዳን ጨረቃ ማየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በዛሬው ዕለት የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን በነገው ዕለት የረመዳን ጾም የሚጀመር ይሆናል።

@alanisquranacademy


🎧የጁሙአ ግብዣ👂

🎤በአቡ ነጅሚያ አብደል ሀሚድ

ሱረቱ ከህፍ ሙሉውን

☞♦️በጁሙዓ ቀን ልንፈፅማቸው ከሚገቡ ተግባራቶች☜ መካከል፦

➊▪️በሌሊት እና በቀን ክፍለ-ጊዜ ሰለዋት ማብዛት

➋▪️ገላን ማታጠብ

➌▪️መፋቂያ መጠቀም

➍▪️ጥሩ ልብስ መልበስ

➎▪️በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ

➏▪️ሱረቱል ከህፍ መቅራት

➐▪️ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ

➑▪️ዱዓ ተቀባይነት የሚያግኝበትን ሰአት መጠባበቅ

https://t.me/alanisquranacademy




በረመዳን ሙስሊም ከማህበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነት

ይህ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከሌሎች ግንኙነቶች አንፃር እጅግ እይታው ከፍ ያለ ሲሆን እያንዳንዱ እንቅስቃሴም በተግባር የሚገለፅ ነው፡፡ሙስሊሞች በማህበረሰባዊ ስራዎች ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባው ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆንም ተገቢ ነው፡፡በማህበረሰባዊ ግልጋሎቶች ላይ መከባበር፣መረዳዳትን ያጠቃለለ ስራዎች የሚሰሩበት የለውጥ ክፍል ነው፡፡
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ አልሁጁራት 49፤10
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم -: ((مثل المؤمنين في توادِّهم وتراحمهم وتعاطفهم مثل الجسد، إذا اشتكى منه شيء تداعى له سائر الجسد بالسهر والحمى)) 
መልእክተኛው(ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ “ሙስሊሞች እርስ በርስ መዋደዳቸው፣ በእዝነታቸውና በርህራሄያቸው እንደ አንድ ሰውነት ናቸው። አንዱ የሰውነት ክፍል የታመመ እንደሆነ ሌላው የሰውነት ክፍል በትኩሣት እና ያለ እንቅልፍ በማደር ይታመማል” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ሙስሊም ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር

ይህ ማህበረሰባዊ ለውጥ ከስብከት በዘለለ መልኩ በተግባር እንዲገለፅም ኢስላም ያዛል፡፡ ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር የማህበረሰባዊ ስራዎችን አለመተግበር ከኢስላማዊ መርህ ጋርም ያጋጫል፡፡አንድ ሰው ሁልጊዜም ቢሆን ጉጉቱ መልእክተኛውን(ሰዐወ) መከተልና እርሳቸውን መምሰል ይኖርበታል፡፡ መልእክተኛው(ሰዐወ) ደግሞ ከሙስሊሙም ጋር ሆነ ሙስሊም ካልሆኑ የማህበረሰቡ አካሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት በጥበብና በእዝነት ብሎም በመልካም ግሳፄ የታጀበ ነው፡፡ይህም ትልቅ ተግባር የኢስላም መንፈሱም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ አነህል 16፤125
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم : ((فوالله لأنْ يَهدِيَ الله بك رجلاً، خير لك من أن يكون لك حُمْر النَّعَم))
ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ በጌታዬ እምላለሁ አንድን ሰው ወደ እውነተኛው መንገድ መምራት የቀያይ ግመሎች ባለቤት ከመሆን የተሻለ ነው፡፡
እነዚህ የለውጥ ክፍሎች ላይ በፅናት መታገልና መበራታት እንዲሁም ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት የአዎንታዊነትን አዲስ ገፅ መክፈት ነው፡፡ ከረመዳን ትምህርት ቤት እነዚህን ሙሉ የለውጥ ክፍሎች ለመሰነቅ እንዘጋጅ!
አላህ በሰላም ያድርሰን…….

https://t.me/alanisquranacademy


ሙስሊም ከነፍሱ ጋር ያለው ግንኙነት
የረመዳን ወር ነፍስን ለመታደግ፣ እርሷን ለመተሳሰብ፣ወደ መልካም ቦታ ለመግራት መልካም የለውጥ አጋጣሚ ነው፡፡ ለውጥ የሚጀምረው ነፍስን ከማስተካከል ነው፡፡ ያለባትን ስህተት ለማስተካከል ሁልጊዜ የሚቀጥልና ተከታታይ ልማድ ሆኖ የሚቀር ክትትል ያስፈልጋታል፡፡ ይህ ክትትል ግለሰቡን ወደ ተሻለ መስመር ያደርሰዋል፡፡
يقول الحسن البصري – رحمه الله – : “المؤمن قوَّام على نفسه، يحاسب نفسَه لله – عز وجل – وإنما خفَّ الحسابُ يوم القيامة على قومٍ حاسَبوا أنفسَهم في الدنيا، وإنما شقَّ الحساب يوم القيامة على قوم أخَذوا هذا الأمرَ من غير محاسبة”.
ሀሰን አልበስሪ (ረዐ) እንዲህ ይላሉ፡ ሙእሚን የራሱ ነፍስ ላይ ብርቱ ነው፤ ለአላህ ብሎ ነፍሱን ይተሳሰባል፤በዚህ አለም ላይ ነፍሳቸውን የተሳሰቡ ሰዎች አላህ(ሱወ) ነገ (የውመል ቂያማ) ሂሳባቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ ነፍሳቸውን ከመተሳሰብ የተዉ(የተዘናጉ) ሰዎችን ደግሞ አላህ ሂሳባቸውን ያከብድባቸዋል፡፡

https://t.me/alanisquranacademy

20 last posts shown.