"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ኤልሮኢ፡ (⚜ብሒለ አበው⚜)

⚜ የተባረከች ዓይን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች

⚜ የተባረከች ጆሮ የንስሃ መዝሙር በመስማት እራሷን ታነፃለች

⚜የተባረከች ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሃ ይንቆሮቆርበታል።

⚜የተባረከች ምላስ የአምላኳን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ትቀበላለች።

⚜የተባረከ አንደበት ላይ እግዚአብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም

⚜የተባረከች አንገት  የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች

⚜የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሣ በፍቅር ትሞላለች

⚜የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች

⚜የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@aleroe
@alerobot


ኤልሮኢ፡ (⚜ትምህርት⚜)

” አስተርእዮ ማርያም “

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።

ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።

ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።
የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።
ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።

ሰአሊ ለነ ቅድስት
የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን።

@aleroe
@alerobot


ኤልሮኢ፡ (⚜ትምህርት⚜)

ወርሃ ፅጌ  የእመቤታችን ስደት

የእናታችን የድንግል ማርያም ስደት ታሪክ
ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያሉት ቀናተ, ሳምንታት "ወርሃ ፅጌ"በመባል ይታወቃል።ብዙዎች "ፆመ ፅጌ" ብለው ይጠሩታል ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናች በፍትሃ ነገስት የተደነገጉት 7 አፅዋማት አሉ።

ይህ ወቅት ፆመ ፅጌ ለመባል በቤተክርስቲያናችን ቅኖተ መሰረት ከእነዚህ ከ 7ቱ አፅዋማት ጋር አልታወጀም ስለዚህም "ወርሃ ፅጌ እንላለን" ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በፈቃደኝነት የእመቤታችን ፍቅሯን ለመግለፅ ስደቷን ለማሰብ ከልጇ ዘንድ ምህረትን ለማግኘት ከድንግል ማርያም በረከትና ምልጃ ረድኤትንም ለማግኘት መፆም ይችላል።

እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፉ በሕልም ታይቶ "ሄሮድስ ህፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሳ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብፅ ሽሸ፤ እስከነግርህም ድረስ በዚያ ኑር" እርሱም በሌሊት ተነስቶ ህፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብዝ ሄደ።

ከእግዚአብሔር ዘንድ ልጄን "ከግብፅ ጠራሁት" ተብሎ በነብይ የተነገረው ይፈፀም ዘንድ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ። ማቴ 2፤13_15

ድንግል ሆይ! ስደትሽን እያሰብሽ ከልጅሽ ዘንድ ምህረትና ይቅርታን አሰጭን! በበርሃው በደረሰብሽ  ራሃብና የውሃ ጥሙን  አሳሰቢልን፤ ልጄን ይገሉብኛል እያልሽ ስታለቅሽ ከአይኖችሽ የፈሰሰው መሪር እምባ አሳስቢልን! ድንግ ሆይ! በአካላዊ ስጋችን ከመልካም ምግባር ወደ ክፉ ምግባር የተሰደዱትን ስለ ስደትሽ ብለሽ እነሱን መልሻቸው !ድንግል ሆይ ከልጅሽ ጋር ተሰደሽ ስደትን የቀመሽ ስደተኛ ልጆችሽንም መልሻቸው ።ስለኢትዮጲያም አብዝተሽ አሳስቢ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።

@aleroe
@alerobot


Forward from: "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ
*ብሒለ አበው*
አንድ ሰው አንድ አባት ጋር ቀርቦ አንዳንዶች መላእክት ተገለጡልን ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው።
እሳቸውም ከዚህ የበለጠ ደስ የሚያሰኘውስ ሁልጊዜ በኃጢአታቸውን ቢያዩ ቢያስቡ ነበር ሲሉ መለሱለት።
አንድ አባት እንዲህ አሉ ስሕተተኛ በሆናቹ ጊዜ ሁሉ ሌላውን አትወንጅሉ። ይህ የሆነው በራሴ ኃጢአትና ድክመት ምክንያት ነው በሉ። ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲህ በማለት ተናግረዋል በርግጥ መላእክት ሊታዩክ ቢችሉ እንኳን አትቀበል ራስህን አዋርድ። እኔ ሃጢአተኛ ነኝና መላእክትን ባይ ምን ይጠቅመኛል በል።
@aleroe


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

#ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ?
#ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? 
#ሙልሙል ለምን ይታደላል? 
#ጅራፍ ለምን ይጮሃል  ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡ 

#ጅራፍ
  በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ
     ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡
ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሰወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል  ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)
         ይህን ያውቁ ኖሯል?

ለሰባኪያን መቆሚያ ከፍ ያለ ቦታና አትሮንስ በቤተክርስቲያን መጠቀም የተጀመረው ከ386 ዓ.ም አከባቢ ባለው ዩሐንስ አፈወርቅ ነው።  ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ ቀሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ በብዛት ይሰበሰብ ነበር። ነገር ግን የዩሐንስ ቁመት አጭር ነቀረና ከፍ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይና ድምፁም እንዲሰማ መቆሚያ ስፍራና ያጽሐፍት ማንበቢያ አትሮንስ ተሰራች። ቤተክርስቲያንም ከዚያ ዘመን ጀምሮ አትሮንስን ትጠቀምበት ጀመር።

ኑዛዜ በቤተክርስቲያን የተጀመረው ሕጋዊና ድንግል ከሆነው የእስክንድርያ 12እኛ ፓትራያርክ ከአባታችን ከቅዱስ ድሜጥሮስ ወዲህ ነው።አባታችን በከንቱ አምተውት የነበሩ ምእመናን በእግዚአብሔር ፋቃድ ክብሩ ቀተገለጠላቸው ጊዜ አባታችን ይቅርበለን ብለው ንስሐ ሲገቡ ይፍትሕ ይኅድግ ብለው ናዝዘዋል። ኑዛዜም ያን ጊዜ ተጀምሯል።

አንገት ላይ ማተብ ማሰር የተጀመረው ቀን5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሶርያ ያስተምር በነበረው በአባታችን በያዕቆብ ዘእልበረዲ ነው። አባታችን እያስተማረ በሚያጠምቅበት ጊዜ ለተጠመቁትና ያልተጠመቁት እየተቀላቀሉ ቢያስቸግሩት ለማየት ይቻል ዘንድ ለተጠመቁት ምዕመናን ማተብ ያስርላቸው ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማተብ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መለያ ምልክት ሆነ።
         
@aleroe


ኤልሮኢ:(⚜ምክር⚜)
 
   ዝምተኛው መነኩሴ (#ራስአገዝ)

ከዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ ፀሎት አንዱ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን በተጓዙበት ጎዳና ምራኝ" ነበር፡፡ የዚህ ጸሎት ትርጉም ቅዱስ አድርገኝ ማለት እንደነበር በህይወታቸው ፍፃሜ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ እንጂ ቅዱስ ለመሆን ማሰብ ወይም በቅድስና መንገድ ለመጓዝ መሻትና መጸለይ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ከፈጣሪያችን ትእዛዛትና ፈቃድ አንዱን ለመፈጸም መመኘት ነውና እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስም "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" በማለት የቅድስናን ህይወት እንድንኖር እንደመከረን ስናስተውል ቅዱስ የመሆን ትእዛዝ እንዳለብን እንረዳለን፡፡ ስለቅድስና ሲነሳ እኛ ቅዱሳን ልንሆን ይገባል ማለቱ በራሱ ወደር የማይገኝለት ድፍረት ሆኖ ሳይሰማን አይቀርም፡፡ነገር ግን መሻቱ ሳይሆን የቅድስና ቁምነገር  ነኝ አለማለቱ እና በጭራሽም  ነኝ ብሎ አለማሰቡ ላይ ነው፡፡ ሰው ቅዱስ የሚሆነውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ባሻገር በምርጫውና በፍላጎቱ ነውና ይህን የሚያስረዳን ነው።

ዲያቢሎስ ስለመረጠ ከቅድስና ጎድሏል፥ ቅዱሳን መላእክት ደሞ በምርጫቸው ቅዱሳን ሆነዋል ፡፡ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ ለቅድስና መጠራታችንን እና መታዘዛችን እንዲፈጸምልን መጸለይ መሻት መጣር ያስፈልገናል፡፡የጌታችን አማናዊ ቃሉ "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።"ይለናልና።(ማቴ 7:7)
ስለዚህ ቅዱስ የመሆን ፍላጎት ቅዱስ ነውና በማሰባችን ወይም በመመኘታችን ድፍረት መስሎን መጨነቅ አይደገፍም፡፡ ነገር ግን በትህትና መለመንና ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሚፈጸም ማመን ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር ቸርነት (ሰጪነት) በጥረታችን የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ "እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (ዮሐ 15:5) እንዳለ  ያለእርሱ ቅዱስ መሆን ቀርቶ ቅድስናን ማሰብም እንኳን አይቻልም፤ ከእርሱጋ ግን ሁሉ ይቻላል፡፡ ወደቅድስና ከሚመሩን በርካታ ነገሮች እጅግ ጥቂቶቹ በመቀጠል ቀርበዋል፡፡

✞የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ፍቅር ማሰላሰል

✞ህዋሳትን ኃጢአት ከመስራት መጠበቅ

✞ ለሰሩት በደል በቶሎ መፀፀት

✞ከሰው ክብርን አለመፈለግ

✞ምስጋናን አለመሻት

✞ ጥላቻንና ትችትን በፍቅር መቀበል

✞ መጸሐፍቅዱስን አዘውትሮ ማንበብ

✞ ያለማቋረጥ  መጸለይ

✞በምስጢራት  መካፈል

✞ትእዛዛቱን ለመፈጸም መጣጣር

✞በምክረ ንስሀ መጓዝ

✞ራስን እንደተለየ ነገር አለመቁጠር

✞ራስን መገምገም መመልከት

✞ቃለእግዚአብሔርን ማዳመጥና

✞የምንሰማዉን ቃል መፈጸም

✞ከልብ የሆነ ጾምን መጾምና መጸለይ

✞በጎ አድራጎትን መፈጸም

ማንኛውም የምንሰራው ሥራ እግዚአብሔርን ደስ እንዲያሰኝ ብሎ እንጂ አንዳች ጥቅም አገኝበታለሁ  በማለት  አይደለም፡፡ መሪ ምክንያቱ ፍቅር  እንጂ ጥቅም መሆን የለበትም፡፡ ለቅድስና መጋደል እንጂ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ መጀመር የውድቀት መጀመሪያው ሳይሆን መጨረሻ መሆኑን ማስመር ይገባል፡፡ እነኚህ በየጥቂቱ ልናድግባቸው የምንችላቸው መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚጠይቁ ልምምዶች ናቸው ፡፡

ይቆየን!

@aleroe
@AleroeBot


ኤልሮኢ:(⚜ምክረ አበው⚜)

             የአንድ አባት ምክር

በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡

በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎችን ክፋት ለመሸፈን እና በክፋታቸው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ችግሩን ይፈታዋል? ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጥያቄዎች ይነሡ ነበር::

ያን ጊዜ እኒህ አባት እንዲህ አሉን፡፡

«ብዙ ልጆችን የወለደች የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል አጋቧት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የለውም፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ጠላ ጠምቃ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ ለዘመዶቹም ይበትነዋል፡፡

የት ትሂድ? የሠፈሩ ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ አልሆነም፡፡ እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነው የሚቆጥሩት፡፡ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር፡፡ የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?

ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ በዚያ ቤት ሰላም ጠፋ፡፡ ፍቅር ጠፋ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ ነገር እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ያወራል፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ መድረስ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡

ታድያ ይህንን ሃሳባቸውን ለአንድ ሽማግሌ ጠቢብ ሰው ነግረው ገንዘብ እና ሃሳብ እንዲሰጣቸው ፈለጉ፡፡ ሄደውም አማከሩት፡፡ ያም ሽማግሌ ሃሳባቸውን ሁሉ ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፡፡

«ልጆቼ ልክ ናችሁ ሩቅ ሀገር ሄዳችሁ፣ የምትችሉትን ያህል እየሠራችሁ፣ የራሳችሁን ኑሮ በመኖር ችግሩን ሁሉ መርሳት እና መገላገል ትችላላችሁ፡፡ ምን ያስጨንቃችኋል? ቤት ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ሀገርስ ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ግን አንድ ነገር አስቡ፡፡ እንዲህ ማድረጋችሁ ራሳችሁን ብቻ ከችግሩ ታወጣላችሁ እንጂ ችግሩን አትፈቱትም፤ እናንተ ችግሩን ትረሳላችሁ እንጂ ችግሩን አታስወግዱትም፡፡

«ደግሞም የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን የበደለውን ያህል እናንተም ትበድሏታላችሁ፡፡ እስኪ አስቡት ለዚህች ለእናታችሁ ከእናንተ በቀር የደስታዋ ምንጭ ማን ነው? ሁሉም ነገርዋ የሚያሳዝን እና የሚያስመርር ነው፡፡ እናንተ ግን የደስታዋ ምንጮች ናችሁ፡፡ የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን ያሳዝናታል፤ የእናንተ ጥላችኋት መሄድም ያሳዝናታል፤ እርሱ ብቻዋን እንድትለፋ ትቷታል፤ እናንተ ጥላችኋት ስትሄዱም ያለ አጋዥ ትተዋታላችሁ፤ እርሱ በመስረቅ ዘረፋት፣ እናንተም ባለ መስጠት ዘረፋችኋት፤ ታድያ ከእርሱ በምን ተሻላችሁ?

እናንተኮ ያሰባችሁት ለእናታችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ነው፡፡ እናታችሁ ስለተቸገረች አይደለም ያዘናችሁት፣ ችግሩ እናንተን ስለነካ ነው፤ እናታችሁ ስለተራበች አይደለም ያዘናችሁት ረሃቡ ስለነካችሁ ነው፡፡ በእናታችሁ ላይ የደረሰው ችግሳይሆን ስለችግሩ ከየሰው አፍ መስማት ነው የሰለቻችሁ፤ ችግሩን ለመቅረፍ አይደለም መሄድ የፈለጋችሁት፤ ችግሩን ላለማየት እና ላለመስማት ነው፡፡

ከዚያ ይልቅ ሥራ ሠርታችሁ ገንዘብ አግኙ እና ለእናታችሁ ምግብ ስጧት፤ የሚያስርባትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ልብሷን ቀይሩላት፣ የሚያሳርዛትን አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ስትታመም አሳክሟት፣ የሚያሳምማትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ የወግ እቃዎቹን ሰብስቡና አስቀምጡላት፤ዝክረ ታሪኳን ሊያጠፋ የተነሣውን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ እርሱ እያረጀ ሲሄድ እናንተ ግን እያደጋችሁ ነው፡፡ ስለዚህም እየበዛችሁ እና እየመላችሁ ሂዱና ይህንን ቀፍድዶ የያዛትን የመንደሩን ሕግ አስተካክሉት፡፡ ምናልባት የእንጀራ አባታችሁ ቢሞት ሌላ የእንጀራ አባት ደግሞ እንዳይተካ፡፡ እንደዚያ ካደረጋችሁ እናንተ የእናታችሁ ልጆች ናችሁ፡፡ ያለ በለዚያ ግን የእንጀራ አባታችሁ ተባባሪዎች ናችሁ፡፡

ሸረሪት ታውቃላችሁ፡፡ ከሰው ቤት ግድግዳ ላይ ድር አድርታ፤ ወልዳ ከብዳ ትኖራለች፡፡ ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ግን ከቤቱ ወጥታ ቀድማ የምትሮጥ እርሷ ናት፡፡ ቤቱ የኖርኩበት ነው፡፡ ወግ መዓርግ ያየሁበት ነው፤ እሳቱን በማጥፋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብኝ አትልም፡፡ መሸሽን ብቻ ነው የምትፈልገው፡፡ ለራስዋ ብቻ ነው የምታስበው፡፡ ይህ ከሸረሪትነቷ የመጣ ነው፡፡

እናንተ ግን ሰዎች እንጂ ሸረሪቶች አይደላችሁም፡፡ ሰዎችን እያያችሁ ከሀገራችሁ እና ከቤተ ክርስቲያናችሁ ልትርቁ አትችሉም፡፡ አያገባንም ልትሉ አትችሉም፡፡ እሳቱን ማጥፋት ትታችሁ ከእሳት ለማምለጥ ብቻ ልትሮጡ አትችሉም፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ ሸረሪቶች እንጂ ሰዎች አይደላችሁም፡፡» አሏቸው

ይህንን ሰምተው ልጆቹ ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡

እስኪ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ የዚህች ሀገር እና የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ፍላጎት ምንድን ነው? ይህች ሀገር እና ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ ረዳት እንዲቀሩ ማድረግ አይደለምን?  እናንተም እንተዋት፣ እናቁም፣ እንሽሽ ስትሉ ያለ ረዳት እያስቀራችኋት ነው፡፡ የእነርሱ ፍላጎት ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶን ተስፋ ማስቆረጥ አይደለምን? እናንተም ተስፋ ከቆረጣችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ልጆቻቸውን እያስመረሩ ማስኮብለል አይደለምን? ከኮበለላችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ታሪክን፣ ቅርስን፣ ክብርን፣ ልዕልናን መመዝበር እና ማራከስ አይደለምን? እናንተም ታሪኩን፣ ቅርሱን፣ ባህሉን፣ ክብሩን ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በራሳችሁ ዓለም ብቻ ስትቀሩ የእናንት ፍላጎት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎት ተሳካ ማለት ነው፡፡

ታድያ አሁን እናንተ መመለስ ያለባችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡ የምትፈልጉት የጠላቶቿ ፍላጎት እንዲሳካ ነው ወይስ በመከራ ውስጥ ያለችውና ቀን የጣላት የእናታችሁ ፍላጎት እንዲሳካ ? ምረጡ፡፡

✍ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

@aleroe
@Alerobot




ኤልሮኢ ፡ (⚜ዝማሬ⚜)

               የተወደደ ስምሽ ማርያም

የተወደደ ስምሽ ማርያም
እንደአንቺ ንፁህ በዓለም የለም
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም

በንፅህናሽ በመመረጥሽ
ድንግል በእውነት እፁብ ድንቅ ነሽ
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም

ፍጥረታት አንቺን ይማፀኑሻል
ከሲኦል ዓለም አውጪን ይሉሻል
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም

አስራትሽን ኢትዮጵያን
ጠብቂልን ድንግል ህዝቧን
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም


@aleroe
@Alerobot


ኤልሮኢ :(⚜ስነፅሁፍ⚜)

ግዑዙ ከበሮ

ሁለት ወራት ሙሉ እጥፍ ቅልጥፍ ብሎ
በጾምና ጸሎት ከስራው ተገልሎ
በሐዘን በድማሜ ዘውትር አዘንብሎ
የቆየው ከበሮ ዛሬ ዜና ሰማ
የራቀው ቅላጼ በርጋታ ተሰማ
ከሩቅ አስተጋባ በሚነሽጥ ዜማ
ድምጹ ከአጽናፍ አለም ፈሰሰ በግርማ
በአምሳለ እየሩሳሌም በቅድስት ከተማ
ግዑዙ ከበሮ እንዲ ከረቀቀ
በሁዳዴ ተኝቶ ትንሳኤን ካወቀ
የሰው ልጅ ምን ነካው  እንቅልፉ ጨመረ
በትንሳኤ ማግስት እንደተኛ ቀረ።
               

@aleroe
@Aleribot


⚜ መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡
⚜አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡
⚜ ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡

@aleroe
@Alerobot


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

የካቲት 16
ኪዳነ ምህረት


‹ ኪዳን › የሚለው ቃል ‹‹ ተካየደ – ተዋዋለ ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ ፤ ተማማለ ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል ፣ መሐላ ፣ ቃል ኪዳን ፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹ ፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል ፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡

በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና ‹‹ ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ›› እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ‹‹ ሰላም ለኪ ማርያም እምየ ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው? ›› አላት፡፡

እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን ፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን ፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡

ጌታችንም ‹‹ ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ›› ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው ‹‹ … ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ ‹ መታሰቢያሽን ያደረገ ፣ ስምሽንም የጠራ ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤›› በማለት የሚማጸነው፡፡

በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ‹‹ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና ‹‹አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ›› በማለት፣ ‹‹ የእግዚአብሔርን እንግዳ›› ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡

እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል ‹‹ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡

በመጨረሻም ‹‹ በድንግል ማርያም ስም ›› አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ ‹‹እስኪ ቃሉን ድገመው ›› አለው ፤ በሽተኛውም መልሶ ‹‹ ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ ›› ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው ፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት ‹‹ ጨረስህብኝ ›› ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡

በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው ‹‹በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ? ›› ባለው ጊዜ ‹‹ ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል ›› ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን ‹‹ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ? ›› አለችው፡፡

ጌታችንም ‹‹ ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን? ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?›› ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡

ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው ፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ‹‹ ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም ›› ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ‹‹ ሥላሴን ፣ ጻድቃንን ፣ ሰማዕታትንን ፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ ›› አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል ‹‹ ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም ‹ የአምላክ እናት አይደለችም› ብለህ ካድልኝ ›› አለው፡፡

ሰወየውም ‹‹ እርሷንስ አልክድም ›› ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን ‹‹ ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም፡- ‹‹‹ ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ › ያልኸው ቃል ይታበላልን? ›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ምሬልሻለሁ›› አላት፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ‹‹ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ ›› ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን ፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ ፣ ማስማር ( ይቅርታ ማሰጠት ) ማለት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን ‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን ›› እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡-


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

​​ዘወረደ

የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ዮሐ.3-13፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡

ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡

@aleroe
@Aleroebot


Forward from: "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ:

#እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን
☞ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
☞የአብይ ስያሜዎች ስንት ናቸው?
☞የአብይ ፆም ለምን ታላቁ ጾም ተበለ?
☞የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት?
☞የአብይ ጾም ለስንት ሳምንት ይፆማል
☞ስለ ዘወረደ ምን ያውቃሉ?

1ኛ. ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
ፆመ ፦ ተወ " ታቀበ"ታረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው።
ፍቹም ምግብን መተው ' መከልከል' መጠበቅ ማለት ነው።
ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት
ነው። ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት
ነው ።
ፆም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ፆም አለ።
ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው ።
ነብያት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም
ነበር።//ዘፀ ፴፬÷፳፰//34*28//
በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በፆም
ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። //ዮሐ ፪÷፯_፲// 2*7-20//
በሐዲስ ኪዳንም ፆም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ
ስጋዌው የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።//፬÷፪// 4*2//
ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን
በፆም እሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል።// ማቴ ፲፯÷፳፩//
17*21/ሐ
ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙ ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው
ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በፆም እና በፆለት ላይ እንዳሉ ነበር።// የሐዋ
፲፫÷፪//13*2//
ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በፆምና
በፆለት ነበር።//የሐዋ፲፫÷፫//13*3//
ፆምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ፆም ማለት፦ጥለላት ማባልዕትን ፈፅሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ
ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ ፣መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ
እግዚአብሔር በመንበርከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር
ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ፀጋን የምትሰጥ ፣የወንጌል ስራ መጀመሪያ፣
የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው
፣የንፅህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የእንባ መገናኛ መፍለቂያ፣
አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምትነቃቃ፣ ሰውነትን
በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ
መድኃኒት ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ
በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገስታት፣ካህናት በፆምና
በጸሎት ፅሙድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው
በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልንም እንዲያጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን
ፈፅሞላቸዋል።
በሀድስ ኪዳን ፆም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው። //
ማቴ፭÷፮// 5*6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ስጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት
ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው።
ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች:አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች። ~~~ስለዚህ የሚፆም ሰው በፈቃደ
ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሁኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን
ምስጢር ለማየት ከአለማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል።
በአለም እየኖረ ከአለሙ ይለያል። ከአለም አይደለምና//
ዮሐ፲፭÷፲፱//15*19 //

2ኛ.
ዐቢይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምየተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐቢይ
እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ
ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ /መዝ.47፥1፣ መዝ.146፥5/፡፡ ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም
ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት
ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ
አምላካችን ስለጾመው ነው፡፡፣ /አሞ.7፥1/፡፡ ሦስተኛ በዓተ ጾም ይባላል፡፡
የጾም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓት ማለት ነው፡፡ አራተኛ
ጾመ አርባ ይባላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 /ዓርባ/ ቀን
ስለሆነ፣ /ማቴ.4፥1/ አምስተኛ ጾመ ኢየሱስይባላል፡፡ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ
ስላዘዘን፣ ስድስተኛ ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል
ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ
ድጓ ስለ ዘመረ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ማቴ.4፥1
ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡ ዐቢይ ጾም
ስምንት ሳምንታት /55 ቀኖች/ አሉት፡፡ ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሑድ ይገኛሉ፡፡
አሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ
የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

3ኛ.
የአቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት
ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና
ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ
ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር
ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት
ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።

4ኛ.
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
ዘወረደ
ቅድስት
ምኩራብ
መጻጉዕ
ደብረዘይት
ገብርሔር
ኒቆዲሞስ
ሆሣዕ

ሰለ ተትርጉማቸው ከታች ከተለጠፈው ሰንጠረዥ ተመልከት

5ኛ. ለምን አብይ / ታላቅ
ተባለ
አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን
ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ
መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና
ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና
ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው

6ኛኛ.
የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም
ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ 614 ዓ . ም ኪርዮስ የተባለ
የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ 14 ዓመት በኋላ በ 628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

@aleroe


Forward from: "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
Abiye-Tsome-Hudade.pdf
60.6Kb
⚜ትምህርት⚜

ስለ ዐቢይ ፆም

💠.ዐቢይ ለምን ተባለ ?
💠.ስንት ሳምንታት አሉት ?

አጠር ብሎ የተዘጋጀ
ያንብቡ share ያድርጉ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot


ኤልሮኢ: (⚜መዝሙር⚜)

     እግዚአብሔር ያፅናናሽ

እግዚአብሔር ያፅናናሽ እንባሽን ያብሰው
ቤተክርስቲያን ሆይ እስከመጨረሻው
ካህንሽ በመቅደስ ከበጎቹ ጋራ ስለታረደብሽ
እንደ ራሔል እንባ እግዚአብሔር ያስብሽ

ስለ ጌታ ፍቅር ማህተሟን ይዛ አክሊል ተቀዳጀች
በደሙ ከዋጃት ከክርስቶስ ጋራ እኖራለሁ አለች
የእምነት ሰማዕትነት ሲመጣ በገሃድ
ይሻሙ ነበረ ከእሳቱ ለመንደድ
         አዝ
በዚህ በእኛ ዘነን ቅዱሳን ተሻሙ
አክሊልን ለመውሰድ ከሁሉ ሊቀድሙ
የተክለ ሃይማኖት የክርስቶስ ሰምራ ህፃናት ተነሱ
በመሞት ህይወትን ከእግዚአብሔር ሊወርሱ
        አዝ
አህዛብ አትድከም በመግደል አትፀድቅም
ነፍሰ ገዳይነት አሸንፎ አያውቅም
በበቀል ጭካኔ የሰው ልጅን ማረድ
እጅግ የወጣ ነው ከሃይማኖት መንገድ
         አዝ
እቺ ቤተክርስቲያን የተገነባችው በደም ስለሆነ
በሞት ህይወት ሊያገኝ ክርስትያን ታመነ
ምድሪቱ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት
ህዝቧም ሊወድቅ ቀርቧል እንደበግ መስዋዕት

          ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ

@aleroe
@Aleroebot


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

     የመስቀል ዓይነቶች በንድፍ አሠራራቸው


1. የመጾር መስቀል:-

በቅዳሴ እና በማዕጠንት ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን የሚይዘው ነው።

2. የእጅ መስቀል:-

ካህናት ምእመናንን የሚባርኩበት በእጅ የሚያዝ የመስቀል ዓይነት ነው።

3. የአንገት መስቀል:-

ምእመናን ለአምላካቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ከማዕተባቸው ጋር በአንገታቸው የሚያደርጉት ነው።

4. እርፈ መስቀል:-

በማንኪያ ቅርጽ ተሠርቶ በእጅታው ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት ነው። ሠራዒው ዲያቆን በቅዳሴ ጊዜ የአምላካችንን ክቡር ደሙን ለምእመናን የሚያቀብልበት ነው። እንዲሁም ጌታችን በእለተ አርብ የተወጋበት ጦር ምሳሌ ነው።

@aleroe
@Aleroebot

ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

        የመስቀል አይነቶች በተሠሩበት ቁስ

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል። መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸውን ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው። ብለው አባቶች ያስቀመጡትን እንደሚከተለው እንመለከታለን፦

1ኛ. የእንጨት መስቀል:-

ጌታችን የተሰቀለው በዕፅ ወይም በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ሲሆን አዳም ዕጽ ወይም እንጨትን በልቶ ሞትን በማምጣቱ ክርስቶስም በእንጨት ተሰቀሎ ህይወትን ሊሰጠን በእንጨት መስቀል መሰቀሉን ለማሰብ ነው።

2ኛ. የብረት መስቀል:-

ጌታችን በአምስቱ ቅንዋተ መስቀል ለመቸንከሩ ምሳሌ ነው።

3ኛ. የብር መስቀል:-

ይሁዳ በሠላሳ ብር አሳልፎ ስለመስጠቱ አንድም ደግሞ  ከብር ቢሰራ ተስፋን፣ ዕድልን ያመለክታል። ይኸውም እርሱ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ሊሆን በደሙ ዋጋ ከፍሏልና ከእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል።

4ኛ. የወርቅ መስቀል፦

ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለው ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው።

5ኛ. የመዳብ መስቀል:-

መዳብ ቀለሙ ቀይ ይመስላል: ጌታችን ለእኛ ብሎ ያፈሰሰው ደም ምሳሌ ነው።

" ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። "
" ገላ 6÷14"

የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።

@aleroe
@Aleroebot


ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)

ነጠላ አለባበስ እና ምክንያቶቹ

1.ማጣፋት

ይህ አለባበስ ቀኝ እጅን በውጭ በኩል ነፃ በማድረግ እና ግራ እጅን በውስጥ በኩል ትንሽ ክፍተት በመተው የሚለበስ አለባበስ ነው።
ይህም ቀኝ እጃችን ነፃ መሆኑ የዘመነ ፍስሃን ፣ ዘመነ ሐዲስን እና የአዳምን ነፃ መውጣት ያሳያል። ግራ እጃችን መሸፈኑ(መታሰሩ) ደሞ ዘመነ ብሉይን ፣ዘመነ ፍዳን እና የሰይጣንን መታሠር ያሳያል።

2.መስቀለኛ ማጣፋት

ይህ አለባበስ ደሞ በቀኝ በኩል ያለው ጥለት ወደ ግራ ከዛ የግራው ደግሞ ወደ ቀኝ ተደርጎ የሚለበስ አለባበስ ነው። ይህም የቀኙ ወደ ግራ መቅደሙ የሰው ልጅ በድሎ ከገነት መባረሩን ያሳያል። ቀጥሎ ከግራ ወደ ቀኝ መደረጉ ደሞ በሲኦል የነበረውን አዳም ክርስቶስ በገዛ ፈቃዱ ከ5500 ዘመን በኋላ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ወደ ቀደመ ክብሩ እንደመለሰው ያሳያል።

3.ማደግደግ

ይህ አለባበስ አብዛኛውን ጊዜ በሰሙነ ሕማማት የሚዘወትር ሲሆን ይህም በቀኝ ያለው ጥለት ወደ ግራ ካጠፋን በኋላ የግራውን ዙሪያችንን በመጠምጠም የምንለብሰው አለባበስ ነው።
ምሳሌነቱም የመላእክት ሲሆን ቅዱሳን መላእክት ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሰግኑታል። ልክ እንዲሁ በፍትሐ ነገስት እንደተገለፀው አንድ ሰው ለፀሎት ሲቆም የታጠቀ ሊሆን ይገባዋል። ይሄም በፀሎት ጊዜ በትጋት እንድንቆም ይረዳናል።


@aleroe
@Aleroebot



20 last posts shown.

1 398

subscribers
Channel statistics