ኤልሮኢ :(⚜ስነፅሁፍ⚜)
ግዑዙ ከበሮሁለት ወራት ሙሉ እጥፍ ቅልጥፍ ብሎ
በጾምና ጸሎት ከስራው ተገልሎ
በሐዘን በድማሜ ዘውትር አዘንብሎ
የቆየው ከበሮ ዛሬ ዜና ሰማ
የራቀው ቅላጼ በርጋታ ተሰማ
ከሩቅ አስተጋባ በሚነሽጥ ዜማ
ድምጹ ከአጽናፍ አለም ፈሰሰ በግርማ
በአምሳለ እየሩሳሌም በቅድስት ከተማ
ግዑዙ ከበሮ እንዲ ከረቀቀ
በሁዳዴ ተኝቶ ትንሳኤን ካወቀ
የሰው ልጅ ምን ነካው እንቅልፉ ጨመረ
በትንሳኤ ማግስት እንደተኛ ቀረ።
@aleroe@Aleribot