"ገንዘብ የተሳሳተ የደህንነት ስሜትን ይፈጥራል። አንዳንድ ሰዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ስላገኙ የማንነካ ነን ብለው ያስባሉ። ገንዘቡ ሞትን የሚከላከልላቸው ወይም ሞት ፈፅሞ የማይደፍራቸው ይመስላቸዋል ። እውነታው ግን ይሄ አይደለም።
ሕይወት በቅጽበት ልታከትም ትችላለች ። በአንዲት ትንኝ ጠቅታ፣ በአንድ የተሳሳተ ግንኙነት፣ ወይም በአንዲት ጥይት አማካይነት ሕይወት በዐይን ጥቅሻ ፍጥነት ልታበቃ ትችላለች ።
ሀብት የማይበገር ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን ደስታን አያረጋግጥም.።
ብዙ ገንዘብ በማግኘት ብቻ ደስተኛ እንደማይኮን ብዙ ጊዜ ለሰዎች እነግራቸዋለሁ። በገንዘብ ደስተኛ እሆናለሁ ብለህ ካመንክ ምናልባት ብዙ ገንዘብ አግኝተህ አታውቅም ማለት ነው።
ለእኔ፣ የገንዘብ ትክክለኛው ዓላማ ከሌሎች ጋር መኖር፣ ሰዎችን መርዳትና በእነዚህ ግንኙነቶች ደስታን ማግኘት ነው። ማንም ሰው ሁሉንም ነገር ለራሱ በማዋል ዘላቂ ደስታን አያገኝም።
እውነተኛ ደስታ የሚመጣው የተቸገረን ሰው በመርዳትና ፊታቸው ላይ ያለውን ፈገግታ ስንመለከት ነው። ለእኔ አስፈላጊ የሆነው ሀብት ይሄ ነው." - ማይክ ታይሰን
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433