የሁለቱ መንትዮች ግጥምጥሞሽ
ከአንድ ማህፀን የወጡ ተመሳሳይ መንትዮች እንደ ተወለዱ ይነጣጠሉና በተለያየ ቤተሰብ እጅ ያድጋሉ፡፡ የሁለቱም አሣዳጊዎች አይተዋወቁም ነበር፡፡ የሚኖሩትም በተለያየ ግዛት ሲሆን አስገራሚው ታሪክ የተጀመረው ስም ሲወጣላቸው ነበር። ሁለቱም ጀምስ ተባሉ፡፡ ሁለቱ ጀምሶች ሳይተዋወቁ አደጉ።ሁለቱም ሲያድጉ በሙያቸው አናጢ ሆኑ፡፡ አሁንም አልተዋወቁም ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሁለቱም ከያሉበት ግዛት ፍቅረኛ አግብተው ትዳር መሠረቱ፡፡ የሁለቱም ሚስት ስም ደግሞ ተመሣሣይ ሆነ፡፡ ሊንዳ። ከዚያም ሁለቱም ባለትዳር ወንድማማቾች ልጅ ወለዱ፡፡ የሁለቱም ልጆች ወንድ ሆኑ፡፡ የሁለቱም ስም ‹አለን› የሚል መጠርያ ሆነ፡፡ ጀምስ አለን እና ጀምስ አለን፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ትውውቅ የለም! ኋላም ሁለቱም መንትዮች የመጀመሪያ ሚስታቸውን ፈቱ፡፡ በመቀጠልም ሁለቱም ሁለተኛ ትዳር መሰረቱ፡፡ የሁለቱም ሁለተኛ ሚስቶች ስም ተመሳሳይ ሲሆን ቤቲ ይባላሉ፡፡ ከአርባ ዓመት በኋላ ተነጣጥለው ሲኖሩ ቆይተው በአጋጣሚ ተገናኙ፡፡
@Amazing_fact_433