ይህ ማሽን ትኩስ ዳቦና ፡ ፒታ ሰርቶ በነጻ ይሰጣል ።
.....
በዱባይ በኳታር እና በሌሎችም የUAE ከተሞች ረመዷን በመጣ ቁጥር ለእንግዶች ፡ ለመንገደኛ ( ሙሳፊር ) እና ስራ እየሰሩ ላልሆኑ ሰወች የሚዘጋጅ የነጻ ኢፍጣር ምግብ በየቦታው ይዘጋጃል ።
ባብዛኛው መስጅድ ይህ አይነት ዝግጅት አለ ፡ ከዚህም ሌላ በዱባይ በዛ ያሉ ቦታዎች ፡ ትኩስ ዳቦ ወይም ትኩስ የሩዝ ማባያ ቂጣ ( ፒታ ) ሰርቶ በነጻ የሚሰጥ ማሽን የሚገኝ ሲሆን ፡ የሚፈልጉትን መርጠው ሲያዙት ፡ በነጻ ይሰጣል ። በሌሎችም የuae ከተሞች በገበያ አዳራሾች ጭማቂ ፡ ሩዝ ፡ ሳንቡሳ እና ወተት የያዙ ትላልቅ ፍሪጆች ይቀመጣሉ ።
.....
አንዳንድ ሰው ደግሞ አለ ፡ ቢቸግረውም ይሉኝታ ይዞት ወደነዚህ አዳራሾች የማይሄድ ፡ ይህን ስለሚያውቁም ከላይ ያልናቸው አይነት በምግብ የተሞሉ ትላልቅ ፍሪጆችን ሰው የማይበዛበት መንገድ ላይ ያስቀምጣሉ ።
....
እና በአብዛኛው ፍሪጆች ላይ የሚፅፉት አንድ ፅሁፍ አለ ይህን የምናደርገው ለአሏህ ብለን ነውና ፡ ምንዳም ሆነ ምስጋና ማቅረብ አይጠበቅባችሁም ። የቸገረው ሁሉ በነጻ ሊወስድ ይችላል . የሚል ፅሁፍ ይፅፉና ማመስገን እንኳን እንዳትችል ከወዲሁ ይነግሩሀል ። በነገራችን ላይ ይህንን ፡ በመንግስት ደረጃ ብቻ ሳይሆን ፡ ግለሰቦችም የሚያደርጉት ነገር ነው ።
በእነሱ አስተሳሰብ ያን ማድረግ የእነሱ ግዴታ ፡ በነጻ መውሰድ ደግሞ መብትህ እንደሆነ እንዲሰማህ እያደረጉ ነው
ዋሲሁን ተስፋዬ✍