ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
👉የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤
👉ባለቤታቸው ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤
👉ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ህክምና የሰሩ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈታቸው ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት በማድረጋቸው የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ዋርድ በስማቸው ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ህክምና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤
👉የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆም፤
👉በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስማቸእ Talent Scholarship እንዲቋቋም ተወስኗል።
ውሳኔው አስቀድሞ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በኋላም ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ በተወለዱ በ37 ዓመታቸው ባሳለፍነው ቅዳሜ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news