አዋጭ ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ ት/ቢሮ ጋር በጋራ የሚሠራ በመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባደረገው ጥቆማ መሰረት አፄ ናኦድ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አድራሻ አራዳ ክ/ከ/ወ/06 በመሄድ ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወልደመላክ መርዓነህ ጋር ውይይት ተደርጎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች ብቻ ተጠንተው እንዲቀርቡ ስምምነት በተደረገው መሰረት፣ ለትምህርት ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍ ተደርገዋል ፡፡ በትምህርትቤቱ 434 ወንድ እና 598 ሴት በድምሩ 1,032 ተማሪዎች እየተማሩ የሚገኙ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ያለበትን የግብዓቶች እጥረት በማየት 33 የመፅሃፍት አይነት እና 29 የላብራቶሪ እቃዎች አዋጭ ፋውንዴሽን ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ አድርጓል ፡፡