✔️መልስ፦ ጻድቅነት አንጻራዊ ነው። አንድ ጻድቅ ጥቂት በደል ካለችበት የዚያች በደል ፍዳ በዚህ ምድር ይከፈለዋል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው አልዓዛር ጻድቅ የነበረ ቢሆንም በነበረችበት ጥቂት በደል ምክንያት በምድር ድኻና በሽተኛ ሆኖ ኖረ። ነዌ ክፉ የነበረ ቢሆንም ጥቂት መልካምነት ስለነበረው በነበረችው ጥቂት መልካምነት በምድር ሀብታም እንዲሆን ሆኖ ተከፈለው ይላል። ጻድቅን መከራ አያገኘውም ማለት በሲኦል መከራ አያገኘውም ማለት ነው። እንጂ በምድርማ ብዙ ቅዱሳን መከራ እንደገጠማቸው አንብበናል ተምረናል።
▶️፴፩. “የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል” ይላል (ምሳ.15፥17)። ትርጉሙ ቢብራራልኝ?
ቁጥር 27 ላይ “ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል" ሲልስ ነግዶ ከማትረፍ ጋር እንዴት ይታያል?
✔️መልስ፦ የሰባ ፍሪዳ ከጎመን ይልቅ የተወደደ ነው። ነገር ግን ተጣልተው የተወደደውን ፍሪዳ ከመብላት ይልቅ በፍቅር ሆነው የተናቀውን ጎመን መብላት ይበልጣል ማለት ነው። በጥላቻ ሆነን ከምናገኘው ብዙ በፍቅር ሆነን የምናገኘው ጥቂት ይሻላል ማለት ነው። ነግዶ በሚገባ ማትረፍ ኃጢአት አይሆንም ንግድ ለምእመናን የተፈቀደ ሥራ ነውና። ነገር ግን ትርፍ ለማግኘት ብሎ ሰው መሳሳት የለበትም። ከዚህም መንቀፍ የፈለገው መሳሳት መልካም እንዳይደለ ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።