አታልቅሽ በቃ
።፡።።።።፡።።።
ያመንሽው ቢከዳሽ
የእኔ ያልሽው ቢሸሽ
እድሌ ነው ብለሽ
ከቶ እንዳትከፊ
እንባሽን ዋጥ አርገሽ
በብርታት እለፊ
የአንድነት ቀዳዳው
ሽንቁሩ ቢሰፋም
የአብሮነት ሞገሱ
ከልቡ ቢጠፋም
አላወቀም እንጅ
እናት እና እህት ነች
ሴት ልጅ አትገፋም
እረሳሁሽ ካለሽ
አንችም ተይው በቃ
ፍቅር ህይወት እንጅ
አይደለም እቃቃ
አልሆንሽም ካለሽ
ተይው በቃ ይቅር
ባንድ ወገን ብቻ
ፀንቶ አይቆምም ፍቅር
ተይው በቃ ይቅር
🤦🤦🤦🤦🤦
በአንድ እግር ጉልቻ
ጎጆ አይቀለስም
ከሚታመን እንጅ
ከማያምን ሰፈር
ታቦት ወጥቶ አይነግስም
ተይው በቃ እህቴ
ተለያየን ብለሽ ጥቁር አትልበሺ
እንባሽን ጥረጊው ይቅር አታልቅሺ
ሴት ማለት እናት ነች
ይህንን አትርሺ
ልቧን አደንድና እናት ሁሉን ቻይ ነች
ብትከፋም እንኳን መሳቅየለመደች
ችግር ቢደቁሳት
🧑🎨🧑🎨🧑🎨🧑🎨🧑🎨
አካሏ ቢርድም
በራብ እና ውሀ ጥም
በችግሯ ክብደት
ወገቧ ቢጎብጥም
ነገን ችላ ብላ
እናት ተስፋ አትቆርጥም
አንችም
ችግር መጋፈጥን ከእናቶች ተማሪ
ያንች ያልሆነን ሰው
ትቶኝ ሄደ ብለሽ በእንባ አታቀርቅሪ
ይልቅ
በተስፋ ጠብቂ የአምላክሽን ጥሪ
ልክሽን በልክሽ እስኪሰጥ ፈጣሪ
አይዞሽ🤦🤦🤦🤦🤦🤦
✍belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
።፡።።።።፡።።።
ያመንሽው ቢከዳሽ
የእኔ ያልሽው ቢሸሽ
እድሌ ነው ብለሽ
ከቶ እንዳትከፊ
እንባሽን ዋጥ አርገሽ
በብርታት እለፊ
የአንድነት ቀዳዳው
ሽንቁሩ ቢሰፋም
የአብሮነት ሞገሱ
ከልቡ ቢጠፋም
አላወቀም እንጅ
እናት እና እህት ነች
ሴት ልጅ አትገፋም
እረሳሁሽ ካለሽ
አንችም ተይው በቃ
ፍቅር ህይወት እንጅ
አይደለም እቃቃ
አልሆንሽም ካለሽ
ተይው በቃ ይቅር
ባንድ ወገን ብቻ
ፀንቶ አይቆምም ፍቅር
ተይው በቃ ይቅር
🤦🤦🤦🤦🤦
በአንድ እግር ጉልቻ
ጎጆ አይቀለስም
ከሚታመን እንጅ
ከማያምን ሰፈር
ታቦት ወጥቶ አይነግስም
ተይው በቃ እህቴ
ተለያየን ብለሽ ጥቁር አትልበሺ
እንባሽን ጥረጊው ይቅር አታልቅሺ
ሴት ማለት እናት ነች
ይህንን አትርሺ
ልቧን አደንድና እናት ሁሉን ቻይ ነች
ብትከፋም እንኳን መሳቅየለመደች
ችግር ቢደቁሳት
🧑🎨🧑🎨🧑🎨🧑🎨🧑🎨
አካሏ ቢርድም
በራብ እና ውሀ ጥም
በችግሯ ክብደት
ወገቧ ቢጎብጥም
ነገን ችላ ብላ
እናት ተስፋ አትቆርጥም
አንችም
ችግር መጋፈጥን ከእናቶች ተማሪ
ያንች ያልሆነን ሰው
ትቶኝ ሄደ ብለሽ በእንባ አታቀርቅሪ
ይልቅ
በተስፋ ጠብቂ የአምላክሽን ጥሪ
ልክሽን በልክሽ እስኪሰጥ ፈጣሪ
አይዞሽ🤦🤦🤦🤦🤦🤦
✍belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19