በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አምላክ ልጁን ላከ ፥ የማይጠልቅ ጀንበር
ድንግል እናት ሆነች ፥ የብርሃን መንበር ።

ከሰማየ ሰማይ ፥ መጣ በትህትና
አየነው ታቅፋው ፥ ትንሽ ብላቴና።

ያየፍዳ ዘመን ፥ ብርሃን ሆነ ለምለም
በክርስቶስ ልደት ፥ ፀሀይ ወጣ ለአለም።

✍ አቤል ታደለ

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

"መልካም ገና"


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ምንኛ....
ምንኛ ኃይል ኖረው
የአዳም እንባ ፀፀት
ከመንበርህ ስቦህ ያስተኛህ ከበረት፤
ምንኛ ቢያሰቃይህ ነው
የአዳም ፍቅር እና ናፍቆት
ቤተመንግስት እያለ የተወለድከው ከበረት?
ላንተስ አይገባም
ያ የከብቶች ማደሪያ፤
አንተ እኮ ቅዱስ ነክ
ዓለም ሳትፈጠር የነበርከው መጀመሪያ።
እንዴት ታድያ በረትን መረጥክ
ከሞላ ቤተመንግስት?
ዓለምን ትህትና ያስትማርከው እረኛ የፍቅር አባት፤
ባልችልም መመለስ ያንተን ውለታ
ማስታወስ አያቅተኝም ልደትህን
ሁሌም ታህሳስ 29 የኔ ጌታ።

መልካም ገና ለሁላቹም።

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ፀጉሯን ታጥብቀው

'
'
ፊት ለፊቴ ተቀምጣለች
ድግስ አላት ትጠጣለች
ይመስለኛል ሰክራለች

ወይም ሰክሬለሁ
ጠጣለች መሰለኝ
ወይም ጠጥቻለሁ

ታየኛለች በድግግም
ታፈጣለች በሰከንዱ
ይጨንቀኛል እንደ ምንም
አይጨንቀኝም እንደ ወንዱ

ጨፈረች እንደልቧ
ትጮኻለች እንደ ዓለም
እሷን ማወቅ
ለእኔ ቀርቶ
ላለም ሰውም ብርቅ አደለም

መስላኝ ነበር ስገጣጠም
መስሎኝ ነበር የፈለገች
መስሎኝ ቀረ እንደተራ
ወንድነቴን እንደናቀች

ተጨንቄም ተዋወኳት
እንደምንም ክብሬን ጥዬ
ስሟን ነግራኝ ስሜን ረሳው
አላጣት ምንም ብዬ

ብዬ ብዬ ብዬ....

በመሃል በጭፈራው
በሰቆጣ ዘፈን
ስትዘፍን ሳያት ፣
ድንገት ተቀየረች
የለበሰችው ፀጉር
ወልቆ ጉድ አረጋት

😏

geez_mulat 🦘

ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ሰው ከክብሩ ሲወርድ ፥ ፈጣሪውን ሲተው
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፥ ሰው መሆን ሲያቅተው

የሰው ልጅ እንደ ሰው ፥
እንዴት እንደ ሚሆን ፥ ሆኖ ስላላየው
ሰው ሆነ ፈጣሪ ፥ ሰው መሆን ሊያሳየው።

✍ አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ብልጭ 
'
'
ስንቱን ነገር ነውር ልበል
ስንቱን ነገር  ላስተምርሽ
ስንቱን ስንቱን ማለቴ እንኳ
ስንቴ እንደሆን በነገርኩሽ

ተመከሪ ኧረ ስሚኝ
ጨንቆኛል ያንቺ ነገር፣
ትልቅ ነበርሽ አትበሳጭ
ክብረቢስ ነሽ እንደ ሀገር ፣

አትቅለይ ባደባባይ
መጋረጃ ቀሚስ ለብሰሽ
ቆርቆሮ ነው ወርቅ አደለም
አንገትሽ ጋ ስትዳበሽ ፣

ይጋለጣል እንደ ቡዳ
በእሳት ዘመን ውሃ ሰጦሽ፣
በደረቀ እሾህ ሄደሽ
ራት አልሽኝ ያንቺን ግጦሽ ፣

አታዋርጅኝ እባክሽ
ክብር አለኝ ለመሬቱ፣
አትዝለይ ይጋለጣል
ካለ ዘፈን ሲሆን ምቱ፣

እኔ ብሆን አልዳኝሽም
እኔ ብሆን አልተውሽም
የትም ሄደሽ አትቅለይ
አታምሪም ማሪያምን
አምነሽ ተ ቀ በ ይ ፣

መስሎሽ ከሆን እንደቅናት
ያንቺን ብልጭ የማልወደው
ያንቺን ማማር ማልፈልገው፣
ውበትሽ ጋ እንድራመድ
መርጋት ነበር 'ሚያስፈልገው ፣

ስንቴ ልምከር ያንቺን ጉዳይ
ነፍጥ ብል ጫካ ካለም፣
ሁሉን ቦታ አዳርሰሻል
ያንቺ እውነት ካለም' የለም ፣

አረጀሁኝ እንደዘበት
አትሰሚኝም እዛው አለሽ ፣
ይሄ ልቤ ይሆን እንዴ
ያንቺን እድሜ የተዋሰሽ ፣
'
'
ግዕዝ ሙላት 🦘

@geez_mulat

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ዘምሪ

ከንፈርሽ ሲላቀቅ ግጥሙን ሊያዜመው
ሊቀፅል ሲነሳ ፍክት ሊያደርገው
ዜማን ሊሞሽራት ሲኩላት ሲያስጌጣት
የድምፅሽን ብርሃን አልብሶ ሲያስውባት
      
         እኔ እጨነቃለሁ
ድምፅሽ ሴጣን ይመስል ደርሶ እለከፋለሁ
  
.......አንቺ ስትዘምሪ......
ዛር በውስጡ እያለ ጠበል እንደገባ
የማወራው ቆቦ ስሜቴ አራምባ
  
   ዘምሪ አንቺ ብቻ
  ቀፅይ አንቺ ብቻ
  ተቀኚ ያለ አቻ


የዳዊት በገና ድምፅሽ ላይ ተገኘ
የዕዝራ መሰንቆ በለዛሽ ተቀኘ
      
ምነው ባደረገኝ ጥርስ ወይ ከንፈርሽን
ድምፅሽ በኔ ሲያልፍ እንዳያት ገነትን

      የምሬን ነው ምልሽ
ዘፈን ሀጢአት ሳለ ባንቺ ከከበረ
ማረኝ አምላኬ እያልኩ እሰማሽ ነበረ

         እባክሽ🥺
ድንገት እንኳ አንዴ
      ቢቻል ድምፅ'ን መሳም
ከከንፈርሽ ሲደርስ
       እኔም አንዴ ልሳም።


        @henila31

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ጠንካራ መስያት ነው ። የምታየው ብቻ መስያት ነው ። ለሷ ያለኝ ቦታ ያሳየኋት እና የነገርኳት ብቻ መስሏት ነው።

ሌላም ሰው እኔ ያልኳትን ብሏት ዋሽቷት ስላገኘችው፤ ቃልም፣ ተግባርም  ማመን አቁማ ነው ።

ስታገኘኝ 'Dead inside' የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት  መልበሴን አላስታወሰችውም ።ሳቄ የቲሸርቴን መልዕክት ከልሎት ነበር ።

የማያቁኝ፣  ያልሰሙኝ  የሰጡአት አስተያየት ልቧን ተጭኖት ነው ። የተሰበረ ሁሉ የሚጠገን መስሏት ነው ። ጊዜ ሁሌ አዳኝ መስሏት ነው ። 

ከልጅነቴ ጀምሮ የሚራራልኝ አልነበረም!!

ልጅ እያለሁ:-

አባቴ ይወደኝ ነበር ። አንድ ነገር ሳይዝልኝ ቤት አይገባም ፣ ሳያጫውተኝ አይተኛም። መንገድ ስንሄድ እሽኮኮ ያደርገኝ ነበር ። ላገኘው ሁሉ "ልጄ ነው"  ይል ነበር።  ዘና ያለ ነው ፣ ሙዚቃ  ይወዳል፣ ተጫዋችም፣ ዝምተኛም ፣ ሳቂታም፣  ኮስታራም  ነበር ።

ከእናቴ ጋር  ብዙ ግዜ ቢጨቃጨቁም ፤ ሁለቱም  ይወዱኝ ነበር ። ፍቅር አሰጣጣቸው ለየቅል ነው ። ሰው ለሚወደው  የሚሰጠው የሚችለውን ሁሉ ነው ።

የሆነ ቀን ፀባቸው ከሮ ፍርድቤት ቆሙ ። ይዘውኝ ሄዱ።  የሚያወሩት ስለ መለያየት፣ ስለተቆራጭ ምናምን ነበር።

አይን አይኔን እያየ "አላምናትም፤ ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም" አለ ። አላመንኩም : ውሸቴን ነው ይላል ብዬ ጠበኩት ህይወት እንደዚ አይነት ቀልድ እንደማታውቅ አላቅም ነበር ።

ልጄ አይደለም ካለኝ በኋላ የተወራውን መስማት አልተቻለኝም ።

"ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም " ያለው   ፊቱ ፣ ሁኔታው ድምፁ ፤ እርግጠኝነቱ ከልቤ አልጠፋ አለ።
እናቴ  እጄን ይዛ ወደ ቤት ተመለስን ።

አደባባይ ላይ "ልጄ አይደለም" ያለኝ ከሰጠኝ ፍቅር ሁላ ስለበለጠብኝ ውስጤ ደነገጠብኝ ።
   
የሚታይ ነው የሚሰማ መታመን ያለበት ??

ለምን ይዘውኝ ሄዱ ? ፣ እማኝ ባለበት ስካድ ማየት እኔን ከማበላሸት ውጪ ምን ይጠቅማል ?? ያን ቀን አባት አልባ ሆኜ ተመለስኩ ።

ዘግኖ ባዶ ማግኘት ህይወት ውስጥ አዲስ አይደለም !!
       © Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


❤ስንት ሰዎች አሉ!❤

ህይወት ስታጓጓን ..
ደንገት ሞት እንዳለ እየተዘናጋን
ጊዜ ነፍገናቸው ..
ንፁህ ፍቅራችንን ፍፁም ያልታደሉ
ስንት ሰዎች አሉ።
ቆርጦ የመጣ ቀን ማለፋችን ላይቀር
ምንድነው ጥላቻ ሁሌም እንፋቀር።

✍️ዘሪሁን ከ አሰላ
ታህሳስ 24/2017

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


✅Telegram Premium እና Telegram Stars የምትፈልጉ ካላችሁ @yoni1639 አናግሩን።


ለካ
.
እንባ ቢያስመስል ፈሪ
ደፋርነው ባሉት ይብሳል፣
ካገኜ አቅፎ 'ሚያባብል
ጀግናም ከልቡ ያለቅሳል።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


የማርያም ትህትና

በቅድስናዬ፤
በድንግልናዬ፤
መች አለች መረጠኝ ፥ ንጽሕናዬን ዓይቶ
የባርያውን ውርደት ፥ እንጂ ተመልክቶ።

የዘላለም ንጉስ
እውነተኛ ፀሐይ ፥ ክርስቶስን ይዛ
የጨረቃን እናት ፥ አየቻት ተጉዛ
ብትመሰገንም ፥ ቢጨምርም ክብሯ
ድንግል አትታበይ ፥ እንደ ሰው አትኮራ
ድምጿም አይሰማ ፥ እዩኝ እዪኝ አትል
ያደገችው መቅደስ ፥ ሀር ስትፈትል
እንደ ልጅ ቦርቃ ፥ መች ታውቃለች ድንግል።

ለልጇ ሲዘመር ፥ ሲባል ሆሳዕና
ልመስገን ልወደስ ፥ እናቱ ነኝና
ነቅላቹ አምጡልኝ ፥ የዛፎቹን ላባ
መች ይነጠፍልኝ ፥ ብላለች ዘንባባ።
በምን ቋንቋ ብንፅፍ ፥ በምን መዝገበ ቃል
የሷን ትህትና ፥ ለመግለጽ ይበቃል ።

እንደሷም ከፍጡር
እንደሷም በዓለም
ከሁሉ ከፍ ያለ ፥ ፃድቅ እንደሌለም
እንደሷም ከፍጡር
እንደሷም በዓለም
ራሱን ዝቅ ያረገ ፥ ትሑት ማንም የለም።

✍አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

5k 0 34 5 76

የኔና ያንቺ ህይወት
━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት...
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት....

እውነት እውነት ስልሽ...
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።

                        ✍️-ዳዊት(የለትዬ ልጅ)
                            

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


BUMS Daily Combo

ወደ CITY የሚለው ቦታ ትገባላችሁ ከዛም LOTTERY ውስጥ ትገቡና ምስሉ ላይ ታሉትን combo መርጣችሁ check ማለት ነው።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1


ብታውቂ ነይ ከእኔ...
ባታውቂ ነይ ወደ እኔ...
             (ርዕሱ ነው)


ከውቢት ከተማ አንዲት ሴት ነበረች፣
ሁሉ የሚመኛት በግብር ያማረች፤
                    አንዲት ሴት ነበረች።

ከሴቶቹ መሃል ትመስላለች ንግሥት፣
ብቻዋን ስትገኝ ታስንቃለች እንስት።

ውዴ! ከእግዜሬ በታች የዓሳ ሕይወት ያለው፣
በሠማዩ ሥሪት፣ በምድር በሰፋው በሚታየው ማይ ነው።
ታድያ የእኔ ልብ ያለው አንቺ ጋር ነውና፣
ወይ ነይልኝ ወይ ና በይኝ እወድሻለሁና።

አውቃለሁ! ዓይን ዓይንሽ እያየሁ ፍቅሬን አልገለጥኩም፣
አውቃለሁ! እሞትልሻለሁ ብዬ አልተናገርኩም፣
ታውቂያለሽ? ኃይል ማጣቴና እንደሆንኩኝ ድኩም?

አላምንህም ብለሽ ብትዞሪ ዓለም፣
እመኚኝ! ከአፍቃሪሽ በላይ ላ'ንቺ 'ሚሆን የለም።
ብታውቂ ነይ ከእኔ ጋር ድመቂ፣
ባታውቂም ነይ ወደ'ኔ ከጎኔ አትራቂ።
ላገኝሽ እተጋለሁ...፣
ደግሞ እንዳትርቂኝ እሰጋለሁ።

አሰብኩትና ለአንቺ መንበርከኬን ... ፈራሁት አምላኬን
አትታዘበኝ ጌታዬ ... አንተም ታ'ቃለህ ከፍቅር ለፍቅር መላኬን።
በእርግጥ አንተ ለእኔ ምላሽ አለህ፣
አንተ ራሱ አፍቃሪ አይደለህ?

አስታውሽ? ሳጥናኤል በምኞት መውደቁ፣
ከንቱነት ለእሱ ማሳበቁ፣
    እናማ...
የእኔም ምኞት አውጥቶ ቢጥለኝ፣
የአንቺ እሺታ እንጅ ሌላ መጽናኛ የለኝ።
ግዴለም ሐሳብሽ ሐሳቤ ይሁን፣
ልዕልት ላግባና እኔም ንጉሥ ልሁን።
አትፍሪኝ፣ ቅረቢኝ...
ዓይንሽን ግለጭ፣ አንብቢኝ።
የፍቅረኛሞች ሰፈር ውሰጂኝ፣ አድርሺኝ፤
ጠይቂኝ ልቤን ልስጥሽ ከዚያም አድሺኝ።

ይኸውልሽ ሃ!   የእኔ ስኬት...
አንቺን ማኖር ነው ወሰን በሌለው ልኬት!
           ●| HT |●

✍ መንገደኛው (
@MekuriyaM )
            The traveler

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


Jawar Mehhamed Altsetsetim አልፀፀትም @kooblife.pdf
10.6Mb
━━━━━━✦✗✦━━━━━━

አልፀፀትም

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

✏️ደራሲ:- ጀዋር መሀመድ

✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️✍️
✈️ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ!! ✈️

@booklibrarychannel

✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️✍️


"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው" አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ"
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?' አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

ይልቅ እንጠጣ እስኪ።
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


Zoo

Rebus of the Day:
Tapir
Riddle of the Day:
Parrot

👇👇👇👇

🔗 LINK

ከአሁኑ ጀምሩ !

@DropGenius1


ከሷ ጋ ተቃጥረናል የምቶደው ገጣሚ ዛሬ ግጥም ያቀርባል። ለሁለታችንም ትኬት ቆርጬ ከአዳራሹ ደጃፍ ቆምያለው አላፊ አግዳሚውን እየተመለከተኹ።

እሷን የምትመስል ሴት ሳይ ፊቴ ይፈካና እሷ አለመሆኗን ሳረጋግጥ ሰአቴን አያለው ግጥሙ ሊቀርብ ሽራፊ ደቂቃዎች ቀርተውታል አልመጣችም።

ደቂቃዎች አለፉ።

ከውስጥ የጭብጨባ ድምፅ ሰማው ዝግጅቱ ተጀምሯል። የሚመጣው ሰው እየቀነሰ....እየቀነሰ ሄደ... ምንገጥሟት ይሆን በመንገዷ ምንችግር ገጠማት እልና ደግሞ ቀርታስ ቢሆን ትታኝ ሄዳ ቢሆንስ እላለው በብዙ ሀሳብ ውስጥ ተዘፈቅኹ በመሀል ከአዳራሹ የገጣሚው ድምፅ በስሱ ይሰማኝ ጀመር...

ያማል


እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም

አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ

እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ

እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን
ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣ ልበል?

ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት
እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል

እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን !
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ

ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል ።

ግጥሙ ሀሳቤን ገዝቶት ከአዳራሹ ተጠግቼ አዳምጬ እንደጨረስኹ ስልኬ ላይ መልክት ደረሰኝ...

✍️ Nat

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


መንገድ ጠፍቶን ስንደናበር ላረጋጉን ፣ ወደቅን ስንላቸው ላልፈረዱብን ። በድለናቸው ይቅርታን ለሰጡን ፦

ሚስጥራቸውን ላጋሩን፣ ደስታችን ለተካፈሉ፣ ሃዘናችንን ቦታ ለሰጡት ፣ ለተጠነቀቁልን ፣አጋርነታቸው ወረት ለሌለበት ፣ በቆሚነት የኛ ለሆኑ ።

እንድናምናቸው ለሆኑ ፣ ደግነታቸው ለማይስተን ፣ ለሚወዱን ፣ ሊረዱን ግማሽ መንገድ ለሚመጡ ፣ ለሚያበረቱን

ችርስ ለነሱ 🙏

ኑሩልን ❤

©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

20 last posts shown.