ጠንካራ መስያት ነው ። የምታየው ብቻ መስያት ነው ። ለሷ ያለኝ ቦታ ያሳየኋት እና የነገርኳት ብቻ መስሏት ነው።
ሌላም ሰው እኔ ያልኳትን ብሏት ዋሽቷት ስላገኘችው፤ ቃልም፣ ተግባርም ማመን አቁማ ነው ።
ስታገኘኝ 'Dead inside' የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት መልበሴን አላስታወሰችውም ።ሳቄ የቲሸርቴን መልዕክት ከልሎት ነበር ።
የማያቁኝ፣ ያልሰሙኝ የሰጡአት አስተያየት ልቧን ተጭኖት ነው ። የተሰበረ ሁሉ የሚጠገን መስሏት ነው ። ጊዜ ሁሌ አዳኝ መስሏት ነው ።
ከልጅነቴ ጀምሮ የሚራራልኝ አልነበረም!!
ልጅ እያለሁ:-
አባቴ ይወደኝ ነበር ። አንድ ነገር ሳይዝልኝ ቤት አይገባም ፣ ሳያጫውተኝ አይተኛም። መንገድ ስንሄድ እሽኮኮ ያደርገኝ ነበር ። ላገኘው ሁሉ "ልጄ ነው" ይል ነበር። ዘና ያለ ነው ፣ ሙዚቃ ይወዳል፣ ተጫዋችም፣ ዝምተኛም ፣ ሳቂታም፣ ኮስታራም ነበር ።
ከእናቴ ጋር ብዙ ግዜ ቢጨቃጨቁም ፤ ሁለቱም ይወዱኝ ነበር ። ፍቅር አሰጣጣቸው ለየቅል ነው ። ሰው ለሚወደው የሚሰጠው የሚችለውን ሁሉ ነው ።
የሆነ ቀን ፀባቸው ከሮ ፍርድቤት ቆሙ ። ይዘውኝ ሄዱ። የሚያወሩት ስለ መለያየት፣ ስለተቆራጭ ምናምን ነበር።
አይን አይኔን እያየ "አላምናትም፤ ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም" አለ ። አላመንኩም : ውሸቴን ነው ይላል ብዬ ጠበኩት ህይወት እንደዚ አይነት ቀልድ እንደማታውቅ አላቅም ነበር ።
ልጄ አይደለም ካለኝ በኋላ የተወራውን መስማት አልተቻለኝም ።
"ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም " ያለው ፊቱ ፣ ሁኔታው ድምፁ ፤ እርግጠኝነቱ ከልቤ አልጠፋ አለ።
እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤት ተመለስን ።
አደባባይ ላይ "ልጄ አይደለም" ያለኝ ከሰጠኝ ፍቅር ሁላ ስለበለጠብኝ ውስጤ ደነገጠብኝ ።
የሚታይ ነው የሚሰማ መታመን ያለበት ??
ለምን ይዘውኝ ሄዱ ? ፣ እማኝ ባለበት ስካድ ማየት እኔን ከማበላሸት ውጪ ምን ይጠቅማል ?? ያን ቀን አባት አልባ ሆኜ ተመለስኩ ።
ዘግኖ ባዶ ማግኘት ህይወት ውስጥ አዲስ አይደለም !!
© Adhanom Mitiku
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19