ሌላ ሴት አሳዩን
ፈጣሪዋን ወልዳ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ጡቶቿን የጠባ
ማርያም ማርያም ፥ አንበል ነጋጠባ ።
አምላኳን ታቅፋ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ በእጆቿ መሐል
በማርያም ተገርመን ፥ ተደንቀን አንዋል።
ፈጣሪዋ የነሳው ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ከእሷ ሥጋና ነብስ
ማርያምን ከንግዲ ፥ እናቁም ማወደስ።
እናንተ ምታቋት ፥
ያለዘር ፀንሳ ፥ ቃሉን ብቻ ሰምታ
የድንግልናዋ ፥ ማህተም ሳይፈታ
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ካለች ያያችሁት
ማርያምን ማመስገን ፥ እንተው እንዳላችሁት ።
✍ አቤል ታደለ
ለአስተያየት : @abeltadele
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ፈጣሪዋን ወልዳ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ጡቶቿን የጠባ
ማርያም ማርያም ፥ አንበል ነጋጠባ ።
አምላኳን ታቅፋ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ በእጆቿ መሐል
በማርያም ተገርመን ፥ ተደንቀን አንዋል።
ፈጣሪዋ የነሳው ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ከእሷ ሥጋና ነብስ
ማርያምን ከንግዲ ፥ እናቁም ማወደስ።
እናንተ ምታቋት ፥
ያለዘር ፀንሳ ፥ ቃሉን ብቻ ሰምታ
የድንግልናዋ ፥ ማህተም ሳይፈታ
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ካለች ያያችሁት
ማርያምን ማመስገን ፥ እንተው እንዳላችሁት ።
✍ አቤል ታደለ
ለአስተያየት : @abeltadele
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19