Video is unavailable for watching
Show in Telegram
መሬት መንቀጥቀጡ በፈንታሌ ተራራ ፍንዳታ አስከትሏል
በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡
በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛውና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎም ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት ማሳየቱን ነው ያስረዱት፡፡
በአካባቢው የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው÷ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር በኩላቸው÷ዛሬ ከሰዓት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው ብለዋል፡፡
በመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ እና ጭስ መታየቱም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡
መረጃው የፋና ዲጅታል ነው