ለህክምና ገብተው የሚያክሞት ሮቦት ነው ቢባሉ ይስማሙ ይሆን?
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ሳንድራ ሱልትዘር የተሰኘች እንስት በፍሎሪዳ የምትኖር የአንጀት ህመም ተሰምቷል ነበር ወደ ሆስፒታል ያመራችው፡፡
በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የቀዶ ጥገና ሮቦት ሐኪም ደግሞ ሳንድራን እንዲያክም ሀላፊነት ተሰጥቶት ነበር ይላል የኒዮርክፖስት ዘገባ፡፡
ይህ ሮቦት ሐኪምም ሳንድራን የአንጀት ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጣት እያለ በፈጸመው የሕክምና ስህተት ህይወቷ አልፏል ተብሏል፡፡
ሮቦት ሐኪሙ በሳንድራ ቀጭን አንጀት ላይ በፈጸመው ስህተት ምክንያት ለሞት ተዳርጋለች የተባለ ሲሆን ክሱ በባሏ እንደተመሰረተ ተገልጿል፡፡
የቤት ውስጥ ስራን ጥንቅቅ አድሮ የሚሰራው “ሮቦት የቤት ሰራተኛ”
ይህን ሮቦት ሰርቶ ለሆስፒታሉ የሸጠው ዳቪንቼ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ክሱ ተመስርቶበታል የተባለ ሲሆን ሮቦቱ ለሰራው ቸልተኝነት እና ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ወደ አገልግሎት በማስገባት ካሳ እንዲከፍልም ተጠይቋል፡፡
ሮቦቱ በታካሚዋ ላይ የህክምና ስህተት እንደፈጸመ ኩባንያው ያውቅ ነበር የተባለ ሲሆን ይህን አውቆ ታካማዊ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ተጨማሪ ህክምና እንድትወስድ ለሆስፒታሉም ሆነ ለታካሚዋ አላሳወቀምም ተብሏል፡፡
ሮቦቱ የቀዶ ጥገናውን ሲያከናውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቅሟል የተባለ ሲሆን በዚህ ምክንት ቀጭን አንጀቷ ላይ የከፋ ጉዳት እንዲደርስባት ማድረጉን ኩባንያው እያወቀ ሀላፊነቱን እንዳልተወጣ ተገልጿልh