የሰሜን ኮሪያ መረጃ መንታፊዎች በ2024 1.3 ቢሊየን ዶላር የክሪፕቶ ገንዘብ እንደዘረፉ የምርመራ ውጤት አጋለጠ
በአጠቃላይ በ2024 የዲጂታል ገንዘብ ስርቆት በ21 በመቶ ጨምሮ ታይቷል
በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው የፈረንጆቹ 2024 አመት የሰሜን ኮሪያ መረጃ መንታፊዎች ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ “የክሪፕቶ ከረንሲ” ገንዘብ መዝረፋቸውን የጥናት ውጤት አመላክቷል፡፡
“ቼይን አናሊሲስ” የተባለው የጥናት ተቋም ባደረገው ጥናት ከፒዮንግያንግ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው መረጃ መንታፊዎች (ሀከሮች) በ2023 ከዘረፉት ገንዘብ በእጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ በ2024 መዝረፋቸውን ገልጿል፡፡
ስርቆቱ አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ምዕራባውያን ሀገራት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን መንታፊዎቹ የክሪፕቶ እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አሳጥተዋል፡፡
የትራምፕ መመረጥን ተከትሎ ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች የዲጂታል ገንዘቦች ዋጋ መጨመር የመረጃ መንታፊዎቹ የወሰዱት ገንዘብ መጠን እንዲያድግ ስለማድረጉ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ባለፈም የዲጂታል ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ሰዎች የይለፍ ቃሎች እና የደህንነት መጠበቂያዎች ደካማ መሆን ለስርቆቱ ማደግ ተጨማሪ ምክንያት ነው፡፡
በአጠቃላይ በ2024 በመረጃ መንታፊዎች የተሰረቀው የክሪፕቶ ገንዘብ ከ2023 ጋር ሲነጻጸር በ21 በመቶ የጨመረ ቢሆንም ከ2021 እና 2022 አመት አኳያ ሲወዳደር ግን ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ አመት ካጋጠሙ ዋና ዋና ክስተቶች መካከል ከጃፓኑ ዲኤምኤም የክሪፕቶ ኩባንያ የተሰረቀው 300 ሚሊየን ዶላር እና ከህንዱ ዋዚርኤክስ የተወሰደው 235 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
#Share_x5
#Join
@bunatech
@bunatechdiscussion