አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የዮሐንስ ራዕይ 22፥11-14
«ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እንሆ፥ በቶሎ እመጣለኹ፥ለያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋራ አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ፊተኛውና ዃለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
➘➘➘
@christian930
ግሩፕ፦ @AlphaOmega930
📩☞ @Kyrieelesion

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter






📌ማስታወሻ
➖ ➖ ➖
ክፉ ትውልድ እንዲህ ይላል እስከ ዛሬ ለ18 ዓመት ለፍልፋችኋል የምትመኩበት አምላክ እስከ ዛሬ መቸ መጣ :ምንስ አደረገን:እናንተ ትጮሃላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ ፍርድ ትላላችሁ ጆሮአችን እስከሚታክተው ሰማናችሁ ምንም የሚመጣ የለም።እኛም ለሥልጣኔአችንም ስለሥልጣኔአችንም ጉልበታችንም ሀብታችንም በዓለም የዘረጋነው ሥርዓታችንም ሁሉ አንዳች የሚነካው የለም።የእናንተን ሥላሴ: የእናንተን መድኃኔዓለም: የእናንተን ማርያም:የእናንተን መልአክ:የእናንተን ቅዱሳን ታሪክም ገድልም ሁሉንም አናውቃቸውም ።ግብረሰዶምነት መብታችን ነው ዓለምንም ሁሉ ከድኗል የምንሻውን ከመፈጸም የሚያግደን የለም።ዘወር በሉ አናውቃችሁም ብላችሁ ቁማችኋል ዲያብሎስን ታምናችኋል አምላካችሁ አድርጋችሁታል ፤በአዘዛችሁም ቁማችኋል ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋል።ልብ በሉ ምስክሩ እኛም ነንን ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ :ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ እንግዲህ እውነቱ ይለያል።እኛ የሥላሴ ባሮች: የድንግልም ልጆች:የሊቀ መላእክቱም ወዳጆች የቅዱሳንም ፍሬዎች የታመንበት አምላክ የአብርሃሙ ሥላሴ በእኛ አንደበት እንደተናገረው እንደ መልዕክቱ አገላለጽ :እንደ ደብዳቤዎቹ አገላለጽ:እንደ መግለጫዎቹ እንደ ትምህርቶቹ እውነትነት:የእኛም ታማኝ አገልጋይነት ይታወቅና እና ይገለጽ ዘንድ እግዚአብሔር በታላቅ የበቀልና የፍርድ ሂደት በታላቅ ቁጣ ትቢያ ሊያደርጋችሁ ደርሷል በደጃችሁም ነው።
ከዲያብሎስ የታጠቃችሁትን ትዕቢታችሁ ክህደታችሁ ንቀታችሁ እኒህ ሁሉ በምድር እንደጸኑ ያኖሯችኋል እንደሆነ እነሆ ልናይ ነው።የእኛ አምላክ ስለባሮቹ ስለቃሉ ስለትዕዛዙ ስለሥርዓቱ ሲል በቅናት እና በቁጣ ካልተነሳ እርምጃውንም በማትገምቱት በማታስቡት መልኩ ይዞት ካልመጣ በእርግጥ እንዳላችሁት እኛ አምላክ የለንም ውሸታም ነንን ማለት ነው።
ስለዚህ የእናንተ አምላክ ከእግዚአብሔር ታግሎ ከአሸነፈ እኛም ተሸንፈናል ማለት ነው።እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ ተዘርግቷል ሁሉንም እናየዋለን።ሲድራቅ: ሚሳቅ :አቢዲናጎምን ከእሳት ያወጣው አምላካችን: በእርግጥ ለአምላክነቱ: ለስሙ: ለክብሩ: ለፈቃዱ ቀናይነቱን ለልጆቹ ፈራጅነቱም በግልጽና በማትክዱበት መልኩ ሲውጣችሁ ተረት ብላችሁ የናቃችሁት ቃሉ ሲተገበርባችሁ አይ ተሳስተናል ማሩን እ ከልሉን አስጥሉን ማለት የለም።የለም የለም።መዳንም የለም።ከእነ ክህደትህ ከእነ ትዕቢትህ ሰዶሞን የበላው እሳት በሺ እጥፍ ተባዝቶ ይበላሃል።ፌዝህ ንቀትህ ያድንህ በቃ እሱኑ ተማመን ።ያ የተማመንህበት ዲያብሎስ እሱ ያድንህ በቃ።
ያሳደድኸን የገደልኸን የአሰርኸን እኛ የልዑልም የድንግልም ታማኝ ባሮች ብትጮህ ብታቅራራ ሺ ጊዜ ብትኳትን ከእንግዲህ አታገኜንም ለአንዴም ለመጨረሻም ተሰነባብተንሃል።
➖ ➖ ➖
📌የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በእምነታችሁ ጽናት በምክር መስማታችሁ ምክንያት አሸናፊ ሁናችኋል።ዓለምን አሸንፋችኋል። ኮንናችሁታል ታገሱ በጾም በጸሎት ትጉ።ለእኛም ደካማ አገልጋዮቻችሁ ጌታ ምሕረቱን :ቸርነቱን :ፀጋውን አብዝቶልን በትህትና እንድናገለግላችሁ ፀልዩልን።

📌ክርስቲያን መሠል አስመሳዮች ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን የምታመልኩ ወዮላችሁ! የሚገርም ክርስቲያን ተብየ ምዕመን ፡በተለይ ሴቶች አንድ ሊቅ ነኝ ሊቃውንት ነኝ የሚሉ እግር ስር ወድቃ አባቴ በእርስዎ እግር ሥር በመባረኬ እጅግ ተደስቻለሁ ብላ እንደ ምሳሌ በማሕበራዊ ሚዲያ ስታስተጋባ ሰማናት።እሺ አምላክስ መቼ ነው እግሩ ስር ወድቀሽ የሚባርክሽ እ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰው የሰጠሽ አባት ተብዮች ያጠፉሽ ከንቱ ትባያለሽ።እንደ እሷ መሰል የሆናችሁ ሁሉ ከንቱ ተብላችሁ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ።
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ከወጣው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ከ46 እስከ 51 ደቂቃ ላይ የተወሰደ።
22/02/2017 ዓ.ም


🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ፍርድ አዘል መግለጫ
21/02/2017 ዓ.ም




🇨🇬 ልዩ ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20
20/02/2017 ዓ.ም




Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🟢 🟡 🔴
  ኢትዮጵያ
➖ ➖ ➖
ርስተ ድንግል ማርያም

ጌታችንም ክብርት «...እናቱን በማያልፈው በአባቴ መንግሥት በሕያዋንና በሙታን ልፈርድ ዳግመኛ ወደዚህ ዓለም እስክመጣ ድረስ ርስት ይሁንልሽ» -ድርሳነ ቁስቋም ማርያም

እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወድዳቸዋለች፣ ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡
-ገድለ ዮሴፍ አረጋዊ፣ ተአምረ ማርያም


Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
◦◆◦
እውነተኞቹ ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆችና መጪው ዕጣቸው
◦◆◦

ቀንና ጊዜ ባለፈ ቁጥር ሥጋ ለባሽ በመከራ ክብደት ይደክማል፡፡ ኃያል ጌታ ግን ለበረከቱ፣ ለምሕረቱ ያተማቸውን ልጆቹን ያጸናል፡፡ የሰጠውን ( የገባውን) ቃል ኪዳን ያከብራል፡፡

ሰው በድካም ዝሎ የተገባለትን ተስፋ ሁሉ ይተዋል፡፡ በብርቱ ድካም ዝሎ ይወድቃል፡፡ ልዑል ግን ያኔ ድካሙን ሁሉ ከድኖ፣ አድሶ፣ በብርታት ሞልቶ በደስታ እንዲቦርቅ ያደርገዋል፡፡

የታመንበት የሠራዊት ጌታ ሁሌም እስከ ዘለዓለሙ የታመነ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅሩ፣ መታደጉ፣ በረከቱ ልቡን የሞላው ዳዊት እንዲሁ አለ፦

እግዚአብሔር ወገኖቹን እንደ አይን ብሌን ይጠብቃቸዋል፡፡ በማንኛውም የዲያበሎስ ዘዴ ይወድቁና ይጠፉ ዘንድ በፍፁም አይፈቅድም፡፡

ወገኔ የልዑል ልጅ፤ የቅዱሳን የከበሩት መላእክት ልጆች ብዙ ብትሰቃዩም ይድረሳችሁ የተገባችሁን ነጭ ልብስ ለበሳችሁ፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ልዑል ዙፋኑን የሚዘረጋባት፣ ልጆቹን እንቁዎቹን በዙፋኑ የሚያኖርባት፣ ድንግል ልጆችዋን በበረከቷ፣ በፍቅሯ የምታረሰርሳት፣ ኢትዮጵያ ቅዱሳን የከበሩት መላእክት ዙሪያዋን በእሳት አጥረው የሚጠብቁአት፣ የሚባርኳት ኢትዮጵያ፣ የፀናችው አንዲቷ የተዋሕዶ እምነት እንደፀሐይ የምታበራባት ኢትዮጵያ ለልዑል የሰራዊት ጌታ ሌትም ቀንም ለክብሩ ለስሙ ምስጋና እንደጅረት የሚፈስባት ድንግልና ቅዱሳን የከበሩት መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማእታት፣ ነቢያት፣ሐዋርያት፣ ስማቸው የሚከብርባት፣ የሚመሰገኑባት ኢትዮጵያ በክብሯ ጥግ ማንም የማይደርስባት የእግዚአብሔር የስስት ልጁ ናት፡፡

ከዚህ ድንቅ አገር የተፈጠራችሁ፣ ለአባታችሁ ለልዑል፣ ለእንቁዋ ለአገራችሁ ኢትዮጵያ ዋጋ ከፍላችሁ በጭንቅ እዚህ ለደረሳችሁ ወገኖቼ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በእምነት ድሉን ተቀዳጅታችኋልና!

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5




ታላቁ ጻድቅ አባ ዘወንጌል ዘኢትዮጵያ አመታዊ መታሰቢያ ቀን ዛሬ ጥቅምት 10 ነው ።

እንኳን ለታላቁ አባታችን አባ ዘወንጌል ዘኢትዮጵያ 5ኛ አመት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ። የአባታች በረከት ረድኤት በሁላችንም ላይ ይደርብን።

ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል 1 (ቅድስት በርባራ)
#በድምፅ_ንባብ

🌹 ቅድስት በርባራ ማናት?
🌹 ቃልኪዳኗስ?
🌹 ዐበይት በዓላቶቿስ መቼ ይታሰባሉ?

🫴 እኒህን ጥያቄዎች፦
በስሟ የምንማጸን፤ በስሟ ጽዋ የምንቃመስ፤ ዝክሯን የምናዘክርና በዓላቶቿን የምናከብር ቤተሰቦች ልናውቅ ይገባል።


📌 በጽሑፍ ለማግኘት ይሄንን ባለቀለም ጽሑፍ ይጫኑ !

ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡

ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡

የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


🫴🌹 የአባት ምክር ለልጆች!

የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ክፍል 7ለ ላይ ካለው የተወሰደ!


Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🇨🇬 ደብረ ማርቆስም በድጋሚ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ሰማዩ ለኢትዮጵያ መስክሯል !!!


🇨🇬 ሸዋ እንሳሮ ዛሬ በቀን ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም የሰማዩ አምላክ ምስክርነት ሰጥቷል።

t.me/Ewnet1Nat




🌹 «አዘክሪ ድንግል አንብዓ መሪረ፤ ዘውኅዘ እምአዕይንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ።

ድንግል ሆይ ከዓይንሽ የፈሰሰውን በልጅሽ ፊት የወረደውን ቁጡ እንባ አሳስቢ»


በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤

የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።

ደቀ መዛሙርቱም፦ የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።

የዮሐንስ ወንጌል 2፥14-17




Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
"...የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል!፦ ኢትዮጵያ እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ ከተሞችዋም ሁሉ የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ። የቤቱም ፍርስራሽ ሁሉ እንደ ዱር ከፍታና ተራራ ይሆናል ብሎ ተናገረ።

አዲስ አበባ በይ አይዞሽ! ፎቅሽን ቶሎ ቶሎ ሥሪ፤ ሰማይ ጠቀስ አድራጊው። አይ ፎቅ! አይ ሪል ስቴት! አይ ኮንዶሚኒየም ቤት! ኦሮሞ ሊኖርብህ ሕዝብን የሚያስቸግርብህ፥ የቤቱ ባለቤት የሆነው ደግሞ ድሃውን ስደተኛ ተከራይ ሁሉ የሚዘርፍብህና የሚያስለቅስብህ፤ መንግሥት ተብየው ደግሞ ለራሱ ጥቅም ሲል ገበሬውን ከመሬቱ ነዋሪውን ሕዝብ ከመኖሪያው እያፈናቀለ የሚያሰፍርብህ። ሕዝቡም ቢሆን ሃብታሙም ሁሉ በማጭበርበር ያለው አልበቃው ብሎት፥ ድሀው ደግሞ መኖሪያ በማጣት በማልቀስ የሚስገበገብብህ፤ እንኳን ደስ አለህ ልበልህ!? ወይንስ እግዚአብሔር ያጽናናህ ልበልህ? እንደ እድልህ። ወይ ቆመህ የወፎችና የአይጦች፤ የአራዊት መኖሪያ ልትሆን ነውና ወይንም ፈርሰህ ፈራርሰህ የድንጋይ ክምር ልትሆን ነውና። ለነገሩ ግን ከፈረስህ እንኳ ቆይተሀል። ገና እየሰሩህና እንደሰሩህ አይደል የምትፈርስ።..."

➩ ከአባ አምኃ ኢየሱስ ገብረዮሐንስ ፪ኛ አገራዊ መልእክት የተወሰደ!
t.me/christian930

20 last posts shown.