Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🟩 🟨 🟥
ኢትዮጵያ
የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር!
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም!
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን!
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ!
🍀 ዓቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ | ጾመ ሁዳድ ] 🍀
ዓቢይ ማለት «ዐብየ - ከፍ አለ» ከሚለው ግሥ የተገኘ ሲሆን #ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፦
[ሀ] ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ፣
[ለ] በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ፣
[ሐ] ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ➻ #ትዕቢት፣ #ስስት፣ #ፍቅረ_ንዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
❗️ “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ (እስከ 12 ሰዓት) ይጹሙ! ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ! በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ (ምሽት 1 ሰዓት ድረስ) ይጹሙ!” ይላል (ፍት.ነገ.አን 15፥595)❗️
በቤተክርስቲያን ስያሜ መሠረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፦
1. ዘወረደ
2. ቅድስት
3. ምኩራብ
4. መጻጉዕ
5. ደብረ ዘይት
6. ገብርኄር
7. ኒቆዲሞስ
8. ሆሳዕና ይባላሉ።
#እንኳን_አደረሳችሁ፤ #እንኳን_አደረሰን !
ልዑል እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን ንስሐ ገብተን፣ በእውነት ጾመን ከፈቃዱ ጋር የምንታረቅበት፥ የኢትዮጵያና የተዋሕዶን ትንሣኤ የሚረጋገጥበት ያድርግልን። ፍርዱን አጽንቶ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን፤ ጾመን ለማበርከት ያብቃን አሜን።
[ይጹም ልሳን ፤ ይጹም ዓይን ፤ ይጹም እዝን]
አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
t.me/AlphaOmega930
http://t.me/Ewnet1Nat