የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ ከሚገኙ በወጪ ንግድ ጋር ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያየ።
በዲስትሪክቱም የምስጋና እና ዕዉቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
*************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ቅርንጫፍ የደንበኞችን ወር ምክንያት በማድረግ በዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ የሀገር ዉስጥ እና ለዉጭ ባለሀብቶች የምስጋና እና ዕዉቅና ሰርተፍኬት በዲስትሪክቱ ዳይሬክተር እና በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጂ እጅ ተበርክቶላቸዋል::
በዚህም መርሃ ግብር ላይ ከደንበኞች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የጋራ የዉይይት መድረክ የነበረ ሲሆን በዚህም ደንበኞቹ ከባንካችን ጋር ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበዉ ለመስራት ያላቸዉን ቁርጠኝነት የገለፁ ሲሆን ባለሀብቶቹ ከባንኩ ጋር ላላቸዉ ግኑኝነት በዲስትሪክት ዳይሬክተሩ አቶ ወዬሳ ጥላሁን ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም ባንካችን ለደንበኞቹ አሁን ካለዉ የላቀ እና ልዩ አገልግሎት ለመስጠት ቃል ገብተዉላቸዋል::
በተመሳሳይም የሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሀፒ ሀይሌ ለባለሀብቶቹ እና ለባለድርሻ አካላት ከባንካችን ጋር ላላቸዉ አብሮነት ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ ለቀጣይም አብሮነታዉቸዉን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ገልፀዉ፤ ቅርንጫፉም ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት “የላቀ አገልግሎት፤ ደስተኛ ደንበኛ” በሚል መርህ ከበፊቱ በልዩ ሁኔታ ለማቅረብ ቃል ገብተዋል::