ዲያቆን ወልደ ሰንበት መጣጥፎች ፣ ትምህርቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ መንፈሳዊ ቻናል ትምህርቶች ፣መጣጥፎችን ፣ወጎች የሚተላለፉበት ነው። እንዲሁም የበአላት ወረቦች ፣ምስባክ ያገኙበታል

ይህ ቻናል በባለቤቱ የተከፈተ ቻናል ነው

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌹ፀሐይ-ዘኢትዮጵያ-አቡነ ተክለሀይማኖት🌹

🥰እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለሀይማኖት የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ 🌹🙏🙏🙏

መልካም በአል

ሐሙስ ታህሳስ 24/4/2017


Forward from: ማኅበረ ቅዱስ ገብርኤል
​​​​

#ብሥራተ_ገብርኤል

➤ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ታህሳስ ፳፪ ብሥራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብሥራቱን የነገረበት ቀን ነው።

➤ እንዴት ብሥራቱንማ የነገራት መጋቢት ፳፱ ቀን ነው ካሉ ትክክል ነው፤ ብሥራቱን የነገራት መጋቢት ፳፱ ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ፫ ሰዓት ላይ ነው።

#ታዲያ_ዛሬ_ለምን_እናከብረዋለን?

➤ ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር በመሆኑ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት ሰሩ፦
➢ የመጋቢት ፳፯ ስቅለቱን ጥቅምት ፳፯ ቀን እንዲሁም
➢ የመጋቢት ፭ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍት ቀን ወደ ጥቅምት ፭ ቀን ዞሮ እንዲከበር አደረጉ፡፡
➢ የመጋቢት ፳፱ ብሥራቱን ደግሞ ታሕሳስ ፳፪ ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ #ደቅስዮስ ይባላል።

➢ በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ታአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡

➢ የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብሥራቱ መከበር አለበት ብሎ ሥርዓት ሰራ። አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ።
የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱም ታህሳስ ፳፪ በዛሬዋ ቀን ነው።

➢ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች።

➢ በተለይም በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡

#አብሳሪው_መላክ_ቅዱስ_ገብርኤል ለሁላችህን ብስራቱን ያሰማን ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡

#_ሰናይ__ቀን🙏

#ለመቀላቀል👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam






Forward from: ማኅበረ ቅዱስ ገብርኤል
🕊 † ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል † 🕊

- ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃናት አንዱ: በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ: በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና: ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ: ሠለስቱ ደቂቅን: ዳንኤልን: ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::+ከምንም በላይ ቤተ ክርስቲያን "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: የስሙ ትርጏሜ "አምላክ ወሰብእ-እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::
መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም ከእግዚአብሔር ተልኮ አብስሯታል::

- ቅዱስ ገብርኤል ዛሬ የብሥራቱ መታሰቢያና ዳናህ በተባለ ሃገር ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ነው::
"ገብርኤል ዜናዊ ምጽዓተ ክርስቶስ አንበሳ::
ለዛቲ በዓልከ በዘይትሌዓል ሞገሳ::
በዓለ ማርያም አንበረ ደቅስዮስ በርዕሳ::" እንዲል:: [አርኬ]

ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን : ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አዕምሮውን: ጥበቡን በልቡናችን አሳድሪብን::

 🕊

[  † ታሕሳስ ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ተአምረ ማርያም
፪. ቅዱስ ደቅስዮስ ጻድቅ
፫. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፬. ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ
፭. አባ አርኬላዎስ

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. አባ እንጦንስ
፫. አባ ዻውሊ የዋህ
፬. ቅዱስ ዮልዮስ
፭. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ

" የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው:: መንፈስ ግን አንድ ነው:: አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው:: ጌታም አንድ ነው. . . ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር . . . ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ: ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ . . . ይሰጠዋል::" [ ፩ቆሮ.፲፪፥፬ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


Forward from: ማኅበረ ቅዱስ ገብርኤል
🕊

[  ✞  እንኩዋን "ለተአምረ እግዝእትነ ማርያም": "ቅዱስ ደቅስዮስ": "ቅዱስ አንሰጣስዮስ" እና "ቅዱስ ገብርኤል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

---------------------------------------------

🕊  †  ተአምረ ማርያም  †  🕊

- "ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ [በላይ] : ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ [ሲፈጸም] ተአምር ይባላል::

- ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::

- እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ [ኦሪትን ተመልከት] እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ [፩ ነገሥት] እንደ ነበር ይታወቃል::

- እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: [ማቴ.፲፥፰, ፲፯፥፳, ማር.፲፮፥፲፯, ሉቃ.፲፥፲፯, ዮሐ.፲፬፥፲፪]

- እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: [ሐዋ.፫፥፮, ፭፥፩, ፭፥፲፪, ፰፥፮, ፱፥፴፫-፵፫, ፲፬፥፰, ፲፱፥፲፩]

- በተአምራት ብዛት ደግሞ ከጌታ ቀጥላ ድንግል እመ ብርሃን ትጠቀሳለች:: ዛሬም የምናስበው የእርሷን ተአምራት ነው::

- የእግዝእትነ ማርያም ሙሉ ሕይወቷ ተአምር ነው:: አበው:- "ድንግል ተአምራት ማድረግ የጀመረችው ገና ሳትወለድ ነው" ሲሉ የሚጸንባቸው ሰዎች አሉ:: ከአዳም ውድቀት በሁዋላ በእርሷ እንደሚድን "ሴቲቱ" [ዘፍ.፫፥፲፭] በሚል ከተነገረው በሁዋላ ድንግል በብዙ ተአምራት [በምሳሌ] ተገልጣለች::

- ለአብነት ያህልም እግዚአብሔር ኖኅን ከጥፋት ውሃ እንዲሁ ማዳን ሲችል ተአምራቱን በመርከብ ገለጠ:: [ዘፍ.፯፥፩] ለሚያስተውለው ያቺ መርከብ ናት ድንግል::

- አብርሃም ይስሐቅን ሊሰዋ ሲል በተአምራት በግ በእፀ ሳቤቅ ተይዞ ተገኝቷል:: [ዘፍ.፳፪፥፲፫] ያዕቆብ በቤቴል ድንቅ መሰላልን ተመልክቷል:: [ዘፍ.፳፰፥፲፪] ሙሴ በጽላቱ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: [ዘጸ.፴፬፥፳፱, ዘሌ.፲፥፩]

- የአሮን በትር ስትለመልም ድንቅ ተአምራቱ እመቤታችንን ያሳያል:: ኢሳይያስ የድንግልን መጽነስ "ምልክት [ተአምር] ይሰጣቹሃል" ሲል ገልጾታል:: [ኢሳ.፯፥፲፬]

- በሐዲስ ኪዳንም የድንግል :-

- ያለ በደል መጸነሷ:
- ንጽሕት ሆና መወለዷ:
- በቤተ መቅደስ ለ፲፪ ዓመታት ምድራዊ ምግብን አለመመገቧ:
- ያለ ወንድ ዘር መጸነሷ [ሉቃ.፩፥፳፮] :
- ያለ ምጥ መውለዷና
- በልደት ዕለት የታዩ ተአምራት [ሉቃ.፪፥፩] :
- እናትም: ድንግልም መሆኗ [ሕዝ.፵፬፥፩] ሁሉ በራሱ ድንቅ ተአምር ነው::

- ከዚህ ባለፈም በቃና ዘገሊላ ያደረገችውን ዐይነ ልቡናው ከታወረበት ሰው ውጪ ዓለም ያውቃል:: [ዮሐ.፪፥፩] ባለ ራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ:-

- "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ:: ፀሐይን ተጐናጽፋ: ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት: በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች" ብሎ የእመቤታችን መገለጥ [መታየት] በራሱ ተአምር መሆኑን ነግሮናል:: [ራዕይ.፲፪፥፩]

- ድንግል እመቤታችን በሕይወተ ሥጋ ከሠራችው ተአምራት በበዛ መንገድ ላለፉት ፪ሺ ዓመታት ስትሠራ ኑራለች:: እየሠራች ነው:: ገናም ትቀጥላለች:: ለሚያምናት ተአምራትን መሥራት ብቻ አይደለም: ነፍሱንም ከሲዖል ታድነዋለች::

- ሁሉን ቻይ ልጅ አላትና እርሷም ሁሉን ትችላለች:: እንኩዋን የፈጣሪ እናት ድንግል ማርያም የክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያቱም "የሚሳናችሁ የለም" ተብለዋል:: [ማቴ.፲፯፥፳]


🕊  †  ቅዱስ ደቅስዮስ  †  🕊

- ይህ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ በዘመነ ጻድቃን አካባቢ እንደ ነበረ ይታመናል:: ከምናኔ ሕይወቱ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ የጥልጥልያ ሃገር ዻዻስም ነበር:: ይሕ ቅዱስ ሰው በእውነቱ ያስቀናል::

- እመቤታችንን ሲወዳት መንጋትና መምሸቱ እንኩዋ አይታወቀውም ነበር:: ፍቅሯ በደም ሥሮቹ ገብቶ በደስታ ያቃጥለው ነበርና ዘወትር እያመሰገናት አልጠግብ አለ:: የሚያስደስትበትን ነገር ሲያስብ ደግሞ የተአምሯ ነገር ትዝ አለው::

- ከዚያ በፊት የእመቤታችን ተአምሯ በየቦታው ይነገራል: ይጻፋል: ይሰበካል:: ግን በአንድ ጥራዝ አልተያዘም ነበርና በሱባኤ: በፈጣሪው እርዳታ: በፍጹም ድካም የእመ ብርሃንን ተአምራት ሰብስቦ በአንድ ጠረዘውና ለአገልግሎት ቀረበ::

- እርሷን ከመውደዱ የተነሳ ይህንን አድርጉዋልና እመ ብርሃን ወደ እርሱ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ ደስ አሰኘኸኝ" አለችው:: መጽሐፉንም ተቀብላው ባረከችው:: "አመሰግንሃለሁ" ብላውም ተሰወረችው::

- በዚህ ጊዜ ቅዱሱ ሐሴትን አደረገ:: [እመቤታችን ማየት እንዴት ያለ ሞገስ ይሆን!]
ቅዱስ ደቅስዮስ ግን ፍቅሯ እንደ እሳት ልቡን አቃጠለው:: አሁንም ደስ ሊያሰኛት ምክንያትን ይሻ ነበር::

- እመቤታችን ጌታን የጸነሰችበት በዓል [መጋቢት ፳፱] ሁሌም ዐቢይ ጦም ላይ እየዋለ ለማክበር አይመችም ነበርና ቅዱሱ ታሕሳስ ፳፪ ቀን ሊያከብረው ወሰነ:: በሃገሩ ያሉ ክርስቲያኖችን ጠርቶ ታላቅ በዓልን ለድንግል አከበረ::

- ሕዝቡም ጸጋ በዝቶላቸው ስለ እመቤታችን ታላቅ ሐሴትን አደረጉ:: በዚያች ሌሊትም እመ ብርሃን በሞገስ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ! ዛሬም ፍጹም ደስ አሰኘኸኝ! እኔም ስለ ክብርህ ይህንን አመጣሁልህ" ብላ ሰማያዊ ልብስና ዙፋን ሰጠችው::

- ማንም እንዳይቀመጥበት ነግራው: ባርካው ዐረገች:: ከዚህች ዕለት በሁዋላ ቅዱስ ደቅስዮስ ፈጣሪውንና ድንግል እናቱን ሲያገለግል: ተአምሯን ሲሰበስብ: ምዕመናንን ሲመራ ኑሮ በዚህች ዕለት ዐርፏል:: ከእርሱ በሁዋላ የተሾመው ዻዻስም በድፍረት በእርሱ ዙፋን ላይ በመቀመጡ መልአክ ቀስፎ ገሎታል::

- የእመቤታችንን ተአምር መስማትና ማንበብ ያለውን ዋጋ የሚያውቅ ጠላት ሰይጣን ግን ዛሬም ድረስ ባሳታቸው ሰዎች አድሮ ተአምሯን ይቃወማል:: " እኛ ግን ለእመቤታችን እንሰግዳለን!! ተአምሯንም እንሰማለን!! ጥቅማችን እናውቃለንና!! "

- ለመረጃ ያህልም :-

- የእመቤታችን ተአምር የሰበሰበ [ ቅዱስ ደቅስዮስ ]
- የተአምሯን ሥርዓት ያዘጋጁ [ ቅዱሳን አበው ማቴዎስ: ማርቆስና አብርሃም ሶርያዊ ]
- እሰግድ ለኪን የደረሰው [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ]
- የተአምሯን ሃሌታ [ ቅዱስ ያሬድ ]
- የዘወትሩን መቅድም [ ቅዱሳን ሊቃውንት ] ናቸው::

" ልመናዋ ክብሯ በእውነት ለዘለዓለሙ ይደርብን !! "


🕊  †  ቅዱስ አንስጣስዮስ   †  🕊

የግብጽ ፴፮ኛ ፓትርያርክ የሆነው ይህ አባት በ፮ኛው ክ/ዘ የተወለደ ሲሆን በትጋቱ: በትምሕርቱና በድርሰቱ ይታወቃል:: ምዕመናንን ለማስተማርም ከ፲፪ ሺህ በላይ ድርሰቶችን ደርሷል:: ብዙ መከራዎችን አሳል በ፯ኛው መቶ ክ/ዘ ዐርፏል::






ይህንን ጸሎት በወሬ ነጋሪ የሰማው ያ መኮንን በጣም ተገርሞ በቅዱሱ ፊት ሔዶ በግንባሩ ተደፋ:: "ስጠላህ የወደድከኝ አባት ሆይ! ማረኝ?" አለው:: ቅዱስ ጢሞቴዎስም አስተምሮ አጠመቀው:: ፪ቱም አብረውሲጋደሉ ኑረው ዐርፈዋል::

አምላከ ቅዱሳን በረድኤተ መላእክት ጠብቆ በወዳጆቹ ምልጃ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. አእላፍ [፺፱ኙ] ነገደ መላእክት
፪. ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
፫. "13ቱ" ግኁሳን አበው [ሽፍቶች የነበሩ]
፬. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
፭. አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፬. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

"ስለ መላእክትም :- "መላእክቱን መናፍስት: አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ" ይላል . . . ነገር ግን ከመላእክት :-  "ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ተብሏል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ: የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?" [ዕብ.፩፥፯-፲፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! †

[  † እንኩዋን "ለ፺፱ [ 99 ] ኙ ነገደ መላእክት": "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]


🕊   †  አእላፍ መላእክት †   🕊

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ [፻] : በክፍለ ነገድ አሥር [፲] አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3፫ ሰማያትና በ፲ ከተሞች [ዓለማት] አድርጉዋል::

መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

፩. አጋእዝት [ የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው ]
፪. ኪሩቤል [ አለቃቸው ኪሩብ ]
፫. ሱራፌል [ አለቃቸው ሱራፊ ]
፬. ኃይላት [ አለቃቸው ሚካኤል ]
፭. አርባብ [ አለቃቸው ገብርኤል ]

፮. መናብርት [ አለቃቸው ሩፋኤል ]
፯. ስልጣናት [ አለቃቸው ሱርያል ]
፰. መኩዋንንት [ አለቃቸው ሰዳካኤል ]
፱. ሊቃናት [ አለቃቸው ሰላታኤል ]
፲. መላእክት [ አለቃቸው አናንኤል ] ናቸው::

ከእነዚህም - አጋእዝት: - ኪሩቤል - ሱራፌልና - ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር [በ፫ኛው ሰማይ] ነው::

- አርባብ: - መናብርትና - ስልጣናት ቤታቸው ራማ [በ፪ኛው ሰማይ] ነው::

- መኩዋንንት: - ሊቃናትና - መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር [በ፩ኛው] ሰማይ ነው::

መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ [አገልጋይ] ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት [አራቱ ወቅቶች] እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

- ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ [ዘካ.፩፥፲፪]
- ምሥጢርን ይገልጣሉ [ዳን.፱፥፳፩]
- ይረዳሉ [ኢያ.፭፥፲፫]
- እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ [መዝ.፺፥፲፩]
- ያድናሉ [መዝ.፴፫፥፯]
- ስግደት ይገባቸዋል [መሳ.፲፫፥፳, ኢያ.፭፥፲፫, ራዕ.፳፪፥፰]
- በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ [ማቴ.፳፭፥፴፩]
- በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::


🕊   †   አእላፍ    †   🕊

ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::

ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር ፲፫ ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ፲፫ ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር [በትዕይንት] አገልግሎታቸውም ይነግረናል::

ለምሳሌ :-

- ያዕቆብ = በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: [ዘፍ.፳፰፥፲፪]
- ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: [፪ነገ.፮፥፲፯]
- ዳንኤል ተመልክቷል:: [ዳን.፯፥፲]
- በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: [ሉቃ.፪፥፲፫]
- ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: [ራዕይ.፭፥፲፩]

ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን [አማላጆች] ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::


🕊 † ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ †  🕊

የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::

ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ [ድውይ] ሆነበት:: ለ፴፭ ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::

በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ ፲፫ ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::

መነኮሳትን ይወዳልና ፲፫ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::

ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ ፲፫ በመሆናቸው ጌታ ፲፪ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::

ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ፴፭ ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ፲፫ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::

ጌታ ፲፪ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::

እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: ፲፫ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም ፲፫ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::


🕊  †  ቅዱስ ጢሞቴዎስ  †  🕊

ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና [ግብጽ] ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::

ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::

ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና::"








ከዓመታት የቅድስና ሕይወት በሁዋላም ቅዱስ ሚናስ ሚስቱን አስፈቅዶ በርሃ ገብቷል:: በተጋድሎ ሳለም እግዚአብሔር ለእረኝነት መርጦት: ተመይ በምትባል የግብጽ አውራጃ ላይ ዽዽስናን ተሹሟል:: በዚያም እስካረጀ ድረስ ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

እንደ ደመና የከበቡን የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ በቸርነቱ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት [ቅዳሴ ቤቱ]
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
፫. ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ [ሰማዕታት]
፬. ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
፭. ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ [ጻድቃን ወሰማዕት]
፮. አባ ናሕርው ሰማዕት

[   †  ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. ሥሉስ ቅዱስ [አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ለአንበሳ የተሰጠ]

" የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: " [ዕብ.፲፩፥፴፭-፴፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


🕊

[  †  እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]  

🕊 † ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ  †  🕊

መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ፯ ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ [አንስጣስዮስ] እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም [ልዳ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፳ ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት [የአሁኗ ቤይሩት - ሊባኖስ] ሰዎች ዘንዶ [ደራጎን] ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና ፸ ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ዐውደ ስምዕ] ደረሰ::

ከዚያም ለተከታታይ ፯ ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: ፫ ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው" : "ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ::
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ::" እንዲል መጽሐፍ::

ከ፯ ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: ፯ አክሊላትም ወርደውለታል::

ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ፫፻፺ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::

ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት [ነገሥታት] መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ፵፯ ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

በ፫፻፭ ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን [ደወሉን] ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ፯ ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::


🕊 † ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ †  🕊

በቤተ ክርስቲያን "ጊዮርጊስ" የሚባሉ ብዙ ቅዱሳን አሉ:: ከልዳዊው ቀጥሎም ይህንን ግብጻዊ ሰማዕት እንጠቅሳለን:: ስሙ ጊዮርጊስ የተባለውም በታላቁ ሰማዕት አማላጅነት ስለ ተገኘ ነው::

አባቱ ኅዳር ፯ ቀን የሊቀ ሰማዕታትን ቅዳሴ ቤት ሊያከብር ሒዶ ስለተማጸኑ የሚስቱ ማሕጸን ተከፍቶለት ልጅ ወልዷል:: ስሙንም ጊዮርጊስ ብሎታል:: ባደገም ጊዜ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ሆነ::

የግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብርታቱ ምንድን ነው ቢሉ :-ንጹሕ አምልኮቱ ጾምና: ጸሎቱ: በጐ ምጽዋቱ ነው:: "ስም ይመርሕ ኀበ ግብር - ስም ወደ ተግባር ይመራል" እንዲሉ አበው የሰማዕቱን ስም ይዞ እሱም ይሔው እድል ገጠመው::

በአጋጣሚ ወላጆቹ ሲሞቱ የሚኖረው ከከተማው መኮንን ቤት ነበር:: ምክንያቱም የመኮንኑ ሚስት እህቱ ናትና:: ችግሩ ግን መኮንኑ አርማንዮስ ጣዖት አምላኪ: በዚያ ላይ ጨካኝ መሆኑ ነው::

አንድ ቀን ግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመኮንኑን ሴት ልጅ ወደ በርሃ ወስዶ የደብረ ቁስቁዋም መነኮሳትን ዝማሬ አሰማት:: ክርስትናንም አስተማራት:: ይህንን የሰማው መኮንኑ ግን በብስጭት ቅዱስ ጊዮርጊስንና የራሱን ሴት ልጅ በአደባባይ አሰይፏቸዋል:: የክብርን አክሊልም ተቀዳጅተዋል::


🕊  † ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ † 🕊   

እነዚህ ቅዱሳን እናትና ልጅ ናቸው:: ዘኖብያ እናቱ ስትሆን ዘኖቢስ ደግሞ ወጣት ልጇ ነው:: የቅዱሳኑ ሃገር ደግሞ ተበይስ ትባላለች:: በዘመነ ሰማዕታት ድንቅ በሆነ ሕይወታቸውና ተአምራቸው እንደ ኮከብ አብርተዋል:: ከ፭ ጊዜ በላይም ከተደገሰላቸው የሞት ወጥመድ በእግዚአብሔር ኃይል አምልጠዋል::

" ክርስትናችን አንክድም: ከክርስቶስ ፍቅር አንለይም በማለታቸው :-

፩. ልብሳቸውን ገፈው: በዓየር ላይ ሰቅለው: ደማቸው እስኪንጠፈጠፍ ገረፏቸው:: በክርስቶስ ኃይል ተረፉ::

፪. የእንጨት መስቀሎችን አሰርተው በአደባባይ ቸንክረው ሰቀሏቸው:: ከዚህም ዳኑ::

፫.. ሁለት ወንበሮች ላይ ችንካሮችን ተክለው በዚያ ላይ አስቀመጧቸው:: አሁንም በፈጣሪ ኃይል ዳኑ::

፬. ጥልቅ ጉድጉዋድ ተቆፍሮ: እሳትም ነዶ በዚያ ውስጥ ተጨመሩ:: ቅዱስ መልአክ ግን ወርዶ አጠፋላቸው::

፭. አንዴ ደግሞ በቤት [በውሽባ ቤት] እሳት ነዶ በውስጥ ተጨመሩና ተዘጋባቸው:: እግዚአብሔር ግን ከዚህም ታደጋቸው:: ስለ ክብራቸውም ቅዱስ መልአክ ወርዶ እነሱን አክብሮ: መኮንኑን ዙፋኑን አሸክሞ በአደባባይ አዙሮታል::

አንዴም ጋን አሸክሞ በሁዋላቸው አስከትሎታል:: በነዚህ ሁሉ ድንቆች ብዙ ሕዝብ እያመነ በሰማዕትነት ሙቷል:: በመጨረሻ በዚህ ቀን ዘኖብያና ዘኖቢስ ሲሰየፉ መብረቅ ወርዶ ፶፬ አሕዛብን ገድሏል:: በዚህም መኮንኑ ተገርሞ በክርስቶስ አምኗል::


🕊  †  አባ ሚናስ ዘተመይ †  🕊

ይህ ቅዱስ አባት ደግሞ ጣዕመ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው በተክሊል አጋቡት:: ወደ ሙሽራይቱ ገብቶም "እህቴ! ይህ ዓለም ኃላፊ ነውና ለምን በድንግልና አንኖርም?" አላት::

እርሷም በደስታ "ይሁን" አለችው:: ለበርካታ ዓመታትም ቀን ቀን ሥራቸውን ሲሠሩ: እንግዳ ሲቀበሉ ይውላሉ:: ሌሊት ደግሞ ወገባቸውን ታጥቀው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ያድራሉ::







18 last posts shown.