🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! †
[ † እንኩዋን "ለ፺፱ [ 99 ] ኙ ነገደ መላእክት": "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † አእላፍ መላእክት † 🕊
እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ [፻] : በክፍለ ነገድ አሥር [፲] አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3፫ ሰማያትና በ፲ ከተሞች [ዓለማት] አድርጉዋል::
መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
፩. አጋእዝት [ የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው ]
፪. ኪሩቤል [ አለቃቸው ኪሩብ ]
፫. ሱራፌል [ አለቃቸው ሱራፊ ]
፬. ኃይላት [ አለቃቸው ሚካኤል ]
፭. አርባብ [ አለቃቸው ገብርኤል ]
፮. መናብርት [ አለቃቸው ሩፋኤል ]
፯. ስልጣናት [ አለቃቸው ሱርያል ]
፰. መኩዋንንት [ አለቃቸው ሰዳካኤል ]
፱. ሊቃናት [ አለቃቸው ሰላታኤል ]
፲. መላእክት [ አለቃቸው አናንኤል ] ናቸው::
ከእነዚህም - አጋእዝት: - ኪሩቤል - ሱራፌልና - ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር [በ፫ኛው ሰማይ] ነው::
- አርባብ: - መናብርትና - ስልጣናት ቤታቸው ራማ [በ፪ኛው ሰማይ] ነው::
- መኩዋንንት: - ሊቃናትና - መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር [በ፩ኛው] ሰማይ ነው::
መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ [አገልጋይ] ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት [አራቱ ወቅቶች] እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
- ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ [ዘካ.፩፥፲፪]
- ምሥጢርን ይገልጣሉ [ዳን.፱፥፳፩]
- ይረዳሉ [ኢያ.፭፥፲፫]
- እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ [መዝ.፺፥፲፩]
- ያድናሉ [መዝ.፴፫፥፯]
- ስግደት ይገባቸዋል [መሳ.፲፫፥፳, ኢያ.፭፥፲፫, ራዕ.፳፪፥፰]
- በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ [ማቴ.፳፭፥፴፩]
- በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
🕊 † አእላፍ † 🕊
ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::
ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር ፲፫ ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ፲፫ ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::
ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር [በትዕይንት] አገልግሎታቸውም ይነግረናል::
ለምሳሌ :-
- ያዕቆብ = በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: [ዘፍ.፳፰፥፲፪]
- ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: [፪ነገ.፮፥፲፯]
- ዳንኤል ተመልክቷል:: [ዳን.፯፥፲]
- በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: [ሉቃ.፪፥፲፫]
- ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: [ራዕይ.፭፥፲፩]
ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን [አማላጆች] ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::
🕊 † ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ † 🕊
የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::
ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ [ድውይ] ሆነበት:: ለ፴፭ ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::
በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ ፲፫ ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::
መነኮሳትን ይወዳልና ፲፫ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::
ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ ፲፫ በመሆናቸው ጌታ ፲፪ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::
ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ፴፭ ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::
በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ፲፫ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::
ጌታ ፲፪ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::
እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: ፲፫ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም ፲፫ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::
🕊 † ቅዱስ ጢሞቴዎስ † 🕊
ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና [ግብጽ] ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::
ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::
ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና::"