ትብል ተዋሕዶ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


🔊 "ለእመ ረሳእኩኪ ቤተክርስቲያን ለትርስአኒ የማንየ"
❖ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
✞ ትምህርቶችን፥
✞ የየዕለቱን ስንክሳር፥
✞ ቅዱሳን ስዕላት፥
✞ ዝክረ ቅዱሳን እና
✞ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው።
በዚህ ቦት ያገኙናል ፤ @demesetewahedo_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ሉቃስ ወንጌል 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
¹¹ ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
¹² በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
¹³ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
¹⁴ እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።

  ┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


“የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤”
  — ኤፌሶን 5፥9-10

         🌹ሠናይ መዓልት ይኵን ለነ🌹
        ✨መልካም ቀን✨

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም) ፥ ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና፥ ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”
" በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት። "

📖 ቅዱስ ያሬድ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ፃዕር ወፃማ፥
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ፥
ማርያም ድንግል ክልልተ ሞገሰ ወግርማ፥
አጽንዒ በረድኤትኪ ለሕይወትየ ድካማ፥
እምሕይወተ ጌራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ።

ትርጓሜ

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ያለመጨነቅና ያለፃዕር ከሥጋዋ ለተለየች ነፍስሽ ሰላምታ ይገባል። አነዋወሯም በልጅሽ ቀኝ ጎን በክብር ነው።
ድንግል ሆይ፤ ከፈጣሪ ዘንድ የባለሟልነትን ግርማን የተጎናፀፍሽ ነሽ። በረድኤትሽ ሰውነቴን ከድካሟ አሳርፊያት ክብሯም (ኃይሏም) ከደጋግ አባቶቿ ክብር (ኃይል) ያነሰ አይሁን።

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የሕይወት የድኅነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን እግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን፤ በጸሎቷም ከክፉ ነገር ይጠብቀን፤ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን! አሜን !

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"ወሶበ እቤ ድኅፃ እገርየ፣ ምሕረትከ እግዚኦ ረድአኒ። "
📖 መዝ. ፺፫÷፲፰

"እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕረትህ ረዳኝ።"
📖 መዝ. 93÷18

         🌹ሠናይ መዓልት ይኵን ለነ🌹
       ✨መልካም ቀን✨

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"ክርስትና ሰዎችን በተወሰኑ ሀሳቦች ማሳመን አይደለም። ይልቁንም ከክርስቶስ ፍቅርና ታላቅነት ይካፈሉ ዘንድ መጋበዝ ነው፡፡ ሰዎችን በጥዑም ንግግር ለመማረክ ብላችሁ ወጥመድ ውስጥ እንዳትወድቁ ጸልዩ፡፡ በትህትናም መናገርን ልመዱ ሰዎችንም በራሱ በክርስቶስ መማረክ ይገባችኋል፡፡"

📖 ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ ፥ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሳችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

📖 ቅዱስ ባስልዮስ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


ማቴዎስ ወንጌል 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
¹⁴ ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።
¹⁵ ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።
¹⁶ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
¹⁷ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል

"ወአሜሃ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምገሊላ ውስተ ዮርዳኖስ ከመ ይጠመቅ እም ኀበ ዮሐንስ"

“ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።”
  — ማቴዎስ 3፥13

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"ክፋትን_ከአንተ_አርቃት"

"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"

 📖 ቅዱስ ባስልዮስ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር" ማለት ምን ማለት ነው ?🤔

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ማለት ሥላሴ ወይም ሦስትነት ወይም ሦስት የመሆን ምሥጢር ትለያለች ትደነቃለችም እንደማለት ነው።

◎ መነሻ ግሶቹም እንደሚከተሉት ናቸው፥

👉🏽 ሠለሰ  - ሦስት አደረገ
ሥላሴ - ሦስት መሆን /ሥስትነት
👉🏽 ረመመ - አደነቀ
ትትረመም- ትደነቃለች
👉🏽 ነከረ - ለየ /አደነቀ
ትትነከር -ትለያለች / ትደነቃለች

ነቅዕ (ምንጭ) ፦ መ/ር ኃይለኢየሱስ መንግስት

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


" ሥላሴ ሳይለያዩ በአንድ መለኮት በአንዲት መንግሥት በአንድ ክብር ጸንተው ይኖራሉ፤ አንድነት በሦስትነት፤ ሦስትነት በአንድነት አለ፤ በዚህ ሁሉ በተረዳ ዕውቀት ጥሩ ንጹሕ በሆነ ልቡና እናምናለን።"
📖 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዘካርያስ

🌹እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!🌹

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


" ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ፤ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል፤ ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።"

ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


🌹እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!🌹

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም የተወለደባት ዕለት ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት። ለእርሱም ከቸር አባቱና ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት፣ ክብር፣ ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን። 

            ✨✨✨መልካም በዓል✨✨✨

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


"አስቀድሞ ነቢዩ ዳዊት በቃልኪዳኗ ታቦቱ ፊት ዘመረ ፤ ይህቺ ታቦት ከቅድስት ድንግል ማርያም ውጪ ማን ሊሆን ይችላል? ታቦቷ በውስጧ የኪዳኑን ጽላት ይዛለች ፤ ቅድስት ድንግል ግን የዚህን ቃልኪዳን ባለቤት ተሸክማለች። የቀደመው ጽላት ውስጥ ሕግ ተጽፏል ፤ የኋለኛይቱ ታቦት ውስጥ ያለው ጽላት ደግሞ ወንጌልን ይዟል። የመጀመሪያዋ ጽላት የእግዚአብሔርን ድምፅ ተሰምቶበታል ፤ እውነተኛዋ ጽላት ደግሞ አካላዊው ቃል አድሮባታል። የቀደመችይቱ ታቦት ከውስጥ እና ከውጭ በወርቅ ያጌጠች ያሸበረቀች ናት ፤ እውነተኛዋ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም በውስጥም በውጭም በድንግልና ጌጥ ያሸበረቀች ናት። የቀደመችይቱ ታቦት በምድራዊ ወርቅ የተዋበች ያጌጠች ናት ፤ እውነተኛዋ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ በሰማያዊ ጌጥ ያጌጠች ናት።"

📖 ቅዱስ አምብሮስ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


🌹እንኳን ለኅዳር ጽዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!🌹

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።እንዲሁም አክሱም ጽዮን የእመቤታችን ጽላት የገባችበት ዓመታዊ ታላቅ በዓል ነው፤ በዚህች ዕለት ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት በተአምራት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኘች።
ገናናዋ ድንግል ሆይ! ከታላቅነት ሁሉ በላይ አንቺ ታላቅ ነሽ ፤ የእግዚአብሔር ቃል መኖሪያ የሆንሽው ሆይ! በታላቅነት የሚተካከልሽ ማን ነው? ድንግል ሆይ! ከፍጥረታት ሁሉ ከየትኛው ፍጥረት ጋር አንቺን አወዳድርሻለሁ? በወርቅ ፈንታ በንጽሕና የተለበጥሽ የ ቃል ኪዳኗ ታቦት ሆይ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ! እውነተኛው መና የተገኘበትን የወርቅ መሶብ የያዘችው ታቦት አንቺ ነሽ! ይኽውም መለኮት የተዋሐደው የአንቺ ሥጋ ነው!"
📖 ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ክብርት እመቤታችን ጽዮን ማርያም ከበዓሏ ረድኤት በረከት ትክፈለን፤ የዓሥራትን ሀገሯን ቅድስት ኢትዮጵያን ትጠብቅልን ሰላም ፍቅር ታድርግልን።
አሜን!

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ፤
በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ፤
ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ፤
በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ትርጓሜ

ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር ክርክር በተደረገ ጊዜ፥
የዘለፋን ቃል ላልተናገረው አንደበትህ ሰላም እላለሁ።
ሚካኤል መልአክ ሆይ ክብርህ ከመላእክት ሁሉ ክብር ከፍ ያለ ነውና፤ በሥዕልህ ፊት ቁሜ ልማናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ እሺ በማለት ፈጥነህ ቃልህን አሰማኝ። 📖 ይሁ 1፥9

📖 መልክአ ሚካኤል

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


''ከሚነበበው ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ለደስታዬ ምንጭ የሆነ ቃል ወደ ጆሮዬ ጥልቅ አለ፥ ይህም ለነፍሴ ዕረፍትን የሠጣት የዚያ ወንበዴ ነገር ነው። ጌታችን እጅግ ብዙ ከኾኑት ጠላቶቹ መካከል ሆኖ ለዚያ ወንበዴ እንዴት እንደራራለት ሰማሁ፥ አቤቱ እኔንም የስምህን ድምጽ ስሰማ በደስታ የምሞላ ባሪያህን ወደዚያች ገነት ውሰደኝ፥ ሕሊናዬ በዚያ ሊመሰጥ ክንፎቹን እያማታ ነውና።"

📖 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🔔 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


🌹እንኳን ለደብረ ቁስቋም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም  አደረሳችሁ! አደረሰን!🌹

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ስድስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገባ በመንገድ ጉዞ ካገኛቸውም ድካም አረፉ።

ሰላም ለአእጋሪከ ውስተ ደብረ ቊስቋም እለ ጌሣ፤
ሕፃነ ማርያም ክርስቶስ አመ ጐየይከ ደወለ ንሒሳ፤
ወአመ በጽሐ ህየ እንዘ ይነሥእ ኃይለ አንበሳ፤
እንተ ሠመርከ በኀድዓት ለነፍሱ ታፍልሳ፤
ሰላም ሰላም ለወልደ ዮሴፍ ዮሳ።

ክብርት እመቤታችን ከበዓሉ በረከት ረድኤት ትክፈለን፤ ሀገራችንን ሰላም ፍቅር ታድርግልን።

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄


“ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፥
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፥
ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር፥
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፥
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር።”

ትርጓሜ

"የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ ተወዳጅ ልጅሽ በጒያሽ (በእቅፍሽ) እንዳለ ይህንን ምስጋና አሳርጊ።"

📖አባ ጽጌ ድንግል (ማህሌተ ጽጌ)

┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄
🌹 @demesetewahedo
┄┉✽‌»‌༺ ═ ✞ ═ ༻»‌✽‌┉┄

20 last posts shown.