ታሕሳስ ፳፬ /24/
በዚችም ዕለት ሰሎንቅያ በምትባል በምስር አገር ሰይጣንን ያነጋገረው አባ ጳውሊ አረፈ።
የዚያችም አገር ሰዎች የሔሮድስ ወገን የሆኑ ክፉዎች ናቸው ለእነርሱም ከውሽባ (ዘማዊ) ቤት ገብተው ያድራሉ አባ ጳውሊም ወደዚያች አገር ደረሰ በሚያደርጉት ነገር አዝኖ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ጀመር።
ጸሎቱንም ሲፈጽም ጥቁር ሰው ከውሽባ ቤት ዕራቁቱን የእሳት ሰይፍ ተሸክሞ መጣ ። አባ ጳውሊም አንተ ማን ነህ ማንንስ ትሻለህ አለው እኔ ሰይጣን ነኝ አንተ ወደርሱ በለመንክ ጊዜ ጌታ ላከኝ አለ ። አባ ጳውሊም ሰዎችን የምታስትበትን ሁሉ ንገረኝ አለው።ሰይጣንም የእግዚአብሔርን ፍቃድ የማያደርጉትን እንደሚያስት ነገረው።
በዚያችም ሌሊት ከእግዚአብሔር የታዘዘ መቅሠፍት ወርዶ በውሽባ ቤት ያሉትን አጠፋቸው ከአምስት ወንዶችና ከአምስት ሴቶች በቀር አልተረፉም። አባ ጳውሊም ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ አላቸው ። በየወሩ አንዲት ቀን ወደ ውሽባ ቤት እየገባን ከሚስቶቻችን ጋር ተድላ ደስታ እንድናደርግ አባቶቻችን አዘዙን በሩንም ዘግተን መብራትንም አጥፍተን ከእጃችን የገባችዋን ሴት ይዘን እንተኛለን አሉት።
ከዚህም በኃላ አባ ጳውሊ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው ከዚህም በኃላ ወደ በዓቱ ተመልሶ ገድሉን በፈጸመ ጊዜ በመልካም ሽምግልና ወደ እግዚአብሔር ሔደ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯