መንፈሳዊ ትምህርት | eotc theology 🔍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


| ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄|
|  ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት!!  |
መዝሙር
ወቅታዊ ጉዳዮች
.. open ..
|____________|
                     \ (•◡•) /
                       \      /
                        ——

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


❗❗❗❗#ሼር_SHARE

❗# አትመኝ ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡
❗# አትቅና ፦ እንደ ቃየን ወንድምህን ትገላለህ፡፡
❗# አትስከር ፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡
❗# ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ
❗# በአባቶች አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡
❗# እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡
❗# በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድትገባለህ
❗# ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡
❗# ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡
❗# ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይትነሣለህ
❗# ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


Mootiin samiif lafaa  ilma kee
Waqni samiif lafaa  mucaa kee
Kadhanaaf ati gara samii hin ilaaltu
Harka keera jira kan ati kadhattu/waaqessitu

Waaqayyoo samiiraa addunyaa daawwate
Kasoominakee arge maariyam si filate
Kan akka kee hin jiruu uumama hunda kessaa
arabnin koowaa'eekee addunyadhaaf labsa

dokimas dhiphuu isaa osson dubatiinii
Rakkoo isaa hubattee argamuu keetiinii
Iddoon atti jirtuu hundumtuu guutuudhaa
Namni sin qabaane jiruunsaa hiruudhaa


Nutoo  hin dandeenyu fuula isaa dhaabachuuf
Sumaaaaf yaa Maariyaam kun kan dnda'aamuuf
Akka sadoom taanee akka gamooraatti
Kadhanaa keetiinii nu gargaari atii

├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን ተክሌ
├───────────────


አዲስ ዝማሬ “ማርያም ማርያም“ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ


#አዝ__

ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)

#አዝ___

መዳኒት ታቅፈሽ  የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)

#አዝ___

በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)


#አዝ___

የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)


├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•


#እንኳን_አስተርእዮ_ማርያም_አደረሳችሁ

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል።
✅ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

♦ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፣ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል።
✅ ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጿል❗

✅ ባሕረ ጥበባት ፈልፈለ ማኅሌት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችንን ሶልያና በማለት በሐዲስ ቅኔ ይቀኝላታል።

♦ለሶልያና ስመ ተጸውኦ መነሻ ግንዱ “ሴሊኒ” የሚለው ልሳነ ጽር (የግሪክ ቃል) ነው ይላሉ የሀገራችን የሰዋስው ሊቃውንት፤ በትርጉም ሶልያና ያለውን የቅዱስ ያሬድን ስያሜ ከሴሌኒ ጋር በአቻ ፍካሬ “ጨረቃ” የሚል ትርጉም ሰጥተውት እናገኛለን።

♦ ቅዱስ ያሬድ “ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፣ ወረደ ወልድ እም ዲበ ልዕልና፣ ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና” አለ። ሶልያና ባረፈች ጊዜ ክብር፣ የክብርም ክብር የተገባው ወልድ ልጇ ክርስቶስ ከልዕልናው በልዕልና ወረደ እናቱን በጠሊሳነ ንግሥ በዚያን ጊዜ ሸፈናት። “ ጠሊሳነ ንግሥ ያለው የክብሯን መንዲል የንግሥናዋን መጎናፀፊያ ነው።


ሶ ➡ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ (ኪዳንሽ ባይኖር ምክንያተ ድኂን የለም)
ል ➡ ልሳንየ ላእላእ ይሴብሀኪ (ዲዳው ትብ አንደበቴ ያመሰግንሻል)
ያ ➡ያንቅአዱ ሀቤኪ ኩሉ ፍጥረት(ፍጥረታት ሁሉ ወደአንቺ ያንጋጥጣሉ)
ና ➡ ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለድንግል፥ (እነሆ የድንግል ታላቅነቷ ተገለጠ)

✅ ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችን ዕረፍት የሰርግ ቀን በተባለ የዕረፍቷ ዕለት ሰማያዊውን ሰርግ በዓይነ ሕሊናችን አቅርበን ዕንድናይ እንዲል ሲል ያመሠግናታል።

ዮም ይባቤ የበቡ
ኃጢዓተ እለ ዘገቡ
በኪዳነ ድንግል ካህን ሥርየተ እለ ረከቡ
ከመ ይባኡ ለወልድኪ ውስተ ከብካቡ
የሊቁ ፍቅር ምንኛ ይደንቃል! የድንግሊቱ የአምላክ እናት “ቃልኪዳኗ” ኃጢአት ሲሰሩ ለኖሩ ሥርየተ የሚያሰጥ “ካህን” ነው ይላል። የታመኑባት ኃጥአን በዕለተ ምጽዓት በደስታ እየዘመሩ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚሻገሩባት አግዓዚት፣ ተጨንቀው ለሚጠሯት ሰማዒት ፣ ወደ ማኅደረ ነፍስ የሚደርሱባት ማዕዶት እርሷው ናትና።

♦የእናታችን የእመቤታችን የእመብርሃን የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን❗

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ሥርዓተ_ማኅሌት _ዘአስተርእዮ _ማርያም_2017.pptx
1.0Mb
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ኦሮሞ እና መላኩ ገብርኤል

* * *

ሰውዬው ኦሮሞ ናቸው። አንድ ቀን ከነቤተሰባቸው ጰነጠጡ። ጌታን ተቀበሉ። ግን ያው አኗኗራቸው ከለመዱት ብዙ የተለየ አልነበረም። መጋቢያቸው አልፎ እየመጣ ይጎበኛቸዋል። ሲመጣ ያየውን ነገር (ዝክር፣ ሰንበቴ ምናምን) ገስፆ ያስተዋቸዋል። እሳቸውም እየሰሙ፣ እየቀነሱ እየቀነሱ ሄዱ።

አንድ ቀን ሲመጣ የዓመቱ ገብርኤልን ደግሰው ፏ እያሉ ያገኛቸዋል። "እንዴ! እናንተ እኮ አሁን በጌታ ናችሁ፣ ይሄንን ማድረግ አትችሉም!" ይላቸዋል። ሰውዬውም በስጨት ብለው፣

"Paastar, Maaram dhiisaa nuunn jettani, dhiisne. Mikaa'ela dhiisaa nuun jettanii, dhiisne. Hin hafa malee Gabreeliidhaan nutti hindhufiina!" አሉ አሉ።

(ፓስተር፣ ማሪያምን ተዉ አልከን፣ ተውን! ሚካኤልን አታክብሩ አልከን፣ ተውን! የቀረ ይቀራል እንጂ በገብሬል አትምጣብን!)

* *

ገብርኤል በኦሮሞ የሚወደደውን ያህል የሚፈራም መልዓክ ነው። ይሄንን የምትገልፅ አንድ አባባል አለች። ሰውዬው በሰንበት እያረሱ ሚካኤል አያቸውና እንዲህ አላቸው አሉ፦

"Akkan an si argeetti Gabreeliin sii hinargiin!"

("እኔ እንዳየሁህ ገብርኤል እንዳያይህ ብቻ!")

* *

መልካም በዓል !

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


መዝሙር ሖረ ኢየሱስ

ከጥር ፲፪ - ፲፰

ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አሕዛብ (ሖ) አርአዮሙ ስብሐቲሁ አምኑ ቦቱ አርዳኢሁ (ሖ) ወይቤሎሙ ቅድሑ ማየ ወምልዕዎን ለመሳብክት እስከ አፉሆን (ሖ) ጥዒሞ አንከረ ሊቀ ምርፋቅ በረከተ ዘአምላክ ገብረ (ሖ) ቤዛነ ተስፋነ ወልደ አምላክ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ

ትርጉም፦

ኢየሱስ በአሕዛብ ውስጥ ድንቅ የሆነ ተአምር እያደረግ በደስታ ወደ ሠርግ ሄደ ጌትነቱን ገለጠላቸው ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት ውኃ ቀድታችሁ ጋኖቹን እስከ አፋቸው ምሏቸው አላቸው አሳዳሪው አምላክ ያደረገውን በረከት ቀምሶ አደነቀ ወልደ አምላክ ቤዛችን ተስፋችን ነው ውኃውን ወይን አደረገው

የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፪፥፩ - ፲፪፤
፩ዮሐ ፭፥፩ - ፲፫፤
ግብ ፲፥፴፬ - ፴፱፤

የዕለቱ ምስባክ፦

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን መዝ ፹፫፥፮

ትርጉም፦ 

የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና
ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል

ምሥጢር፦ 

ዘሩባቤል መምህረ ሕግ ነውና በረከትን ይሰጣል። አንድም መምህረ ሕግ ዘሩባቤል በረከትን ይሰጣል ይሰጣልና ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳል ይሄዳልና የካህናት ፈጣሪ በሰባ ዘመን ሚጠተ ሥጋውን በማድረግ ይገለጣል።

አንድም ሊቀ ጳጳሳት መምህረ ሕግ ነውና በረከትን ይሰጣል አንድም መምህረ ሕግ ሊቀ ጳጳሳት በረከትን ይሰጣል ይሰጣልና ከእውቀት ወደ እውቀት ይሄዳል ይሄዳልና የካህናት ፈጣሪ በአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በማኅፀነ ማርያም በልብሰተ ሥጋ ይገለጣል።

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፪፥፩ - ፲፬

ቅዳሴ፦ዘዲዮስቆሮስ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ዘመነ አስተርእዮ


"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌷🌹🌺
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
  ፪.፩.፫, #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
#ከጌታ_ጽንሰት_እስከ_ቀራኒዮ_ያደረገችው_አገልግሎት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ተመርጣ እናት እንደምትሆነው በነቢያት በተነገረው ትንቢት መሠረት አምላክ ዓለሙን ለማዳን የቀጠሮው ጊዜ ሲደርስ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ እመቤታችን ላከው እርሷም ሀርና ወርቅ እያስማማች ስትፈትል ልብሱን እየታጠቀ እየፈታ ለእርሷ የሚገባውን ክብር ሰጥቶ እያመሰገናት ለእግዚአብሔር እናት እንድትሆነው መመረጧን ነገራት እርሷም እኔ ወንድ ስላማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? ብላ ጠየቀችው እርሱም “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” አላት። እመቤታችንም እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ (ገረድ) ነኝ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ አለችው።

በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፈስ ነስቶ የዕለት ፅንስ ሆኗል። (ሉቃ 1፥26)

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከዚህ ይጀምራል። እግዚአብሔር ዓለሙን ለማዳን በወደደ ጊዜ እሺ ብላ እመቤታችን ፍቃደኛ በመሆኗ ከእርሷ ሰው ሆኗልና አባቶቻችን በነገረ ማርያም እንደሚያስተምሩት እመቤታችን በቤተ መቅደስ ሳለች መጽሐፈ ኢሳይያስ ስትመለከት ከትንቢተ ኢሳይያስም 7፥14 ላይ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል። የሚለውን ስታነብ ከዚች ድንግል ከዘመኗ ደርሼ እንጨት ሰብሬላት ውሃ ቀድቸላት ገረድ ሆኜ ባገለገልኳት ብላ ተመኝታ ነበር።

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔርም ትህትናዋን ተመልክቶ ለበለጠው አገልግሎት ለእናትነት መረጣት እርሷም በህቱም ድንግልና ፀንሳው በህቱም ድንግልና ወለዳዋለች።

መላእኩ ለአረጋዊ ዮውሴፍ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዞ ወደ ግብጽ እንዲሰደድ ከነገረው አስነስቶ ንጉሥ ሄሮድስ ሙቶ እስኪመለሱ ድረስ እመቤታችን ብዙ ችግሮችን አይታለች/ተንከራታለች።....

#ከጌታ_ጽንሰት_እስከ_ቀራኒዮ_ያደረገችው_አገልግሎት

...እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማስተማር ዘመኑም ከጌታችን አልተለየችም በቅዱስ ወንጌል “የመጀመሪያው ተአምር” ተብሎም የተመዘገበው ተአምር የተከወነው በእመቤታችን ምልጃ ነው። ይኸውም የውሃው ወደ ወይንነት መለወጥ ነው። (ዮሐ 2፥1-11)

በስተመጨረሻም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከመስቀል ሥር ነበረ። ልብን በሚያቃጥል እንባ እያለቀሰች ታዝን ነበር። ከእርሷ ጋር እነ ሰሎሜ፣ እነ ማርያም መግደላዊት ሌሎችም ሴቶች ከደቀ መዝሙርቱም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ቁመው አብረው ያለቅሱ ነበር።

ጌታችንም ለድንግል ማርያም ዮሐንስን እነሆ ልጅሽ አላት ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን ደግሞ ድንግል ማርያምን “እናትህ እነኋት” አለው። ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ወደ ቤቱ ወሰዳት። (ዮሐ 19፥26)

ለጊዜው በዮሐንስ አማካኝነት እመቤታችን ለሐዋርያት በእናትነት መሰጠቷን፤ እርሷም እነርሱን በፀጋ ልጅነት መቀበሏን ያሳያል። ለፍጻሜው ግን እኛን ሁላችንን በፀጋ ልጅነት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም መስጠቱን እና ለእኛ ለሁላችን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፀጋ እናት አማላጅ አድርጎ መስጠቱን የሚያመለክት ኃይለ ቃል ነው።

ለዋርያትም ከጌታችን ሞት እና ትንሣኤ እንዲሁም በ40ኛው ቀን ማረግ በኋላ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋውን እንደሰሙ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በማርቆስ እናት ቤት ዘግተው ደጅ ሲፀኑ (ሲፀልዩ) በመካከላቸው እመቤታችን አብራ እንደነበረች ቅዱስ ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት መጽሐፍ ምስክር ሁኗል። (ዮሐ ሥራ 1፥14)

“እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር” እንዲል። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ለስብከት በየአህጉሩ ሲፋጠኑ እመቤታችን አልተለየቻቸውም ነበር። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ድርሰቱ“ ሞገሰ ስብከቶሙ ለሐዋርያት” ብሎታል። ትርጉም የሐዋርያት የስብከታቸው ሞገስ አንቺ ነሽ ማለት ነው።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አገልግሎት ለመግቢያ ያህል ጠቀስን እንጅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አገልግሎት ከነቢያት ከሐዋርያት ከቅደሳን ሁሉ የበለጠ በፍፁም እምነት ከእናተነት ፍቅር ጋር ልዑል እግዚአብሔርን ያገለገለች እናት ናት።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰


#ቀጣይ_ትምህርታችን-->የእመቤታችን ልደት በነገረ ድኅነት
    
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


#እናታችንቅድስት_ኪዳነምህረት

"ከመረጥኋቸዉ ጋር ቃል_ኪዳኔን አደረግኹ"መዝ.88፥3

👉በስመ አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን

👉 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው
እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ.9፥16

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የአበዉ ነብያት ረድኤት በረከት አይለየን "አሜን🤲🤲🙏🙏


#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ #ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3#ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡
#በነገታው_በጥር_16ም  #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው
#ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡
#በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡
፠ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡
፠ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡
፠ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን (ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡
፠ እናቴ ሆይ አናንያ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋjት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መጽሐፍ እኔን ፋቀኝ...›› ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግሥተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈጽምና ድል እንነሣ›› አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ እያለች እየነገረችው ሳለ አንሠተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡
፠ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤
* በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡
* ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡
* ዐሥራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡
* በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው
* የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡
* በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡
(ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡)
፠ ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡
፠ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡
፠ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
፠ #በነገታው_በጥር_16ም  #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው።

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ጥር 10 የገሐድ ጾም ነው ግን ቀኑ ቅዳሜ ስለሆነ ከእንስሳት ተዋጽኦ ብቻ ነው የምንፆመው ቅዳሜ ከየትኛውም ምግብ የምንከለከለው የትንሣኤ ዋዜማ ብቻ ነው ምክንያቱም አክፍሎት ስለሆነ !
#Share@dnzema


"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
    ፪.፩.፪, #ጥንተ_አብሶ
ጥንተ አብሶ ማለት የውርስ ኃጢአት ማለት ነው። ይህም ከአዳም መረገም የተነሳ በሰው ልጆች ከአንዱ ወደ አንዱ በዘር የሚወረስ ቁራኝነት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከዚህ ሁሉ ማለት በዘር ከሚሆነው ኃጢአት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጠብቋታል።

"መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እም ከርሰእማ" እንዲል ይህንንም ነቢዩ ኢሳይያስ ሲያረጋግጥ እንዱህ ብሏል ት.ኢሳ 1፥9 "እግዚአብሔር ፀባኦት እመ ኢያትረፈ ለነ ዘርዐ ከመ ሰዶም እም ኮነ ወከመ ገሞራ እመሰለነ" ትርጉም፦ አሸናፊ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር በማለት እንደተናገረ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላክ ጥበብ ከእናቷ ማሕፀን ጀምራ በአዳም በደል ከመጣው ከመርገመ ሥጋ እና ከመርገመ ነፍስ ተጠብቃ ያለች ንጽሕት ዘር መሆኗን ትንቢት ተናግሮላታል።

ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት በእመቤታችን የተፈፀመ ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት መሆኑን ቅደስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ መስክሯል። "ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምዕለተ ፀጋ እግዚአብሔር ምስላኪ" ትርጉም ፀጋን የተመላሽ ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው ቡርክት አንቲ አንስት አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። (ሉቃ 1፥28) በማለት መልአኩ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

ይህንን የነቢዩ የኢሳይያስንና የመልአኩ የቅደስ ገብርኤልን ምስክርነት በመያዝ በርካቶች ቅደሳን አባቶችም ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላካዊ ጥበብ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ (ከጥንተ አብሶ) ተጠብቃ የኖረች ንጽህት ዘር ስለ መሆኗ በስፋት መስክረዋል።

ከሊቃውንቱ መካከል ማህቶተ ቤተ ክርስቲያን የተባለው ቅዱስ ያሬድም በድጓ ድርሰቱ እንዲህ ብሏል “ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመባሕርይ ፀዐዳ” ትርጉም ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች ማለት ነው። (ድጓ ገጽ 379) ይህ ማለት ዕንቁ ባሕርይ ክርስቶስን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች አዲስ መዝገብ የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያም አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስን በመብላቱ ምክንያት ከመጣበት የሥጋና የነፈስ መርገም በጌታ ጥበብ ተጠብቃ የኖረች መሆኑን ሲገልጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች ብሏል።

ምሥጢሩ ይህቺን ነጭ ዕንቁ ከደፈረሰ ባሕር ውስጥ ቢጥሏት እንኳን የደፈረሰው ባሕር የርሷን ጥራት ሳይለውጠው በደፈረሰው ባሕር ውስጥ ሳለች አብርታ እንደምትታይ ሁሉ ልክ እንደ ዕንቁዋ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም በአዳም ትዕዛዝ መተላለፍ ከመጣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ በአምላካዊ ጥበብ ተጠብቃ በንፅሕናና በቅድስና ፀንታ የተገኘች መሆኗን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በሚገባ ገልጿታል።

መኃ.4፥7 ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም ጠቢቡ ሰልሞንም መንፈስ ቅዱስ የእመቤታችን ነገር እንደገለጠለት ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም ብሎ ተናገረ ለጊዜው መልክ ከደም ግባት ጋር አስተባብራ በመገኘቷ ይህ ተነግሮላታል። ለፍፃሜው ግን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጥንተ አብሶ የሌለባት ንፅህት መሆኗን የሚያስረዳ ኃይል ቃል ነው።
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታ ጽንሰት እስከ ቀራኒዮ ያደረገችው አገልግሎት
    
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


" በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው። ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " -  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት


መዝሙር ይሠርቅ ኮከብ

ከታኅሣሥ ፳፱ - ጥር ፭

ይሠርቅ ኮከብ እምያዕቆብ ወየአትት ኃጢአተ እምእስራኤል ወአነሂ በኲርየ እሬስዮ ልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር (ወ) ወይከውን ምስማከ ለኲሉ ምድር (ወ) ውስተ አርእስተ አድባር (ወ) ዮምሰ በሰማያት ይትፌሥሑ ሠራዊተ መላእክት ወአነሂ በኲርየ እሬስዮ

ትርጉም፦

ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤል ኃጢአትን ያስወግዳል እኔም በኲር አደርገዋለሁ ከነገሥታት ይልቅ ልዑል ነው ከተራራዎችም በላይ ነው ዛሬ በሰማያት የመላእክት ሠራዊት ደስ ይሰኛሉ።

የዕለቱ ምንባባት፦

ሮሜ ፲፩፥፳፭ - ፍ፤
፩ዮሐ ፬፥፩ - ፱
ግብ ፯፥፲፯ - ፳፫

የዕለቱ ምስባክ፦

ወአነሂ በኵርየ እሬስዮ
ወልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር
ወለዓለም አአቅብ ሎቱ ሣህልየ መዝ ፹፰፥፳፯

ትርጉም፦

እኔም በኲሬ አደርገዋለሁ
ከምድር ነገሥታት ይልቅ ከፍ ያለ ነው
ይቅርታዬን ለዘለዓለም እጠብቅለታለሁ

ምሥጢር፦

በኲረ ምእመናን በኲረ መንግሥት አደርገዋለሁ
በአራቱ ማዕዘን ከነገሡ ይልቅ ልዑል ንጉሥ አደርገዋለሁ
መሐላዬን ለዘለዓለም አጸናለታለሁ

መልእክት፦

በኲር አደርገዋለሁ የሚለው በገጸ ንባቡ ሰጪና ተቀባይ ያለ ይመስላል።
ቅድምና ያልነበረው ሥጋ ቀዳማዊ አምላክ መባሉ፣ ደኃራዊነት የሌለው መለኮት ደኃራዊ ሥጋን ተዋሕዶ ዘመን የሚቆጠርለት መሆኑን፤ በገዥነት ታይቶ የማይታወቅ ሥጋ በገዥነት መታየቱ፣ በተገዥነት ታይቶ የማይታወቅ መለኮት በተገዢ ሥጋ ተገልጦ መታየቱ የሚነገርበት ምሥጢር ነው።

በኲር የሚለው ቃል የሚከተሉትን ዋና ነጥቦችን በግልጽ የሚያስረዳ ቃል ነው።

፩ በኲረ አብ - የአብ በኲር፤

"ወአመ ፈነዎ ለበኲሩ ውስተ ዓለም ይቤ ይሰግዱ ሎቱ ኲሎሙ መላእክተ እግዚአብሔር - በኲሩን ወደ ዓለም በላከው ጊዜ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይሰግዱለታል አለ" እንዲል ዕብ ፩፥፮

ይህም ማለት ቃል ሥጋ በሆነ ጊዜ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ስለሆነ መላእክት የሚሰግዱት በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ለሆነው ነው ማለት ነው። ዘሰገደ ለሥጋ ሰገደ ለቃል ወከማሁ አበዊነ ሐዋርያት ሶበ ሰገዱ ለሥጋ ቅዱስ ሰገዱ ለእግዚአብሔር ቃል ወከማሁ መላእክትኒ ኮኑ ይትለአኩ ለአርአያ ሥጋ ወየአምሩ ከመ ውእቱ እግዚኦሙ ወይሰግዱ ሎቱ - ለሥጋ የሰገደ ለቃል ሰገደ ዳግመኛ አባቶቻችን ሐዋርያት በተዋሕዶ ለከበረ ሥጋ በሰገዱ ጊዜ ለእግዚአብሔር ቃል ሰገዱ መላእክትም እንዲሁ ሥጋን አይተው ያገለግሉ ነበር ጌታቸው እንደሆነ አውቀው ይሰግዱለታል እንዲል። አቡሊዲስ ፵፩፥፪

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በድርሳኑ፦
"እስመ ብሂሎቱ አመ አብኦ (ፈነዎ) ለበኲሩ ውስተ ዓለም ዝ ብሂል አመ አኮ(?)ነኖ በዲበ ዓለም ወእምዝ ሶበ አእመርዎ ይእተ ጊዜ መለከ ኲለንታሁ - ወደ ዓለም በላከው ጊዜ ማለቱ በዓለም ላይ አሠለነጠው/እንዲፈርድ አደረገው ማለቱ ነውና ያን ጊዜ ካወቁት በኋላ ሁሉን ገዛ አንድም ኲለንታ አካሉ ኲለንታ ባሕርዩ ኲለንታ ትስብእቱ ኲለንታ መለኮቱ ሁሉን ገዛ" ብሎ አመሥጥሮታል።

ይህ ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ሲያብራራ፦

"ወኢይቤ ዘንተ በእንተ እግዚአብሔር ቃል አላ በእንተ ሥጋሁ - አሠለነጠው ማለትን ስለ እግዚአብሔር ቃል አንድም ስለቃልነቱ አልተናገረም ስለ ሥጋ አንድም ሰው ስለመሆኑ ነው እንጂ" ብሏል። ድር ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፫፥፳፬፤

ወደስሕተት መውደቅ የሚመጣው እንዲህ ያለውን ድንቅና ጥልቅ ምሥጢር በዚህ መንገድ አለመረዳት ሲኖር ነው።

ማነጻጸሪያ ጥቅሶች፦

"እስመ ኢፈነዎ እግዚአብሔር ለወልዱ ውስተ ዓለም ከመ ይኮ(?)ንኖ ለዓለም ዘእንበለ ከመ ያሕይዎ ለዓለም በእንቲአሁ - በዓለሙ ይፈርድፈበት ዘንድ እግዚአብሔር ልጁን አላከውም በእሱ ዓለሙን ሊያድን ነው እንጂ" ዮሐ ፫፥፲፯፤

"እስመ አብሰ ኢይኴንን ወኢመነሂ አላ ኲሎ ኲነኔሁ አፈወዮ ለወልዱ - አብ በማንም ላይ አይፈርድም ፍርድን ሁሉ ለልጁ ሰጠው እንጂ" ዮሐ ፭፥፳፪፤

ይህም ከላይ እንዳልነው ነገረ ተዋሕዶን አጉልቶ የሚያሳይ ነው።

፪ በኲረ ድንግል - የድንግል በኲር፤

ከአብ ያለ እናት በመወልድ በኲር እንደተባለ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ያለ አባት በመወለድ በኲር ተብሏል።

ቅዱስ ያሬድ "ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር - በሰማያት እናት የሌለችው በምድርም አባት የሌለው እንደሆነ እናምናለን" ብሎ እንደዘመረ።

ቅዱስ ሳዊሮስም፦
"ወዘሀሎ በሕፅነ አቡሁ ኮነ በሕፅነ ማርያም ወዘወለዶ እግዚአብሔር አብ በምሥጢር ዘኢይትረከብ እንበለ መንጸፈ አንስት ወለደቶ ማርያም በሥጋ በምሥጢር ዘኢይትረከብ እንበለ ሩካቤ ተባዕት
- በአብ ዕሪና ያለ እርሱ በማርያም እቅፍ ተይዞ ታየ እግዚአብሔር አብ በማይመረመር ምሥጢር ያለ እናት የወለደውን ማርያም በማይመረመር ምሥጢር ያለ ዘርዐ ብእሲ በሥጋ ወለደችው" ብሏል ሃይ አበው ፹፭፥፴፯፤

፫ በኲረ ምእመናን - የምእመናን በኲር፤

ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ "ከመ ይኩን ውእቱ በኲረ በላዕለ ብዙኃን አኃው - በብዙ ወንድሞች ላይ በኲር ይባል ዘንድ ማለትም በኲረ ምእመናን ይባል ዘንድ የጠራቸውን አጸደቀ" ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል ሮሜ ፰፥፳፱፤

፬ በኲረ ትንሣኤ - የትንሣኤ በኲር፤

"ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን - አሁንም ክርስቶስ ከሙታን አስቀድሞ ተነሥቷል" እንዳለ ብፁዕ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ በኲረ ትንሣኤ ይባላል ፩ቆሮ ፲፭፥፳፤

የዕለቱ ወንጌል፦
ማቴ ፪፥፩ - ፲፫
ቅዳሴ፦  ዘዲዮስቆስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


👉🏽👉🏽👉🏽 የ  #እውነተኛ #ክርስቲያን #መገለጫው ምንድንነው ?

✍ፀሀይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሀይ አትባልም ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሯዋ አይደለምና

✍እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባልም መተንፈስ ተፈጥሯቸው ነውና

✍ዓሳ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ሕይወት ያለ ዓሳ መሆኑ ይቅርና ይሞታል

✍አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፦

1. #ሲጸልይ ነው፦  ክርስቲያን ማለት

👉በወልድ ውሉድ

👉በክርስቶስ  ክርስቲያን

👉በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ነው።

✍ልጅ ከሆኑ ደግሞ አባት ማናገር ተፈጥሮው ነው። ጸሎት ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው።

2. #ሲያመሰግን ነው፦ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ብሎ የሚያምን ነው። ስለዚህ ለአንድ ክረስቲያን የሰማይና የምድር ፍሬ እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው።

3. #ሲመጸውት ነው፦ ክርስቲያን ማለት ሀብት ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ መመስከር ነው። ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌለው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው።

4. #ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ነው፦  ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነው። ይህን ለማድረግ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል መናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወለዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


"ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን ነፍስ ላይ ነው፡፡.በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡ እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ ትጎዳቸዋለህ፡፡ በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡ እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡

ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡-
እነርሱም....
✟ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣
✟ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✟ እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


Forward from: ዝማሬ ቲዩብ zemare tube
⚫ ይህ የዘማሪ አቤል መክበብ ዝማሬዎች እና መንፈሳዊ መልእክቶች የሚቀርቡበት ቻናል ነው❕❕❕
├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•

⬜ ምስጢረኛዬ ኪዳነምህረት ግሩፕን ይቀላቀሉ ⬛

@kidanameherat16


✥ ቅዱስ ዳዊት ✥

ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ
ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም
ንበውእ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ

✣ ቅዱስ ያሬድ ✣

ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ በቃለ አሚን

✤ አባ ጊዮርጊስ ✤

ሰላም ለልደቱ እምድንግል በቤቴልሔም ዘበትርጓሜሁ ቤተ ኀብስት ብሂል

✟ ቅዱስ ቴዎድጦስ ዘዕንቈራ ✟

ወካዕቤ ይቤ ይእዜ አስተርአየ እግዚአብሔር ዮም እምቅድስት ድንግል ወነበረት ድንግል በድንግልናሃ ከመ ቀዳሚ ወኮነት እመ ወዘያማስን  ሕይወተ ኢገብረ ሙስና ወዘይሁብ ሕይወተ ኢያማስነ ወኢምንተኒ

ዳግመኛም ዛሬ እግዚአብሔር ከቅድስት ድንግል ተወልዶ ታየ ድንግልም እንደ ቀድሞዋ በድንግልናዋ ጸንታ ኖረች እናትም ተባለች ሕይወትን የሚለወጥ በድንግል ተፈትሖ ማኀፀንን አላመጣም ሕይወትንም የሚሰጥ በድንግልና መውለድ ምን አላስቀረም አለ

❖ አባ አርከ ሥሉስ ❖

ሰላም ለልደትከ ጥንተ ኆኀያተ አልፋ በከርሠ ማርያም ድንግል ርስሐተ ዓለም ዘኢለከፋ እምኂሩትከ መዋዒት ዘኢይትረከብ ሱታፋ በገዳመ ልብ እምጽንፋ እስከ ጽንፋ ምሉዐ ትፍሥሕት አኀደርከ በተስፋ

✞ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ✞

ወበዊኦሙ ውስተ ቤት ርእይዎ ለሕፃን ምስለ ማርያም እሙ ወወድቁ ወሰገዱ ሎቱ ወአርኀዉ መዛግብቲሆሙ ወአብኡ ሎቱ አምኃ ወርቀ ወስኂነ ወከርቤ

✟ ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል ✟

ዘእንበለ ትወለድ እንተ ማህምም ወወለደት ተባዕተ

ሳታምጥ ወለደችው ምጥም ሳያገኘት ወንድ ልጅን ወለደች

ታኀሣሥ ፳፱ በዓለ ልደተ ክርሰቶስ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

የዓለም መድኃኒት የፍጥረታት ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ በእውነት ዛሬ ተወለደ

ቸር በዓል ያድርግልን ብርሃነ ልደቱ ለሁላችንም ያብራልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን መልካሙን ያምጣልን በሰላም በጤና ጠብቆ ከቁጥር ሳያጎል ለአመቱ በሰላም ያድርሰን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

 
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


  “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
  — ሉቃስ 2፥11

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳቹ አደረሰን

20 last posts shown.