ተሐድሶም አብሮ እንዳይገፋ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ የቤተክርስቲያ መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየሠራች መኾኑን በራሷ የትስስር ገጾች አመልክታለች። ቤተክርስቲያኒቱ በተለይም፣
" ... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ
* በአስተምህሮቿ
* በዕምነቷ
* በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል ..." በማለት ገልጻለች።
ከዚህም የተነሳ፣ " ...ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።" ብላለች።
ከዚህ በዘለለም ጉዳዩ ወደ ክስ ጭምር ሊያመራ እንደሚችል ጠቁማለች።
ይህ አቋሟን በተወሰነ መንገድ ከሚደግፉት መካከል ነኝ። ምንም እንኳ ቤተ ክርስቲያኒቱ ኹለንተናዊ ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት ባምንም፣ በጥላቻ፣ በማናናቅ፣ ርኅራኄ በራቀውና በመሳለቅ ሊኾን ይገባል ብዬ አላምንም። አያሌ ስህተቶች፤ እልፍ እንከ*ኖች፤ የታጨ*ቁ ግድፈቶች በሌላ የስህ*ተት መንገድና የግዴለሽነት ተግባር ይስተካከላሉ የሚል አቋም የለኝም።
እንዲህ የሚያደርጉ አካላት አንዳንዶቹ፣ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በግል እስከ መካሰስ የደረሱ ናቸው፤ ውስጣቸው ንቀትና ጥላቻ የተመላ ከመኾኑም ባሻገር፣ ርኅራኄ አልባ ናቸው። በትክክል የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት የማያውቁም አሉ፤ እኒህን ማስተካከልና መግራት የሚቻል ይመስለኛል። ሌሎች ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን በግልጥ ቃል "ጋለሞታ፤ የሞተች ..." በማለት የሚጠሩም አሉ። በልዩነት ደግሞ የቤተክርስቲያኑን መመለስና መታደስ ናፍቀው፤ ልብዋን ወደ ወንጌል እንድታቀና የሚተጉላት፤ ተስፋና ዕድል አላት ብለው ሳይሰለቹ ስህተቷንና እንከኖቿን በሙግት፣ ብርታትዋን ደግሞ በማጽናት፤ በጸሎትም ከልብ በማሰብ የሚሠሩ ጥቂቶችም አሉ።
ፍርሃቴ ወይም ስጋቴ
ቤተክርስቲያኒቱ በሚደረግባት አሉታዊ ጫናዎች ተሐድሶን ጨርሶ እንዳትገፋ ፍርሃትም፤ ስጋትም አለኝ። ቤተክርስቲያኒቱ ተሐድሶን ከመግፋት ይልቅ ከዚህ በፊት ተቀብለው እንደ ጀመሩት አበው፣ ብታስቀጥል ትጠቀማለች እንጂ አንዳች አትጎዳም። ለሲኖዶስ በቀረቡት ተደጋጋሚ ጥቆማዎች የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ቁጥር መቀነስ ኹነኛ ምክንያቱ የወንጌል በትክክል አለመሰበክና ብሎም የወደቀ "የጽድቅ ሕይወት" መኖር መኾኑ ተጠቅሶአል።
እናም ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ክስና ሕጋዊ እርምጃ የምታመራውን ያህል ለተሐድሶም እጇን ብትዘረጋ መልካም ነው የሚል እምነት አለኝ።
ጌታ እግዚአብሔር በመግቦቱና በትድግናው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በወንጌልና በማይለወጠው የጽድቅ ቃሉ በተሐድሶ ይጎብኝ፤ አሜን።
የጡመራ መድረክ አድራሻ - https://abenezerteklu.blogspot.com/2025/01/blog-post_27.html?m=1