"ሊቃውንቱና መምህራኑ" እንዴት ከመጽሐፉ ተራራቁ?!
ደግሜ ቤዛ ለሚለው ቃል የተሰጠ ፍቺ ልጥቀስ፣ " ... ቤዛ ማለት፦ “... ካሣ፣ የደም ቤዛ፣ አንዱ ሰው የሰውን ደም ስለሚያፈስሰው ለውጥ ወይም ዋጋን፣ ገንዘብን፣ ካሣን መስጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው።” ይላል የከሣቴ ብርሐን መዝገበ ቃላት። (ከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት፤ 1951 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ገፅ 532)። ጌታችን ኢየሱስ ስለ ቤዝወት በተናገረ ጊዜ እንዲህ አለ፣ "የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" (ማቴ. 20፥28፤ ማር. 10፥45) ብሎአል።
በመላው ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ብሎ የተናገረ ከኢየሱስ በቀር ሌላ የለም። ጌታችን ኢየሱስ እኛን ከኀጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት ምትክና ምስያ የሌለውን ሕይወቱን፣ ለእኛ ምትክ አድርጎ በቤዛነት አቅርቦአል። የወንጌላቱ ንባባት በግልጥ የሚያሳዩት፣ ክርስቶስ በእኛ ቦታ ቤዛና ዋጆ መኾኑን ነው። ቅዱስ ጳውሎስ፣ “ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ” (1ጢሞ. 2፥6) ብሎ ሲናገር፣ ጌታችን ኢየሱስ ለመላለሙ ቤዛ ኾኖ መሰጠቱን ያመለክታል።
በወንጌላትም ኾነ በመልዕክታት ውስጥ፣ ስለ ኀጢአት የተደረገ ቤዛነትን በተመለከተ ለኢየሱስ ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም አልተነገረም። ከኀጢአት ሰውን መቤዥ፣ ከኢየሱስ በቀር በሌላ መንገድ የሚቻል ቢኾን፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህን እውነት ጨርሶ ባልሸሸጉ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር የቤዝወትን መንገድ የሠራውና ያዘጋጀው በክርስቶስ መስቀል በኩል ብቻ ነው።
ዳሩ ግን በሰሞኑ የቤዝወት ትምህርት ዙሪያ፣ ኦርቶዶክሳውያን “ሊቃውንትና መምህራን”፣ ከላይ በቅዱሳት መጻሕፍት የተትረፈረፈውንና “ቤዛ ለመኾን አምላክነት ያሻል” የሚለውን የአገሬን ገበሬ አባባል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አጽንተው ይዘው ይገለጣሉ ብዬ እጅጉን ተስፋ አድርጌ ነበር። በተለይም የቤዝወት ትምህርት በቤተ ክርስቲያኒቱ የዳበረና በምልአት የሚነገር ትምህርት ነበር! የሰሞኑ የአባ ገብርኤል፣ “ማርያም ቤዛ አይደለችም” የሚለው ትምህርት ግን የቤተክርስቲያኒቱን "አዋቂዎች" ለትዝብት የጣለ እውነታ ኾኖአል።
ከዚህ የተረዳኹት ትልቅ እውነት፣ የክርስቶስ ቤዝወት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ያህል እንደ ተነቀፈና የማርያም ነገር ደግሞ ምን ያህል ከክርስቶስ በላይ እንደ ኾነ ነው። ይህ ብቻም አይደለም፣ አዋልድና ሌሎች ጽሑፎች ከቅዱሳት መጻሕፍት በላይ ምን ያህል ስፍራ እንደ ተሰጣቸውም ጭምር።
“ሐዋርያዊ መልስ” እንመልሳለን የሚሉት፣ ከጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሌሎቹ ከያሬድ ሌሎቹም ከሌላ … ስለ ቤዝወት ለማስረዳት ይባትላሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሳይጠቅሱ “በክርስቶስ ቤዝወት” ይሳለቃሉ። ፍካሬና ሐቲት፤ ቅኔና ግስ ደርጅቶበታል የተባለው ቤት፣ ስለ ቤዝወት እንዲህ እርጅና ሲጫጫነው ማየት ያሳዝናል። ከዚህ የሚከፋው ደግሞ ለዚኹ ጉዳይ ሲኖዶስ መቀመጡን ስንሰማ ነው። የኦርቶዶክስ ዐይን ማርያም እንጂ ክርስቶስ አለመኾንዋንም አስመስክረዋል። ኢየሱስ ግን እንዲህ ማለቱን ማስታወስ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሚያጠና ተማሪ ታላቅ ጥያቄም፤ መልስም ነው።
“ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማቴ. 16፥26)
የካራ ኦርቶዶክሳውያኑን ተሳልቆና ቤዝወታዊ ነቀፋዎችን ከዚሁ ጋር ላያይዝ።
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24) አሜን።
የብሎግ አድራሻ - http://abenezerteklu.blogspot.com/2025/04/blog-post_23.html