የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሐሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ ።
ዛሬ ጠዋት በተጀመረው በ38 ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተካሄደ ምርጫ ሙሐሙድ አሊየሱፍ ለሊቀመንበርነት የሚያስፈልገውን 33 ድምጽ በማግኘት ቀጣዩ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሆናቸው ተረጋግጧል።
ከህብረቱ ምንጮቻችን ለማወቅ እንደቻልነው በዝግ በተካሄደው 7 ዙር የድምጽ አሰጣጥ የስብሰባው ተሳታፊ መሪዎች ሙሐሙድ አሊየሱፍን ለቀጣዮቹ አራት አመታት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር አድርገው መርጠዋቸዋል ።
ከእርሳቸው ጋር ሲፎካከሩ የነበሩት የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ቢሆንም ለሊቀመንበርነት የሚያበቃውን 2/3 ድምጽ ማግኘት አልቻሉም ።
ሙሐሙድ አሊ የሱፍ ላለፉት 20 ዓመታት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን የበርካታ ቋንቋዎችም ተናጋሪ ናቸው ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews