⚽️ በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ከጊኒ አቻው ጋር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአይቮሪኮስት ከሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ በፊት በዛሬው ዕለት የመጨረሻውን ልምምዱን ያደርጋል፡፡
ቡድኑ በትላንትናው ዕለት የሁለተኛ ቀን ልምምዱን ማድረጉ ሲገለፅ በልምምዱ ላይ 22 ተጫዋቾች መሳተፋቸውና ቢንያም በላይ ግን በጡንቻ ጉዳት ልምምድ አለመስራቱ ታውቋል። የሀዋሳ ከነማው አማካይ ጉዳቱን ተከትሎ በቅዳሜው ጨዋታ የመሰለፉ ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ ስምንት ከዲሞክራቲክ ኮንጎ߹ ጊኒ እና ታንዛንያ ጋር ሲደለደል ዋልያዎቹም በ1 ነጥብ ከምድባቸው ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew
#EBS_SPORTS