ደንበኞች ለሚጠይቁት አገልግሎት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በትጋት መሥራት ይገባል
ደንበኞች ለሚጠይቁት አገልግሎት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በትጋት መሥራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ አሳስበዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም የተጀመሩ የቅድመ መከላከል ሥራዎች እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም ከሥነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር ጋር በተያያዘ ያልተሠሩ ሥራዎች እንዲሁም መሠረተ ልማትን ከሥርቆትና ከጉዳት ለመጠበቅ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች አሁንም ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ተግባራዊ እያደረገው ከሚገኘው የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያ ጋር ተያያዞ ሁሉም ሠራተኞች ተመሳሳይ ግንዛቤ ኖሯቸው ተቋሙ ሊደርስበት ያሰበውን ግብ ለማሳካት በሚደረገውን ጥረት የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያበረክቱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ አንኳር ሥራዎች በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የተቋሙ የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት