ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ተጨማሪ ኃይል ሊሰጥ ነው
ለአዳማ እና ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከአንድ ወር በአነሰ ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ሊሰጡ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማና የሐዋሳ ሪጅኖች አስታውቀዋል፡፡
ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተጨማሪ ኃይል ለመስጠት 766 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ እና 42 ኪሜ የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የተጠናቀቀ ሲሆን 8 ኪ.ሜ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ለኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ቀድሞ ሲያገኝ ከነበረው 20 ሜጋ ዋት በተጨማሪ በ40 ሜጋ ዋት ኃይል ሊያገኝ የሚያስችለው ነው ተብሏል፡፡
ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚደረገው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ ለሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመስጠት የ20 ነጥብ 8 የመሬት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡
ፓርኩ ኃይል ለማቅረብ የቀረው ሥራ ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ማሰራጫ መስመር የማገናኘት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ 19 ምሰሶዎች በማጓጓዝ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአንድ ወር በአነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት የሚደረግ መሆኑ ከአገኘነው መረጃ ተረድተናል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርክ ተጨማሪ መሰረተ-ልማት ለመዘርጋት ያስፈለገው የኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ 21 ኪሎ ሜትር የመሬት ውስጥ የቀጥታ መስመር ለመዘርጋት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት