ለግንባታ ሥራ የተነሱ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው
በአዳማ ከተማ ቁጥር 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ሲከናወን የተነሱ አራት መቶ አባወራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሊደረጉ መሆኑን የአዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጠሃ አህመድ ገለፁ፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙት በአዳማ ከተማ አስተዳደር በቶሌ እና ዋጩ ለፋ ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት የመስመር ዝርጋታ ስራ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡
በተከናወነው ሥራ 17 ነጥብ 5 የዝቅተኛ እና 3 ነጥብ 5 የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሽቦ መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡
አክለውም 3 ባለ 200 ኪ.ቮ.አ እና አንድ ባለ አንድ መቶ ኪ.ቮ.አ ትራንስፎርመር መተከሉን ጠቅሰው ነዋሪዎቹ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታውን ለማከናወን 24 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ወጪውም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሸፈኑን አብራርተዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት