ብጽዕት ነሽ
ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
'አምነሽ የተቀበልሽ ብጽዕት ነሽ ድንግል/2/
በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት አለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልዓክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ሰላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ ሥላሴ
ክብርን የተሞላሽ ምልዒተ ውዳሴ
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ትወልጃለሽ ጌታን በመንፈስቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነገሳል ዘለአለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሠማዩን ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም
እ_ን_ዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ_ም____ር
ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
'አምነሽ የተቀበልሽ ብጽዕት ነሽ ድንግል/2/
በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት አለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልዓክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ሰላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ ሥላሴ
ክብርን የተሞላሽ ምልዒተ ውዳሴ
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ትወልጃለሽ ጌታን በመንፈስቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነገሳል ዘለአለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
አዝ__
ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሠማዩን ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም
እ_ን_ዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ_ም____ር