Forward from: አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
🇨🇬 በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) | ተወዳጆች ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ !
ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡
📖ማቴ 17፥1-9
t.me/AlphaOmega930