🟢🟡🔴
መስከረም 1 |
ርእሰ ዐውደ ዓመት
#
ርእሰ_ዐውደ_ዓመትበግእዝ ዐውደ ዓመት ይባላል - ርእሰ ዐውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተባለ።
[🌼] በዚህች ቀን ከ9ኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ
የከበረ መልአክ ራጉኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል መስከረም 1 ቀን ከሊቃነ መላእክት በብርሃናት ላይ የተሾመበት ዕለት ነው።
ግንቦት 1 ቀን ለታላቁ አባት ለሄኖክ ምሥጢራትን የገለጸበት በዓሉ ነው፡፡
በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ነቢዩ ሔኖክ
"ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡
እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው።
የመልአኩ ልዩ ቃልኪዳን፦
"
የራጉኤል አምላክ ይቅር በለኝ በማለት አንዲት ቃልስ እንኳን ቢናገር እንደ ወዳጄ እንደ አብርሃም፣ እንደ ባለሟሌም እንደ ይስሐቅ፣ እንደ አከበርኩትም እንደ ያዕቆብ ክብርን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ። በራሱ ላይም አክሊል አቀዳጀዋለሁ። ረጅም ዘመናት ሰፊ፣ ወራትም እሰጠዋለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቶታል፡፡
[🌼] ዳግመኛም በዚህች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያ #
ቅዱስ_በርተሎሜዎስ በአሸዋ ከረጢት ውስጥ ተከቶ ወደ ባሕር በመጣል ምስክር ሆኖ ዐረፈ።
[🌼] በዚችም ዕለት #
ጻድቁ_ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ተፈወሰ።
[🌼] ይህች ቀን የታላቁ የቊልዝም ሰው የሆነ ፍጹም ጻድቅ፣ ሰይጣንን አስሮ ዐሥራ አራት ሰው ሊይዙት የማችሉትን ደንጊያ ያሸከመው #
የአባ_ሚልኪ የዕረፍት በዓሉ ነው።#እንኳን_አደረሳችሁ።
T.me/Ewnet1Nat